1.እያንዳንዱን ቀን ተቃቅፎ በመሳሳም ጀምሩት
2.በየቀኑ አንዱ ለሌላው ይጸልይ
3.መጽሐፍ ቅዱስን አብራችሁ አጥኑ
4.ትሑታን ሁን
5.ጨዋ ሁኑ
6.ስጦታ ተለዋወጡ
7.አዘውትራችሁ ፈገግ በሉ
8.ለጋሥ ሁኑ
9.ቀና ሁኑ
10.ይቅር በሉና እርሱት
11.ሌላው የሚፈልገውን ነገር ሌላው ሳይጠይቀው ያድርግ/ታድርግ
12.አድምጡ
13.አበረታቱ
14.ልዩነት ተቀበሉ
15.የእርሱን ወይም የእርሷን ፍላጎት እወቁ
16.የቀደመ የሌላውን ቁርስ ያዘጋጅ
17.በቀን ሁለት ጊዜ ሰላምታ አቅርቡ
18.ቀን ላይ ስልክ ተደዋወሉ
19.አብራችሁ የእግር ጉዞ ስታደርጉ እጅ ለእጅ ተያያዙ
20.አንዱ የሌላውን ሐሳብ ይጠይቅ
21.ፍቅርና አክብሮት አሳዩ
22.ልደቶቻችሁን ደመቅ አድርጋችሁ አክብሩ
23.በፍቅር ቀንና በዓመታዊ በዓላት ወቅት አበባ ተለዋወጡ
24.ስትሳሳቱ ስሕተታችሁን ተቀብላችሁ ይቅርታ ጠይቁ
25.ጉዳያችሁን በእርሱ ወይም በእርሷ መንገድ አድርጉት
26.በማንኛውም አጋጣሚ የተዋቡ ካርዶችን ላኩ
27.የተጋጋለ ክርክርን አስወግዱ
28.ንዝነዛን ከእናንተ አርቁ
29.ችግሮቻችሁን በጋራ ሆናችሁ የጸሎት መፍትሔ ስጡት
30.አብራችሁ ሳቁ
31.በበዓላት ካርዶቻችሁንና የፍቅር ደብዳቤዎቻችሁን አንብቡ
32.እግዚአብሔርና ሰዎችን አገልግሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥም አንድ ሚና ይኑራችሁ
33.”እርሱን/እርሷን ለማስደሰት ምን መድረግ አለብኝ?” ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ
34.ስለ ሕልሞቻችሁ ተነጋገሩ
35.ጨዋ መነካካት አስፈላጊ ነው
36.በሳምንት አንድ ቀን እራት ለመገባበዝ ወይም ባሕር ዳር ለመናፈስና ዜማ ለማዳመጥ ወጣ በሉ
37.ለሌላው ሰው ጥያቄ ሌላኛው ፈጣን ምላሽ ይስጥ
38.ስለ ፍቅራችሁና ስላሳለፋችሁት መልካም ጊዜ ተነጋገሩ
39.አንዱ የሌላውን ጓደኞችና ዘመዶች እኩል ይመልከት
40.አንዱ ለሌለው የሥጋ ተራክቦ ስሜት የነቃ ይሁን 41.ፀሐይ ስትጠልቅ አብራችሁ ተመልከቱ
42.ደጋግማችሁ “አፈቅርሃለው/አፈቅርሻለው”በሉ
43.መጽሐፍ ቅዱስ አብራችሁ አንብቡ
44.ስለ ጋብቻ የሚናገር ጠቃሚ መጽሐፍ አንብቡና ተወያዩበት
45.የእኛ የምትሉት ዜማ ወይም መዝሙር ይኑራችሁ
46.ወቀሳን ማማረርንና ተግሣጽን ከእናንተ አስወግዱ
47.የቀልድና የጨዋታ ስሜት ይኑራችሁ
48.በቤታችሁ ጉዳይ ላይ ተረዳዱ
49.አስፈላጊ ሲሆንም ውጫያዊ እርዳታ ፈልጉ
50.ዕለቱን በመተቃቀፍና በጸሎት አጠናቁት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.