ገብሩ እባላለሁ፤ የ27 ዓመት ወጣት ነኝ፡፡ ታዲያ ችግሬ ምን መሰለህ አንድ የምወዳት ፍቅረኛ አለችኝ፡፡ ጥሩ የሚባል የፍቅር ህይወት አለኝ፡፡ ነግ ግን ወሲብ በምንፈፅምበት ወቅት ገና ብልቴን ሳስገባ አቃጠልከኝ፣ ተቃጠልኩ፣ አሳመምከኝ፣ ታመምኩ፣ እያለች ትጮህ እና ወሲቡን አቋርጣ ትነሳለች፡፡ አረጋግቼ በተደጋጋሚ ብሞክራትም ምንም ለውጥ አይታይባትም፡፡ ምን ላድረግ? እንደዚህ አይነቱ ችግርስ የሚመነጨው ከምን ይሆን?
ገብሩ ነኝ

‹‹በወሲብ ጊዜ እና ከወሲብ በኋላ ህመም እና የማቃጠል ስሜት በብልቴ አካባቢ ይሰማኛል››

ትንሣኤ እባላለሁ የ23 ዓመት ወጣት ስሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ነኝ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የተዋወኩት የምወደው እና የማፈቅረው ጓደኛ አለኝ፡፡ አስበነው ሳይሆን በድንገት ወሲብ መፈፀም ጀመርን፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም አስደሳች የሚባል ወሲባዊ ህይወት ነበረን፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ወሲብ በምንፈፅምበት ወቅት በተለይ ብልቱን ወደ ብልቴ በሚያስገባበት ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል እና የህመም ስሜት ደግሞ ወሲብ የመፈፀም ፍላጎቴን ሙሉ ለሙሉ እንዲጠፋ እያደረገኝ ነው፡፡ ለፍቅረኛዬ በተደጋጋሚ ስለሚሰማኝ ነገር ብነግረውም ሊረዳኝ አልቻለም፡፡ እንደውም ሊጠራጠረኝ ይሞክራል፡፡ በዚህም የተነሳ ሁለታችንም ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ገብተናል፡፡ ለመሆኑ የብልት ህመምና ማቃጠል ስሜት ከምን መጣ?
ትንሣኤ ነኝ

እንደምን ሰነበታችሁ ውድ ጠያቂዎቻችን ትንሣኤና ገብሩ፡፡ ውድ ጠያቂዎቻችን ችግራችሁን በግልፅ ከእኔ ጋር ለመመካከር ስለወደዳችሁ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በመቀጠል ወደ ጥያቄያችሁ ስንገባ ጉዳዩን በስፋት ከማየታችን በፊት አንድ እውነት መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ እሱም አንዲት ሴት ወሲብ በምትፈፅምበት ወቅትም ሆነ ወሲብ ከፈፀመች በኋላ ምንም አይነት የማቃጠልም ሆነ ሌላ የህመም ስሜት ሊሰማት አይገባም፡፡ አንዲት ሴት በወሲብ ወቅትም ሆነ ከወሲብ በኋላ የማቃተልም ሆነ ሌላ የህመም ስሜት የሚሰማት ከሆነ ግን አንድ ያልታወቀ ችግር እንዳለባት ይጠቁመናል፡፡ እንግዲህ ውድ ጠያቂያችን ትንሣኤ አንቺም ላይ የሚታየው እንዲሁም የገብሩ ፍቅረኛ ላይ በወሲብ ወቅት የሚከሰተው የማቃጠልም ሆነ ሌላ የህመም ስሜት ካልታወቀ ችግር ጋር ሊገናኝ እንደሚችል እንገምታለን፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ህመም ካለምክንያት የሚፈጠር ችግር ሳይሆን ከአንድ የጤና ቀውስ መከሰት በኋላ የሚፈጠር ችግር ነው፡፡

ወሲብ በሚፈፀምበት ወቅትም ሆነ ወሲብ ከተፈፀመ በኋላ የሚፈጠር የመቃጠል እና የህመም ስሜት ብዙ ሴቶችም ላይ ባሆን አንዳንድ ሴቶች ላይ እንደሚከሰት በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በሴቶች ጤና እና ስነ ልቦና ላይ የሚያተኩረው ውመን ሄልዝ (Womens Health Magazine) የተባለው ዓለም አቀፍ መፅሔት እንዳስነበበው ከሆነ በአሜሪካ ሀገር በሴቶች ላይ በስፋት ከሚታዩ የወሲብ ወቅት ችግሮች መካከል ቀዳሚው እና ዋነናው በወሲብ ወቅት እና ከወሲብ በኋላ የሚሰማ የማቃጠል እና የህመም ስሜት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነቱ ችግር በበርካታ ሰዎች ላይ የሚከሰት መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችኋል፡፡ በሴቶች ላይ በወሲብ ወቅት የሚፈጠር የህመም እና የማቃጠል ስሜት እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ እንደ የወሲብ ወቅት ችግር አይታይም ነበር፡፡ ይህንን ችግር ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ አንድ የወሲብ ወቅት ችግር እንዲታወቅ እና መፍትሄ እንዲፈለግለት ያደረጉት በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒዮ ኮርፍማን ናቸው፡፡ እንደ ዶ/ር አንቶኒዮ ኮርፍማን ገለፃ በወሲብ ወቅት እና ወሲብ ከመፈፀም በኋላ የሚፈጠር የማቃጠል እና የህመም ስሜት የሚፈጠረው በበርካታ ምክንያቶች ቢሆንም በብልት የውጪኛው፣ የመካከለኛው እና የውስጠናው ክፍል እንዲሁም በማህፀን ትቦ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች በወሲብ ወቅት ለሚፈጠር የማቃጠል እና የህመም ስሜት ዋነኛ መንስኤዎች እንደሆኑ ይጠቁማሉ፡፡ በተመሳሳይ የተለያዩ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ የጤና ችግሮችም በወሲብ ወቅት የሚፈጠር የማቃጠል እና የህመም ስሜትን እንደሚያስከትሉ በእውቆቹ የስነ ወሲብ ተመራማሪዎች ማስተር እና ጆንሰን በ2001 በተደረገው ጥናት ይጠቁማል፡፡ እስቲ ሴቶች ላይ በወሲብ ወቅት ለሚፈጠር የማቃጠል እና መሰል የህመም ስሜቶች ምክንያት የሚሆኑ ችግሮችን ዘርዘር አድርገን እንመልከታቸው፡፡

– በሰውነት ውስጥ የሚኖር የኢስትሮጂን መጠን ማነስ፡- ውድ ጠያቂዎቻችን ሴቶች ወሲብ በሚፈፅሙበት ወቅት የማቃጠል እና የህመም ስሜት እንዲሰማቸው ከሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች መካከል አንደኛው በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የኢስትሮጂን መጠን መቀነስ በሚታይበት ወቅት ነው፡፡ ሴቶች በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የኢስትሮጂን መጠን ደግሞ የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎችን መውሰድን፣ እርግዝና መከላከያ እንክብሎችን መውሰድን፣ እርግዝና መፈጠርን እና ጡት ማጥባትን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል፡፡ የኢስትሮጂ መጠን መቀነስ በብልት እንዲሁም በሽንት ቱቦ አካባቢ ከፍተኛ ድርቀትን እና እርጥበት አልባነትን ስለሚያስከትል የወንድ ብልት ይህንን ክፍል በሚነካበት ወቅት እና ከነካው በኋላ ሴቶች ህመም እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም የውጪኛው የብልት ክፍል ደረቅ እና እርጥበት አልባ ሆነ ማለት የወንዱ ብልት በሚገባበት ወቅት የመፋተግ እና የመላላጥ አጋጣሚ ሊፈጠርበት ይችላል፡፡

– በሽንት ቱቦ ውስጥ በማይታወቅ ምክንያት የሚፈጠር መሰንጠቅ እና መላጥ፡-

አነስተኛ የሚባለው የፌስቱላ ችግር መኖር፡፡ በተቀራራቢ እርቀት ላይ የሚገኙት የብልት እና የፊንጢጣ ቱቦዎች በተለያዩ ምክንያቶች በተለይ ግን በፊንጢጣ በኩል በሚፈፀም ወሲብ የተነሳ የመበሳት እና አላስፈላጊ ፈሳሾችን ማስተላለፍ ሲጀምሩ በሚፈጠረው የፌስቱላ ችግር ተነሳ በወሲብ ወቅት እና ከወሲብ በኋላ የማቃጠል እና መሰል የህመም ስሜት እንዲሰማን ሊያደርግ ይችላል፡፡

– አለርጂ፡- በወንድም ሆነ በሴቶች ብልት የውጪኛው ክፍል ላይ የሚገኙ ነርቮች እና የደምስሮች እጅግ ስስ እና በአካባቢያችን ከሚገኙ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ጋር ንክኪ በሚኖራቸው ወቅት እንደዚህ አይነት ህመምን የማስከተል አቅም አላቸው፡፡ እንደውም በቅር የተደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት አንዳንድ ሴቶች ለአንዳንድ የኮንዶም አይነቶች እና በወሲብ ወቅት ወሲብን ለማቀላጠፍ ተብለው አገልግሎት ላይ ለሚውሉ ፈሳሽ ጄሎች አላርጂክ እንደሆኑ ያሳያል፡፡
በብልት መግቢያ አካባቢ ያሉ ነርቮች እና ጡንቻዎች በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የመኮማተር እና የመጨበጥ ችግርን በሚያስተናግዱበት ወቅት
– በውጪኛው የብልት ክፍል ላይ የሚኖር ቁስለት ወይንም የሚደርስ መሰል ጉዳት
– በተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች መጠቃት
– እንዲሁም በማህፀን ቱቦ ውስጥ እና በማህፀን ውስጥ የሚፈጠር አጢም መሰል ችግርን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ወሲብን በተመለከተ የሚኖር የተሳሳተ እምነት እና አመለካከት እንዲሁም ወሲብ ከመፈፀም ጋር በተገናኘ የሚኖር መጥፎ ትውስታም ለመሰል ችግር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ውድ ጠያቂዎቻችን ትንሣኤ እና ገብሩ በአንቺ ላይም ሆነ በአንተ ፍቅረኛ ላይ ይህንን ችግር ያስከተለው ከላይ ከተዘረዘሩት የዚህ ችግር መንስኤዎች መካከል የትኛው ነው የሚለውን ለማወቅ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት በባለሞያ የታገዘ ምርመራ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

እንደ ጊዜያዊ መፍትሄነት ወሲብ በምትፈፅሙበት ወቅት በቅድሚያ መራቢያ አካላትን መታጠብ እና ማፅዳት ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ወንዶች የሴት ፍቅረኛቸው በብልት አካባቢ እርጥበታማ እስኪሆን እና በተፈጥሮ ሴቶች ወሲባዊ ግንኙነትን ለማቀላጠፍ የሚረዳውን ፈሳሽ እስከሚያመነጩ ድረስ ብልቱን ወደ ሴቷ ብልት ማስገባት አይኖርበትም፡፡ ሴቶች በተፈጥሮ ወሲብ ለማቀላጠፍ የሚያመነጩት እርጥበት እና ፈሳሽ መመንጨት የሚጀምረው አዕምሮአቸው በበቂ ሁኔታ ለወሲብ ዝግጁ ሲሆንና ወሲብን ሲራብ ነው፡፡ ስለዚህ ወንዶች መጥፎ ስሜት እየተሰማት ያለች ሴት ፍቅረኛውን የማቃጠልም ሆነ ሌላ ህመም እየተሰማት ወሲብ እንድትፈፅም ከማድረግ ይልቅ በቅድሚያ አዕምሮዋን ከመሰል ጭንቀት እና ውጥረት እንዲወጣ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ዘላቂው መፍትሄ ላይ በጣም መተኮር አለበት፡፡ ውድ ጠያቂዎቻችን ለዘላቂ መፍትሄ የሚረዳውን ምርመራ እና ሕክምናስ የት ነው የምናገኘው የሚል ነገር ካነሳችሁ በየትኛውም ሆስፒታል ውስጥ ከሚሰሩ የፅንስ እና የማህፀን ሐኪሞች ጋር ማግኘት እንደሚቻል ልንጠቁማችሁ እንወዳለን፡፡ ውድ ጠያቂያችን ትንሣኤ እና ገብሩ በ2009 በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ስኩል ውስጥ በዶክተር አልበርት ፑሪ አማካይነት የተካሄደው እና በርካታ በዚህ መሰል ችግር ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ ያተኮረው ሌላ ጥናት ደግሞ ይፋ እንዳደረገው በወሲብ ወቅት እና ከወሲብ በኋላ በሴቶች ላይ ለሚፈጠረው የማቃጠል እና መሰል ህመም መንስኤ ከላይ የዘረዘርናቸው ምክንያቶች በተጨማሪ በብልት የውጪኛው ክፍለ ኪልትሮይስ ወይንም በዘልማድ ቂንጥር በሚባለው የብልት ክፍል ላይ ምክንያቱ በማይታወቅ ሁኔታ በሚከሰት ቁስል፣ መላጥ፣ ወይንም መሰል ችግር የተነሳ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዶክተሮችም ሆኑ በህመሙ የተጠቁ ሴቶች ጭምር በወሲብ ወቅት የሚፈጠርን የማቃጠል እና መሰል የህመም ስሜት እንደ ችግር ስለማይቆጥሩት ህክምና ለመፈለግ የሚጠሩበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

በሀገርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ዶ/ር አልበርት ፑሪ መሪነት የተካሄደው የ2009 ጥናት ላይ እንደተቀመተው በወሲብ ወቅት የሚፈጠረው የማቃጠል እና ሌሎች ህመሞች የሚሰሙን በውስጠኛው የብልት ክፍል ይሁን እንጂ ህመሙ የሚመነጨው ግን በብልት የውጪኛው ክፍል ላይ በሚገኘው ቆዳ ላይ በኪልትሮይስ አሊያም በብልት አፍ ላይ በሚደርስ ጉዳት የተነሳ ነው፡፡ እንደ ዶክተር አልበርት ገለፃ ይህ በብልት የውጪኛው ክፍል እና ቂንጥር በምንለው የብልት ክፍል ላይ በሚደርስ ጉዳት የተነሳ የሚፈጠረው ህመም በዋናነት በብልት እና አካባቢው የሚገኙ ነርቮችን በማስቆጣት የመሸብሸብ እና የመኮማተር ባህሪን እንዲይዙ ያደርጋል፡፡

በብልት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች መኮማተር ደግሞ ብልት እርጥበት አልባ እንዲሆን በማድረግ የወንዱ ብልት ወደ ሴቷ በሚገባበት ወቅት ለከፍተኛ ህመም እንድትዳረግ ያደርጋታል፡፡ እንዲህ አይነት ችግር ካለባት ሴት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉ ወንዶችም በብልቷ መድረቅ የተነሳ በሚፈጠርባቸው መላላጥ የተነሳ ከቁስለት እስከ ተለያዩ ችግሮች እስከመጋለጥ የሚደርስ ውስብስብ ችግርን ያስከትልብናል፡፡ እንደዚህ አይነት ችግር ያለባቸው ሴቶች በወሲብ ወቅት የሚሰማቸውን የማቃጠል እና ህመም በተወሰነ መልኩም ቢሆን በብልት አካባቢ እና በእግር መገጣጠሚያ ዙሪያ ያሉ ነርቮች ፈታ እንዲሉ እና እንዳይኮማተሩ የሚረዳ ስፖርት ከወሲብ በፊት መስራት ተመራጭ ነው፡፡

1 COMMENT

  1. ተከተል እበላለሁ በቅርብ ቀን በፈንጥጣዬ አከበብ ከውስጥ ወደ ውጭ ወጣ ከዛም ክንታሮት ነው ተብሎ በበህላው መንገድ ተከምኩ ጥሩ ለውጥም አሰየኝ ቁሱሉ ከደነ ቦኃላ ከዛች ጎን ትንሽ ቀዳዳ ፈጥሮ 5 ቀን 4ቀን ቆይቶ ፈሳሽ ይፈሳል እንዶ ፌስቱላ ልሆን ይችላል ብዬ አስብኩ ምንአልበት ህክምና አላ ወይ ለእንደዝ አይነት ችግር???

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.