ደረቅ ሳልን ለመከላከል በቤት ውስጥ በቀላሉ የምናዘጋጃቸው መድሃኒቶች።

ደረቅ ሳል ጉሮሮዎን ካሰመሞትና በእንቅልፍ ሰዓት የሚያስቸግሮት ከሆነ እነዚህን በቀላሉ የምናዘጋጃቸውን ነገሮች በመጠቀም ማከም እንደምንችል በተለያዩ ጊዜያቶች የተሰሩ ጥናቶች አመላክተዋል።

እነዚህም፦

በጨው መጉመጥመጥ፦ በመጠኑ ለብ ባለ ውሃ ውስጥ አንድ ማንኪያ ጨው በመጨመር ቃና ብለን ጉሮሯችንን እንዲያጸዳ በማድረግ መጉመጥመጥ ደረቅ ሳልን ለመከላከል ወይም በቀላሉ ላስቆም ይችላል ተብሏል።

የሽንኩርት ጭማቂ፦ ሽንኩርቱን ከትፈን የሽንኩርቱን ውሃ በንጹህ ጨርቅ በመጠቀም ቀጨመቅን ብኋላ የሽንኩርቱ ውሃ ላይ አንድ ማንኪያ ማር ጨምሮ በቀን ሁለት ጊዜ እንደ ሽሮፕ መጠቀምም ደረቅ ሳልን ይከላከልልናል ተብሏል።

ፍራፍሬዎችን አዘውትሮ መመገብ፦ ፍራፍሬዎችን በጭማቂ መልክም ይሁን ጥሬያቸውን አዘውትሮ መጠቀም ፍራፍሬዎቹ በውስጣቸው ባለው ንጥረ ነገር አማካኝነት ለደረቅ ሳል እንዳንጋለጥም ይረዱናል።

አረንጓዴ ሻይ፦ አረንጓዴ ሻዩን በሻይ ቅጠሉ ማሸጊያ ጀርባ ላይ ባለው አጠቃቀም መሰረት ካፈላን በኋላ አንድ የሻይ ማንኪያ ማር ጨምሮ መጠጣትም ደረቅ ሳልን ለማከም ፍቱን ነው ተብሏል።

የአረንጓዴ ሻይ እና የማር ጥምረት ደረቅ ሳልን ከማከም ባሻገርም በደረቅ ሳል ወቅት የሚከሰቱ የጉሮሮ ህመሞችንም ለማከም ይረዱናል።

የዝንጅብል ሻይ፦ በፈላ ሻይ /ከተገኘ አረንጓዴ ሻይ / ውስጥ አንድ የሻይ ማንኪያ ዝንጅብል በመጨመር መጠቀምም ለደረቅ ሳል መፍትሄ ነው ሲሉም ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

ምንጭ፦healthdigezt.com

በሙለታ መንገሻ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.