በሙለታ መንገሻ

ደም ግፊት በተለያዩ መንገዶች ሊከሰት የሚችል ሲሆን፥ ለምሳሌም ጨው አብዝቶ መጠቀም፣ አነስተኛ የፕሮቲን መጠን ያላቸው ምግቦችን በመመገብ እንዲሁም በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካለማድረግ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል።

አንዴ በደም ግፊት ከተያዝንም ወደ ነበረበት ለመመለስ ለረጅም ጊዜ መድሃኒት መውሰድ ወይም ከብዙ አይነት ምግቦች ራሳችንን እንድናገል ያደርገናል።

ለዚህ ይረዳ ዘንድም በቻይናዎች ዘንድ ለዘመናት ሲጠቀሙበት የነበረው እና በተመራማሪዎች ተጠንቶ የደም ግፊታችን ሲጨምር በ5 ደቂቃ ውስጥ ወደ ነበረበት ለማውረግ የሚረዳንን መንገድ እናካፍሎ።

በምንጨናነቅበት ወቅት የሰውነታችን ጡንቻ በመቆጣት የደም ቧንቧችን እንዲጠብ በማድረግ ደም እንደልቡ እንዳይዘዋወር ያደርጋል ይህም የደም ግፊታችን መጠን ከፍ እንዲል ስለሚያደርግ ጭንቀትን ማሰወገድ አለብን።

የድም ግፊት ሲያጋጥመን አንገታችንን በሁሉም አቅጣጫ አስር ጊዜ ቀስ እዩልን ወደ ላይ እና ወደታች በማሸት የድም ግፊት መጠንን መቀነስ ይቻላል ተብሏል።

ከአንገታችን ዝቅ ብሎ ያለ ቦታን / collarbone/ የሚባለውን አካባቢ ቢያንስ ለአንድ ደቂቃ ያክል በሁለቱም አቅጣጫ በማሻሸት ወይም በመታሸት የደም ግፊታችንን እንዲወርድ እና ወደ ነበረበት ቦታ እንዲመነለስ ማድረግ እንችላለን።

በሙለታ መንገሻ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.