በሙለታ መንገሻ

ብዙ ሰዎች በጥርስ ህመም ምክንያት ሲሰቃዩ እና እንደፈለጉ ምግብ መመገብ ሲቸገሩ እናስተውላለን።

የጥርስ ህመም ስሜትን ለመቀነስም በተለያየ ጊዜ የወጡ ጥናቶች መፍትሄ ይሆናሉ ያሉትን ዘርዝረዋል።

እነዚህም፦

1. አሲድነት ያላቸውን ምግቦች እና መጠጦች አለመጠቀም

የጥርስ ህመም ያለባቸው ሰዎች በተፈጥሮ አሲድነት ካላቸውን ምግቦች እና መጠጦች ማራቅ እንዳለባቸው ይመከራል።

ምክንያቱ ደግሞ አሲድነት ያላቸው ምግቦች እና መጠጦች የጥርስ ህመም ስሜትን ያባብሳሉ ስለሚባል ነው።

አሲድንት ያላቸውን ምግቦች እና መጠጦች እንደተጠቀምን በ20 ደቂቃ ውስጥ ጥርሳችንን ማጽዳትም ይመከራል።

2. ጥርሳችንን የምንቦርሽበትን መንገድ ማስተካከል

ጥርሳችንን ሀይል በቀላቀሉ መልኩ የምናፀዳ ከሆነ ጥርሳችን ስለሚጎዳ የህመም ስሜት በቀላሉ እንዲሰማን ሊያደርገን ይችላል።

ስለዚህም ጥርሳችንን ስናጸዳ ቀለል አድርገን በስሱና ከላይ ወደ ታች በመቦረሽ የህመም ስሜትን መቀነስ ይቻላል።

3. ጥርስ ማፋጨት

ብዙ ሰዎች ሲናደዱ ወይም ተኝተው በእንቅልፍ ልባቸው ጥርሳቸውን የማፋጨት ባህሪ አለባቸው፤ ይህም ጥርሳችን በቀላሉ ለህመም ስሜት እንዲጋለጥ ያደርገዋል።

በተቻለን አቅም ጥርሳችን ከመንጋጋችን እንዳይጋጠም በማድረግ ጥርስ መፋጨትን በመከላከል የጥርስ ህመም ስሜትን መከላከል ይቻላል።

በተጨማሪም ከፍተኛ የህመም ስሜት የሚሰማን ከሆነ የጥርስ ሀኪምን ማማከር ተገቢ ነው።

ምንጭ፦healthdigezt.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.