የእርድ አስገራሚ የጤና በረከቶች

0

በሙለታ መንገሻ

በብዛት ለምግብ ማጣፈጫ ቅመምነት የምንጠቀመው እርድ በርከት ያሉ የጤና በረከቶች እንዳሉት ተነግሯል።

ስለዚህም እርድን በምግብ ውስጥ ጨምሮ መጠቀም ከምግብ ማጣፈጫነት ባለፈ ለሰውነታችን ጤናም በርከት ያሉ ጥቅሞችን እናገኛለንም ተብሏል።

እርድ ከሚያስገኛቸው የጤና ተቀሜታዎቸ ውስጥም፦

የመርሳት በሽታን ይከላከላል፦ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እርድን መጠቀም አእምሯችን ላይ መዘገየት እንዳይከሰት የሚከላከሉ ጥቃቅን ህዋሶች እንዲያድጉ በማደረግ የመርሳት ወይም አልዛይመር እየተባለ በሚጠራው በሽታ እንዳንጠቃ ይከላከላል።

ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል፦ እርድ በውስጡ ባለው ኩርኩሚን ንጥረ ነገር ለፕሮስቴት ካንሰር የመጋለጥ እንድልን ይቀንሳል።

በተጨማሪም በእርድ ውስጥ የሚገኘው ኩርኩሚን የጡት ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር እና ሉኬሚያን የመከላከል አቅም እንዳለውም ጥናቱ ያመለክታል።

የምግብ መፈጨት፦ እርድን በምግባቸን ውስጥ ቀላቅለን መጠቀም የምግብ መፈጨት ስርዓታችንንም ያሻሸላል ተብሏል።

ጉበታችንን ለማጽዳት ይረዳናል፦ እርደ ውስጥ የሚገኘው ኩርኩሚን ንጥረ ነገር ጉበታችንን ስለሚያጸዳልን እርድን በምግባችን ውሰጥ ማሰገባት ይረዳናል።

የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ በእርድ ውስጥ ያለው ኩርኩሚን ንጥረ ነገር በደማችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር የሰዎችን በስኳር በሽታ የመጋለጥ እድል ይቀንሳል።

ቁስልን ለማከም ይረዳል፦ በሰውነታችን ላይ አነስተኛ የሆነ ቁስል ካለ እርድን በቦታው ላይ በመነስነስ ወይም በመቀባት ቁስሉ ቶሎ እንዲድን ይረዳናል ተብሏል።

የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም ይጨምራል፦ እርድን መጠቀም እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን በከፍተኛ ደረጃ የሚከላከል ሲሆን፥ በተጨማሪም በባክቴሪያ ፈንገስ እና ቫይረሶች የሚመጡ ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል።

ምንጭ፦ healthdigezt.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.