እለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ስንከውን እንውላለን። ነገር ግን በብዛት የምንሰራቸው ስራዎች ላይ ጥነቃቄ ካልታከለበት በጤናችን ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ይታወቃል። በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ ለአደጋ ከሚጋለጡት እና ከፍተኛ ጥንቃቄን ከሚሹ የሰውነት ክፍላችን ውስጥ አንዱ አይናችን ነው።

በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የአይን ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ኪምበርሊይ ኮኬርሃም፥ አሁን አሁን በርካታ ወጣቶች ላይ የአይን ጤና ችግር በብዛት እየተስተዋለ መጥቷል ይላሉ። ይህ ሊሆን የቻለውም በእለት ተእለት እንቅሰቃሴያችን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ስንሰራ ለአይናችን ተገቢውን ጥንቃቄ ስለማናደርግለት ነው ሲሉም ይናገራሉ።

አሁን ላይ በብዛት ለአይን ህመም መንስዔ እየሆኑ ከሚገኙ ነገሮች ውስጥ የስክሪን አጠቃቀማችን ማለትን እንደ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ ቴሌቭዥን እና ታብሌት ስክሪን በዋናነት ይጠቀሳል።

vision-illustrationከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት፣ ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓት፣ ሲጋራ ማጨስ እና ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደትም ለአይን ህመም መንስኤ መሆናቸውን ዶክተር ኪምበርሊይ ይናገራሉ።

አይናችንን የሚጎዱ እና ለመከላከል ማድረግ ያለብን ተግባራት…

  1. የስክሪን አጠቃቀማችን

ከኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን የአይናችን እይታ ላይ ጉዳት ከሚያደርሱት ውስጥ አንዱ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ረጅም ሰዓት እንደ እንደ ላፕቶፕ፣ ስማርት ስልክ፣ ቴሌቪዥን እና ታብሌት ስክሪኖች ላይ በምናሳልፍበት ጊዜ አይናችን በመሃል እየጨፈንን እረፍት የማንሰጠው ከሆነ ለአይን መድረቅ፣ ለአይን ህመም እና የአይናችን እይታ እንዲደክም ያደርጋል።

vision-eyesight-eyes-sore-tired-strain-screens
የስክሪን አጠቃቀማችን

በስክሪን ምክንያት እንዲህ አይነት ችግሮች እንይከሰትብን በአይናችን እና በስክሪን መካከል ያለው ርቀት ቢያንስ 16 ኢንች መሆን አለበት የተባለ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪም በስክሪኑ ላይ የምናየውን የፅሁፍ መጠን ማሳደግ ለአይናችን ጤንነት ይረዳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.