በኔቸር ሜዲስን ላይ ይፋ የተደረገ አዲስ የጥናት ውጤት መጾም የተለመዱ የካንሰር አይነቶችን ለመከላከል እንደሚረዳ አረጋግጧል፡፡

አዲስ የጥናት ውጤት እንዳረጋገጠው መጾም የደም ካንሰርን ይዋጋል ተብሏል
በኔቸር ሜዲስን ላይ ይፋ የተደረገ አዲስ የጥናት ውጤት መጾም የተለመዱ የካንሰር አይነቶችን ለመከላከል እንደሚረዳ አረጋግጧል፡፡ የዩቲ ሳውዝዌስት ህክምና ማእከል ያካሄደው ይህ የጥናት ውጤት ጾም የካንሰር ህዋሳትን እድገት ይከላከላል ሲል ነው የተናገረው፡፡

ጾም በተለይ እንደ የደም ካንሰር ያሉና በወጣትነት የእድሜ ዘመን ላይ የሚከሰቱ የካንሰር አይነቶችን ለመከላከል ፍቱን መድሀኒት ነው ሲሉ ተመራማሪዎቹ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

በአይጦች ላይ ሰፊ ምርምር ያደረጉት አጥኚዎቹ ለደም ካንሰር እንዲጋለጡ የተደረጉ አይጦች የተለያዩ አመጋገብን እንዲከተሉ በማድረግ አስገራሚ ውጤት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ እንዲጾሙ የተደረጉ ወይም ምግብ የተከለከሉ 75 በመቶ የሚደርሱ አይጦች የካንሰር ህመሙ ምልክት ሳይታይባቸው ከ 120 ቀናት በላይ በህይወት መቆየታቸውን የተናገሩት አጥኚዎቹ ሳይስተጓጎል እንዲመገቡ የተደረጉት ግን በ 59 ቀናት ውስጥ ሞተዋል ብለዋል፡፡ በዚህም የተነሳ መጾም ወይም ምግብን ለተወሰነ ጊዜ ገታ ማድረግ እጅግ ትልቅ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

መጾም በውፍረት የተነሳ የሚመጣንና በደም ውስጥ የሚከማችን ሌፕቲን የተባለ የሰውነት ህዋስን መጠን ይቀንሳል ያሉት ሳይንቲስቶቹ ይህ የሰውነት ህዋስ መከማቸት ደግሞ ለካንሰር እጅግ አጋላጭ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ይህን ምርምር በሰዎች ላይ ለመሞከር እየተዘጋጁ መሆኑንም ምሁራኑ ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ምን አይነት የመጾም መንገዶችን መከተል ለዚህ ጤናማ አኗኗር እንደሚረዳ ለማወቅ ተጨማሪ ምርምሮችን ማድረግ እንደሚጠይቅ ነው ምሁራኑ የተናገሩት፡፡

የትኛው የጾም አይነት ጠቃሚ፤ የትኛው ደግሞ ጎጂ እንደሆነ ሳይረዱ ሰዎች ለጤናዬ ይጠቅመናል በሚል ብቻ በመጾም ለምግብ እጥረት ራሳቸውን እንዳያጋልጡና በሽታን የመከላከል አቅማቸውን እንዳያዳክሙ ምሁራኑ አስጠንቅቀዋል፡፡scienceblog

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.