ጤናማ እንቅልፍን ለመተኛት የእንቅልፍ ሳይንቲስቱ ሶስት ነገሮችን ይመክራሉ ቀኑን ሙሉ ስራ ላይ አሳልፈው ማታ አልጋቸው ላይ አረፍ ለማለት ቢሞክሩም እንቅልፍ በቀላሉ የማይወስዳቸው ሰዎች ቁጥር ትንሽ አለመሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ችግሩ መፍትሄ ያለው መሆኑን የሚገልጹት በአሜሪካ የእንቅልፍ አካዳሚ የእንቅልፍ ሳይንቲስት ራጅ ዳስጉብታ 3 ባህሪያትን መላበስ ለጤናማ እንቅልፍ መፍትሄ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

  1. አልጋን የእንቅልፍ ቦታ ብቻ ማድረግ

በስራ ቦታ ያልተጠናቀቁ ስራዎችን አልጋ ላይ ወጥተው የሚጨርሱ ከሆነ፣ አልጋዎ ላይ በስልኮም ሆነ በላፕቶፖ የተላከሎትን ኢማይል የሚያዩ ከሆነ ተግባሩን በአፋጣኝ ሊያቆሙ ይጋባል ይላሉ የእንቅልፍ ሳይንቲስቱ ራጅ ዳስጉብታ፡፡ አልጋ ላይ ሆነው የሚሰሩ ስራዎች የጤማ እንቅልፍ ጸር ናቸው፡፡ ሰዎች እንቅልፍ አልወስድ ሲላቸው ስልኮቻቸውን የሚጎረጉሩት አሊያም ወደ ሌላ ስራ የሚሸጋገሩት አልጋ ላይ የስራ ቦታ የማድረጋቸው ተጽዕኖ መሆኑን ሳይንቲስቱ ያስረዳሉ፡፡

2. ለእንቅልፍ እራስን ማዘጋጀት

እንቅልፍ ከመተኛታችን 1 ሰዓት በፊት አይምሮን ሊያነቃቁ ከሚችሉ ቴሌቪዥንን ከመመልከት፣ ማህበራዊ ድረ ገጾችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ወደ አልጋ ከመሄድ በፊት አይምሮን ዘና ሊያደርጉ ከሚችሉ ንባብን የመሳሰሉ ተግባራት ማዘውተርን የዘርፉ ሳይንቲስት ይመክራሉ፡፡

3. እንቅልፍ አልወስዶት ካለ ቦታ መቀየር

እንቅልፍ አልወስዶት ካለ አልጋ ላይ መገላበጥ መፍትሄ አይደለም ይላሉ ባለሙያው፡፡ ከዚያ ይልቅ ከአልጋዎ ላይ ተነስተው ለተወሰኑ ጊዚያት መራመድ አሊያም ማንበብ ጠቃሚ ነው፡፡ በግድ ለመተኛት መሞከር አይምሮ ጠንክሮ እንዲሰራ ስለሚያስገድድ ትርፉ ድካም መሆኑን የአሜሪካው የእንቅልፍ አካዳሚ ሳይንቲስት ራጅ ዳስጉብታ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፤ ዘ ኢንዲፔንደንት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here