ጤና – አዘውትረን ባለማድረጋችን ለጭንቀት ሊያጋልጡን የሚችሉ ተግባሮች ምንድናቸው?

ማንኛውም ጭንቀት ያጋጠመው ሰው ጭንቀት ምን ያህል ጉዳት እንዳለው ይረዳል፡፡

ብዙዎቻችንም በቀን ተቀን ውሎዋችን ሊያጋጥመን የሚችልም ተግባር ነው፡፡

የሰውን የሀይል መጠን ከመቀነሱም ባሻገር ሰራችን ላይም ያለው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው፡፡

ታዲያ ጭኝቀትን ሊያመጡ የሚችሉ እና አለማረግ የሌለብን ተግባሮች ምንድናቸው፡፡?

እንቅስቃሴን አለማድረግ ቀላል ችግር ሊመስል ይችላል እንጂ እንቅስቃሴን አለማድረግ በአእምሮ እና ሰውነት ጤንነት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ነው ያለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰውነትን ለተጨማሪ ጭንቀት ሊዳርግ ይችላል በተጨማሪም ሰውነታችን ጭንቀት ውስጥ ሲሆን አእምሮአችን እንቅስቃሴን ከማድረግ ይልቅ ተቀምጦ መደበትን ይመርጣል ይህ ደግሞ ለበለጠ ጭንቀት ይዳርጋል፡፡ ስለዚህም በቀን ውስጥ የተወሰነ እንቅስቃሴን ማድርግ ስውነታችንን ከጭንቀት ሊያላቅቅ እንደሚችል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ያልተመጣጠነ አመጋገብ ጤነኛ የሆነ አመጋገብ ለሰውነታችንን ብቻ ሳይሆን ለአእምሮአችንን ጠቀሜታ እንዳለው ይነግራል፡፡

ኦሜጋ 3 የተባለውን ንጥረ ነገር የያዙ ምግቦችን መመገብ ለአእምሮ ጤንነት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ነው ሳይንቲስቶች የሚናገሩት፡፡

ሰውነታችን እነኚህን ንጥረ ነገሮች በራሱ ማግኘት ስላማይችል እንኚህን ንጥረ ነገሮች ማግኘት የሚችለው ከምግብ ነው፡፡

ስለዚህም የተመጣጠኑ እና ጤነኛ የሆኑ ምግቦችን መመገብ እእምሮአችንን ጤነኛ ከማድረጉ ባለፈ ከጭንቀትም ውጭ ያደርጋል፡፡ በቂ እንቅልፍ አለማግኘት

እራሶትን በተደጋጋሚ ከእንቅልፍ ማራቅ አእምሮትን ለጭንቀት ያዳርጋል ይላሉ ጥናቶች፡፡

የህክምና ኤክስፐርቶች እንደሚሉት የሰው ልጅ በቀን ውስጥ እስከ ስምንት ሰአት የሚደርስ የእንቅልፍ ሰአት ያስፈልገዋል፡፡

እንደ ማንብብ፣እንደ ላፕቶፕ ያሉ የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን በአልጋ ላይ መጠቀም ለእንቅልፍ ማጣት ዋነኛ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ እነሱን በእንቅልፍ ሰአቶት መራቅ ማስወገድ፡፡

ራስዎትን ከማህበራዊ ህይወት ማራቅ ራስዎትን ከጓደኛና ከዘመድ አዝማድ ማራቅ ለጭንቀት ተጋላጭኖትንን ይጨምራል፡፡

ስለዚህም ራስዎትን ከማህበረሰቡ ጋር ማቀላቀል እና ከዘመድ አዝማድ ጋር ማቀራረብ ጭንቀትን እንደሚቀንስ ይነገራል፡፡

አሉታዊ ነገሮችን ማሰብ አሉታዊ አስተሳሰብ የጭንቀት ዋነኛ መከሰቻ ምክንያት ነው፡፡

ስለ ውድቀት ፣መገለልና እና የነገሮች ጥሩ አለመሆን ደጋግመው ባሰቡ ቁጥር አእምሮትን ለጭንቀት እየዳረጉ ነው፡፡

አንዳንዴ በህይወት ሊከሰቱ የሚችሉ መጥፎ አጋጣሚዎች ቢኖሩም እነሱን እያሰብን ራሳችንነ በአሉታዊ ነገሮች በሞላን ቁጥር ራሳችንን ለጭንቀት እያጋለጥን ስለሆነ ከዚህ ልምድ ራሳችንን ማራቅ ይኖርብናል፡፡

ስለዚህም ራሳችንን ከተጠቀሱት ልማዶች በማራቅ አእምሮአችንን ከጭንቀት ማላቀቅ እንችላለን፡፡

ምንጭ፡ ሄልዝ ዳይጄስት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.