ቴሌቪዥን ለረጅም ስአት መመልከት የሚያስከትላቸውን የጤና እክሎች ጥናቶች በተደጋጋሚ ጠቁመዋል።

እጅግ የበዛ የቴሌቪዥን መመልከት ፍቅር የተለያዩ ጉዳቶችን የሚከተሉትን ጉዳቶች እንደሚያስከትሉ ይጠቅሳሉ።

ዝቅ ካለ መቀመጫ ላይ በመሆን ከፍ ካለ ቦታ ላይ የተቀመጠ ቴሌቪዥንን መመልከት በስኳር ህመም መጠቃትን ከማሳደጉም ባሻገር በህይዎት የመቆየት እድልን እንደሚያሳጥር ጥናቶች አረጋግጠዋል። በቅርቡ በፒትስበርግ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት በየአንድ ስአቱ ቴሌቪዥን ላይ የምናሳልፈው ጊዜ በስኳር በሽታ የመጠቃት እድላችን በ3 ነጥብ 4 በመቶ ያሳድጋል ብሏል። በ2011 በብሪታንያ የስፖርት ህክምና ጆርናል (British Journal of Sports Medicine) ላይ የወጣው የጥናት ውጤትም ይህንኑ የሚደግፍ ነው።

በ11 ሺህ ተሳታፊዎች በተደረገው በዚህ ጥናት ላይ ተሳታፊዎቹ ቴሌቪዥን በመመልከት የሚያሳልፉት አንድ ስአት ከእድሜያቸው ላይ 22 ደቂቃ እንዲቀንሱ አድርጓል ተብሏል።የሀርቫርድ የማህበራዊ ጤና ትምህርት ቤት ያካሄደው ጥናትም በየቀኑ 2 ስአት እና ከዚያ በላይ ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ሰዎች ከአጥንት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ተጋላጭ እንደሚያደርግና እድሜን እንደሚያሳጥር ተረጋግጧል።

ቴሌቪዥን አብዝቶ መመልከት በወጣቶች ብቻ አይደለም ጉዳት የሚያስከትለው፤ በአዛውንቶችና በህጻናት ላይም እንጂ። በየቀኑ ከ2 ስአት በላይ ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ህጻናት በከፍተኛ ደም ግፊት የመጠቃት እድላቸው በ30 በመቶ እንደሚያድግ ነው ባለፈው አመት የወጣ አንድ ጥናት ደረስኩበት ያለው። ሌላው ጉዳት ደግሞ የሰውነት ክብደት መጨመር ነው።

ለረጅም ስአት ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ሰዎች ክብደታቸው ለወጥ ባያሳይም እንዳይዘናጉ፤ ለልብ ህመም ሊዳረጉ ይችላሉና ነው ያሉት ያሆ ኒዋስ ያነጋገራቸው የጤና ባለሙያዎች የሚገልጹት። በአለማችን ለሚከሰቱ የልብ ህመሞች ለበርካታ ስአት በመቀመጥ 12 ነጥብ 2 በመቶውን ድርሻ ይወስዳልም ነው የተባለው። ከላይ የዘረዘርናቸው ነጥቦች ምንም እንኳን የሚያስደነግጡ አይነት ቢሆኑም፥ ሰዎች ቴሌቪዥን መመልከት እንዲያቆሙ የሚያስገድዱ አይደሉም። ቴሌቪዥን መመልከት በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት። ይሁን እንጂ እያወቅንም ሆነ ሳናውቅ ለረጅም ስአት ቴሌቪዥን የምንመለከት ከሆነ ጥንቃቄ ብናደርግ ተገቢ ነው በሚል እኛም መረጃውን አጋራናችሁ።

ምንጭ፦ https://www.yahoo.com/health

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በፋሲካው ታደሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.