በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን አዘውትረን የምናዳምጥ ከሆነ በርከት ያሉ የጤና ጠቀሜታዎችን እንደሚያስገኝልን የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቀዎችን ስናነሳ እንደምሳሌም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ሞዛርተ ያሉት ሲጠቀሱ፥ በሀገራችንም የኢትዮ ጃዝ መስራች ክቡር ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄን መጥቀስ እንችላለን።

ታዲያ እነዚህን በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎች ከመዝናኛነትም ባለፈ በእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን እና ጤናችን ላይ ከፍተኛ ፋይዳ አላቸው ተብሏል።

በመሳሪያ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን በማዳመጥ ከምናገኛቸው ጥቅሞች መካከልም፦

አእምሯችንን ንቁ እንዲሆን እንዲሁም የማስታወስ ችሎታው እንዲጨምር ያደርጋል ፦ በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃን ማዳመጥ አእምሯችን በሚሰራው ስራ ላይ ንቁ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን፥ በተጨማሪም የአእምሯችንን የማስታወስ ችሎታም ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።

ይህንን ለማረጋገጥን በኖርዝ አምቢራ ዩኒቨርሲቲ በተደረገ ጥናት በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃን የሚያዳምጡ የሰዎች ከማያዳምጡት በእጅጉን በተሻለ ፍጥነት፣ ቅልጥፍና እና ያለ ስህተት ስራቸውን ሲያከናውኑ ተገኝተዋል።

የተስተካከለ እንቅልፍ እንዲኖረን ያደርገናል፦በመሳሪያ የተቀነባበሩ ለስለስ ያሉ ሙዚቃዎችን ከመኝታ ሰዓት በፊት አዘውትረን የምናዳምጥ ከሆነ በቃላሉ እንቅልፍ እንዲወስደን ይረዳናል ተብሏል።

በተለይም እንደ ፒያኖ እና ጊታር እንዲሁም የሀገራችንን በገና አይነት መሳሪያዎች የተቀነባበሩ ሙዚቃዎች ማዳመጥ የተስተካከለ እና ሰላማዊ እንቅልፍ እንድንተኛ ያደርጋል ተብሏል።

የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖረን ያደርጋል፦ እንደ የደም ግፊት አይነት ችግር ያለብን ከሆነ በመሳሪያ የተቀነባበሩ ለስለስ ያሉ ሙዚቃዎችን አዘውትረን ማዳመጥ የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖረን ያደርጋል።

በእንግሊዝ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠውም በመሳሪያ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን የሚያዳምጡ ሰዎች ካማያዳምጡት በተሻለ የተስተካከለ የድም ዝውውር አላቸው።

የህመም ስሜትን ያስወግዳል፦ እንደ ድብርት ያሉ እና ከስሜት ህዋሳችን ጋር የሚያያዝ የህመም ስሜት የሚሰማን ከሆነ በመሳሪያ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን በመስማት የህመሙን ስሜት ያስወግድልናልም ሲሉ ተመራማሪዎቺ ተናግረዋል።

ሀቀኛ እንድንሆን ይረዳናል፦ በመሳሪያ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን እያዳመጥን የሚሰማንን ነገር በምንናገርበት ወቅት ሀቀኝነታችን እንዲጨምር ያደርጋል።
በኖርዝ አምቢራ የኑቨርሲቲ በተደረገ ጥናት እንደተረጋገጠው ሰዎች በሚናገሩበት ወይም የህይወት ተሞክሯቸውን በሚያካፍሉበት ወቅት ከጀርባቸው በመሳሪያ የተቀነባበረ

ሙዚቃ እያዳመጡ ከሆነ ሁሉንም ነገር ተረጋግተው እንዲናገሩ በማድረግ ሀቀኛ እንዲሆኑ ያደርጋል።

በተጨማሪም በመሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ ሙዚቃዎችን አዘውትረን በማዳመጥ እራሳችንን ደስተኛ፣ የመረጋጋት ስሜት እንዲሰማን እንዲሁም ጤነኛ መሆን እንችላለን።

ምንጭ፦ stethnews.com

በሙለታ መንገሻ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.