(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)
✔ የኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል
አቮካዶ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር (betasisterol) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘዉን የኮሌስትሮል መጠን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔ ለዓይናችን ጤና ጠቃሚ ነው
በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲየን (carotenoid lutien) ዓይናችንን ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚመጡ ሕመሞችን እንድንከላከል ይረዳል፡፡
✔ በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል
በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው (folate) ፎሌት በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን እንደሚቀንስ የተደረጉ ጥናቶቸድ ያሳያሉ፡፡
✔ ከካንሰር ይከላከላል
አቮካዶ የሚመገቡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስና ወንዶችን ደግሞ ከፕሮስቴት ካንሰር የመከላከል የመከላከል አቅም እንዳለው የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
✔ መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል
አቮካዶ ተፈጥሮአዊ ከሆኑ የመጥፎ አፍ ጠረን መከላከያዎች አንዱ ነው፡፡
✔ ለቆዳችን ጥቅም
የኦቮካዶ ቅባት በብዙ የውበት መጠበቂያዎች ውስጥ የሚገባና ለቆዳ ተስማሚ እና ጤናማነት ጠቃሚነት ያለው የፍራፍሬ ዓይነት ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.