የብዙ ተላላፊ በሽታ ያልሆኑ ( non- communicable diseases ) የጤና ጠንቆች መንስሄና ለአንዳንድ በሽታዎች መባባስ ዋንኛ ምክንያት የሆነው የሰውነት ውስጥ ብግነት( inflammation ) ሲሆን ምንጬም  በቀላሉ ወደ ጉሉኮስ( ሰውነታችን የሚጠቀመው የስኳር አይነት ) የሚለወጡ ምግቦች አብዝቶ መመገብ ነው:: ጠንቁም በሽታ ሆኖ

በላብራቶሪ ከመታየቱም በፊት በሰውነታችን ውስጥ ብዙ ጉዳቶች ማስከተል ነው::

  1. የሰውነት ብግነት ( inflammation) :- የስኳር መጠን መዛባት:: ምልክቶቹም :-

1.1 የኮልስትሮል መጠን መጨመር ( መጥፎው የኮልስትሮል አይነት LDL እና ሲከፋ ደግሞ ትራግላሴራይድ Triglycerides መጨመር ;በዛው መጠን ጥሩው የኮልስትሮል አይነት መቀነስ HDL )

1.2 ቦርጭ ማውጣት

1.3 ኢንሱሊን ( በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን የሚቆጣጠር ሆርሞን) ሆርሞን መሉለሙሉ መስራት ማቆም ( insulin resistance) ወይንም በስኳር ህመም መጠቃት

1.4 ያለመጠን መወፈር

1.5  በልብ በሽታ መጠቃት

2. የቆዳ ብግነት ( skin inflammation)

2.1 የቆዳ ያለጊዜው ማርጀት

2.2 የቆዳ መሸብሸብ

2.3 በተፈጥሮ ወዛም የሆነ ፊት በftግር ና በቆዳ ቀዳዳዋች መደፈን ( white and black heads) መባባስ

3. ሰውነት የበሽታ የመከላከል መጠን መቀነስ( ለተለያዪ ኢንፌክሽኖች መጋለጥ)

  1. የአፍ ጠረን ና የጥርስ መበስበስ
  2. ስኳር የምግባቸው ምንጫቸው በሆኑት የበሽታ አምጪ ህዋሳቶች ( ፈንገስ: ባክቴሪያ) ስንጠቃ የምናገኘውን ህክምና አሽንፈው በሰውነታችን እንዲባዙና ደጋግመው እንዲያጠቁን መንገድ መፍጠር; ለምሳሌ በተደጋጋሚ በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ; በሴት ልጅ የብልት ኢንፌክሽን በመሳሰሉት መጠቃት ::

መፍትሄዎች

  1. የደም የስኳር መጠን በቀላሉ ከፍ የሚያደርጉ ምግቦች ና መጠጦች በብዛት ወይንም ለብቻው አብዝቶ አለመመገብ / አለመጠጣት

1.1 ከስንዴ ዘር የሚዘጋጁ ምግቦች :-

ሙዝ ;ፓስታ ; መኮሮኒ: ፒዛ :ሩዝ: ነጭ ዳቦ…..

1.2 የስኳር መጠናቸው ከፍ ያለ አትክልትናፍራፍሬዎች:-ቀይስር  :አተር :ድንች

:ካሮት : ሙዝ : ብርቱካን : ፔር: አፕል: ፖፖያ

1.3 ለቁርስ ተብለው የሚዘጋጁ: የታሸጉ የጥራጥሬ ምግቦች ( cereales ) : ጣፋጭ የማርማታ ምግቦች : ከፍራፍሬ የሚሰሩ ጃም ( fruit

Jam) .

 

1.4 መጠጦች : አልኮል : የለስላሳ መጠጦች

ከላይ የተጠቀሱት የምግቦች ዓይነቶች ሲመገft ገንቢና ሀይል ሰጪ ምግቦች ( protients and fats ) እና አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች አብሮ ማብሰል ወይም መመገብ

ለምሳሌ ገንቢ የሆኑት  ( ስብ የሌለው ስጋ : እንቁላል: የባቄላ ዘሮች( ሽሮ) : ዓሳ … )

ጤነኛ ሀይል ሰጪ ምግቦች( fats) የሆኑት : አቮካዶ : የእቾሎኒ ዘሮች : የተነጠረ ቂቤ : ኮኮናት ዘይት: የወይራ ዘይት (

ኦሊቭ) : የወይራ ፍሬ የመሳስሉትን አብሮ መመገብ::

  1. ከጣፋጭ ምግቦች መገገብ መወሰን/ ማቆም: ኬክ: ኩኪስ
  2. አዘውትረው የሰውነት ገንቢ ስፖርቶች በመስራት የደሞን የስኳር መጠን መቆጣጠር

4 . የበሽታ ምልክት እስከሚመጣ ከመጠበቅ ቢያንስ በአመት አንዴ የደም ምርመራ በማድረግ የስኳርና አጠቃላይ የኮልስትሮን መጠን በመለካት የሰውነቶ የስኳር አጠቃቀም ሁኔታ በመረዳት ቅድሚያ የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ ከበሽታ መከላከል ::

 

ሰብለ አለሙ !! አኩፖንቸሪስትና ኸርባሊስት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.