ክፍል 1አጠቃላይ የመከላከያ ዘዴዎች( General preventive measures for bladder infections):-

እንዳለባቸው ማስተማር ::

1.የምግብ መፍጫ ናየብልት ማይክሮባዮም ( gut and vaginal microbiome /ጥሩ ባክቴሪያዎች)መከባከብ :- አለመጠን ስኳር የበዛበት ምግብ ከመመገብ በመቆጠብ ጎጂ ባክቴሪያዎች እንዳይራft መንገድ አለመክፈት::

  1. ለሴት ልጅ የሚሰጥ ምክር :- ከተፀዳዳሽ በኃላ ከፊት ወደኃላ መጥረግ : ይህም በሰገራ ውስጥ የሚገኙ ጎጂ ባክቴሪያዎች ወደ ፊንኛ እንዳይገft ይከላከላል ::

**ወላጆች ልጆቻቹን ከልጅነት ጀምሮ እንዴት መፀዳዳት
3.ሽንት ከመቋጠር መቆጠብ ( **ወላጆች : ልጆቻቸውን በት/ ቤት ቆይታቸው ሽንት አንዳይቋጥሩ መምከር ::)
4.ስራና ህይወት በማመጣጠን ውጥረትን ( stress) በማስወገድ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከያ አቅምን ማዳበር::
5.በቂ ውሃ በየእለት መጠጣት
6.ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ ቶሎ መሽናት

ክፍል ሁለት :የምግብ ምርጫዎች ምን ይመስላል ?

ፈርመንትድ ምግቦች (fermented foods):-ጠቃሚ ባክቴሪያዎች በምግብ ውስጥ እንዲራft በማድረግ ለምሳሌ እርጎናአትክልቶች በፈርመንት ሂደት በማዘጋጀት በቤት ውስጥ መመገብ (በውጪ ለሚኖሩ ነዎሪዎች : በባክቴሪያ ከልቸርድ የሆኑ ኦርጋኒክ እርጎና አትክልት ምግቦች ከምግብ ግሮሰሪ ገስቶ መመገብ ይቻላል ::)

 

ክፍል ሶስት: ፊንኛ ኢንፌክሽን ቢጠቁ በተደጋጋሚ እንዳይጠቁ ምን ያድርጉ ?

ምንም እንኳን በሰለጠነው ሀለም( በተለይ በአሜሪካ) ብዙ በተፈጥሮ  የማከሚያ  ምርጫዎች ስለሚገኝ ከአላስፈላጊ ፀረ- ህይወት መዳኒት ከመውሰድ መራቅ ቢቻልም ይህ ምርጫ በሌለበት አጋጣሚዎች ፀረ- ህይወት መዳኒት(

ማለትም broad spectrum anti- biotics) መውሰድ ግድ ሲሆን ጎን ለጎን የጠፉትን ባክቴሪያዎች የሚመልሱ ( ክፍል 2)ምግቦች በመመገብና በተጨማሪም ህይወት መላሽ ሰፕልመንት ( pro- biotics supplement:* በዚህ ዙሪያ በቂ ዕውቀት ያለው ባለሙያ በማማከር ገዝቶ መውሰድ ) በመውሰድ በተደጋጋሚ በፊንኛ ኢንፌክሽን ከመጠቃት መከላከል ይቻላል ::

ጤና ይሁኑ!!

ሰብለ አለሙ :: አኩንፖቸሪስትና ኸርባሊስት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.