የስኳር በሽታ ሰውነት ኢንሱሊን የተባለውን ቅመም ሳይሠራ ሲቀር ነው። ኢንሱሊን በሰውነት የሚገኝ ቅመም (ሆርሞን) የምንበላው ምግብ ኃይል እንዲሆነንና ኣካላታችን ጉልበት ኣግኝቶ እንዲሠራ የሚያደርግ ነው። የስኳር በሽታ በደም ውስጥ ያሚገኘውን ስኳር ከሚገባው መጠን እጅግ ከፍ እንዲል ካደረገው፥ ልብ፣ ኣንጐል፣ ኩላሊት፣ የደም-ስሮች፣ ጥርሶች
ሊጎዱ ይችላሉ። የስኳር በሽታ የዓይን መታወርን፣ የግብረ-ስጋን ተግባር መዳከምንና፣ እስከ ሞትም ሊያደርስ የሚችል ነው።
ዋናዎቹ የስኳር በሽታ ዓይነቶች፦
1-ኛ ዓይነት – በልጆችና በጉብሎች የሚገኘው ነው። ድሮ “የልጆች ዓይነቱ” ስኳር በሽታ ተብሎ ይታወቅ ነበር።
2-ኛ ዓይነት – ይህ በብዙ ሰው የሚገኘው ዓይነቱ የስኳር በሽታ ሲሆን፣ “የኣዋቂዎች ስኳር በሽታ” ተብሎ ይጠራ ነበር። ዛሬ ግን በልጆችም ኣዘውትሮ ይታያል፣ ምክንያቱም የዛሬ ልጆች እጅግ ውፍረት፣ የሚዛን ክብደትና ኣለመንቀሳቀ ስን ስለሚያበዙነው። የእርግዝና ስኳር የሚባለው ም በሽታ በኣንዳንድ እርጉዞች ላይ ይገኛል።
የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ኢንሱሊን የተባለውን ኬሚካል ሰውነታቸው በአግባቡ ማምረት ወይም መጠቀም አይችልም፡፡ ኢንሱሊን ማለት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝና ሰውነታችን የሚፈልገው የኬሚካል ዓይነት ነው:: ኢንሱሊን የሚጠቅመው ስኳርና ሌሎች ምግቦችን ወደ ግሉኮስ ለመቀየር ነው፡፡ ግሉኮስ ለሰውነታችን  ኃይል  በመስጠት ሰውነታችንን የሚያንቀሳቅስ ነው፡፡ በስኳር በሽታ ተጠ ቂ  ከሆኑት ውስጥ 1/3ኛ  የሚያህሉት በሽታው እንዳለባቸውው አያውቁም፡፡ በደንብ ካልተከታ ተሉትና እንክብካቤ ካላደረጉለት የስኳር በሽታ ዓይነ ስውርነት፣ የልብ በሽታ፣ በቀላሉ የማይድኑ ቁስሎችንና የመሳሰሉትን በሽታዎች ያስከትላል፡፡ ስኳር ያለባቸው ሰዎች የሚመገቡትን ምግብ በመቆጣጠር፣ የስኳር መጠ ናቸውን በየጊዜው በማወቅ፣ ክኒን/እንክብል በመውሰድና ኢንሱሊን በመውሰድ እራሳቸውን ይንከባከባሉ፡፡ ስኳር ካለብዎት እራስዎን መጠበቅ አለብዎት፡፡ ስኳርዎን በአግባቡ ከተቆጣጠሩ ጤናማ ሆነው ረጅም ሕይወት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
ለስኳር በሽታ የተጋለጡ እነማን ናቸው?
ሐኪሞች “ዓይነት 1″ ከምን እንደሚነሳና ወይም እንዴት እንደሚመጣ ስለማያውቁ ለዚህ ዓይነቱ የስኳር በሽታ የሚጋለጡት እነማን እንደሆኑ መገመት አይቻልም፡፡ ወላጆች የዚህ ዓይነቶቹን የስኳር በሽታ ምልክቶች በጥንቃቄ ማወቅ አለባቸው፤ ልጆቻቸውን  በፍጥነት ወደ ሐኪም መውሰድ እንዲችሉ፡፡
በ”ዓይነት 2”  የስኳር በሽታ በቀላሉ ሊያዙ የሚችሉት፡-ዕድሚያቸው 55 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ፤ ስኳር ያለበት የቅርብ ዘመድ (ወላጅ፣ ወንድም ወይም እህት) ያላቸው፤ ወፍራም ሆነው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማይሠሩ፤ ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ወይም ኮሌስትሮል ያለባቸው
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሕፃናትና ወጣቶች “ዓይነት 2” የስኳር በሽታ ተጠቂ ሆነዋል።  ይህም የሆነበት ምክንያት ብዙ ስብ እና ስኳር ስለሚመገቡ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ/ስፖርት ስለማይሠሩ ነው።  በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች ጤናማ የሆነ አኗኗር የስኳር በሽታን ለመከላከል ጠቃሚ ነው።
የስኳር በሽታ ምልክቶች
“ዓይነት 1″ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሕፃናት የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ፡
– በቀላሉ የማያልፍ የውሃ ጥም
– ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት
– ድካም
-ከፍተኛ የሆነ ውፍረት ወይም ክሳት
– ማስመለስ
በአብዛኛው የ”ዓይነት 1” ተጠቂዎች ስኳር እንዳለባቸው የሚታወቀው ከታመሙ በኋላ ስለሆነ ምልክቱን ዓይተው ወደ ሐኪም መውሰድ የወላጆች ሃላፊነት ነው፡፡
የ “ዓይነት 2” የስኳር በሽታ ምልክቶች፦
– የማይጠፋ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ጥም
– ቶሎ ቶሎ ሽንት መሽናት
– ድካም
– ማስመለስ
– የዓይን መፍዘዝ/በጥራት አለማየት
– የቀላል ቁስሎች ቶሎ አለመዳን
እነዚህ ምልክቶች በእርስዎ ወይም በሚወዱት ሰው ላይ ካዩ ሀኪም ያማክሩ፡፡ ስኳር በሽታ ሊታከም ይችላል፣ ነገር ግን ምልክቶቹን ከናቁ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ሊያስከትልብዎ ይችላል፡፡
ከምንም በላይ የስኳር በሽታ ህሙማን የዶክተርን ክትትል ይሻሉ። በምግብም በሽታውን ከተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.