የሳይቴክ ቤተሰቦች… በመልዕክት መቀበያችን በደረስን ጥያቄ መሰረት ዛሬ ስለጨጓራ ህመም መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል፡፡ በቅድሚያ ሼር አድርጉት፡፡

► መንስኤዎች

የጨጓራ ሕመም የሚከሰተው በጨጓራችን ግድግዳ ላይ ቁስለት በሚያስከትሉ ምክንያቶች ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

 ለጨጓራ ተስማሚ ያልሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ
 የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
 ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መውሰድ
 ቅመም የበዛባቸው ምግቦች መመገብ
 ጭንቀት
 ሲጋራ ማጤስ
 መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ሆድ ማስገባት

► የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ከሰውስው የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው ግን እነዚህን ያካትታሉ፡፡

 የማቅለሽለሽ ስሜት
 የሆድ መንፋት ስሜት
 ማስመለስ
 የምግብ አለመፈጨት
 የማቃጠል ስሜት በተለይ ከምግብ በኋላ
 የምግብ ፍላጎት መቀነስ
 የሠገራ ቀለም መለወጥ ወይም መጥቆር ናቸው

ከባድ የሆነ የጨጓራ ሕመም ያላቸው ሰዎች የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ሊከሰትባቸው ስለሚችል በተጨማሪ እነዚህ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላሉ፡፡

 የማላብ ስሜት
 የልብ ምት መጨመር
 የትንፋሽ ማጠር
 ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜት
 ደም ማስመለስ
 ደም የቀላቀለና ከወትሮው የተለየ መጥፎ ሽታ ያለው ሠገራ መኖር ናቸው፡፡

እነዚህ ዓይነት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ተገቢ የሆነውን ምርመራና ሕክምና ማግኘት ይኖርበታል፡፡

የሕክምናው ሁኔታ የጨጓራ ሕመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት ሊለያይ ቢችልም ያሉትን ምልክቶች በማስወገድ ለሕመምተኛው ፋታ መስጠትና ሕምሙን ያስከተላውን ሁኔታ በምርመራዎች አረጋግጦ መፍትሔ መስጠት ተገቢ ነው፡፡

የጨጓራ ሕመምን ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በማስወገድ ሕምሙ እንዳይቀሰቀስብን ማድረግ ይቻላል፡፡

► ውድ የሳይቴክ ወዳጆች፣ በመልዕክት መቀበያችን የምትልኩልንን ጥያቄዎች ችላ ብለናቸው አናውቅም፡፡ መልስ የነፈግናችሁ እየመሰላችሁ አንዳንዶቻችሁ በብስጭት ሀይለቃል እስከመናገርም የደረሳችሁ አላችሁ፡፡ ነገር ግን አንድም ቀን ችላ ለማለት አንፈልግም፡፡ ሁሉንም ጥያቄ በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ከባድ እንደሆነ ግን እንድትረዱን እንፈልጋለን፡፡ ጊዜው ይቆይ እንጂ አቅማችን የፈቀደውን ከማድረግ አንቦዝንም፡፡ ወደፊት አብረውን ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎችን በማካተት ለጥያቄዎቻችሁ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ ባለሙያ በመልዕክት መቀበያችን ሊያነጋግረን ይችላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይሄንን መልዕክት ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን፡፡

……

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.