ሁልዳ ሮጀር ክላርክ

ትርጉም- መኳንንት ታደሰ         

 

deseaseከጥንት ዘመን ጀምሮ መድኃኒት አዋቂዎች የበሽተኞችን ገንዘብ ሆነ ንብረት ለመዝረፍ ጥበባቸውን እንደ መያዣ ሲገለገሉበት ኖረዋል። የዛሬ ሐኪሞችም ሆኑ የጥንት መድኃኒት አዋቂዎች ጥበባቸውን ሚስጥር በማድረግ ጤና የሚሻውን በሽተኛ በእየ አጋጣሚው ሲመዘብሩት ይታያሉ። በተለይ በዚህ ዘመን የሚገኙ የሕክምና ጠበብቶች (ሐኪሞች፣ መድኃኒት አቅራቢዎች ወይንም ቀማሚዎች ሆኑ አደራ ጠባቂዎቻቸው) ከሠራተኛው ሕዝብ ላይ የሚዘርፉት ገንዘብ ቁጥር ሥፍር የለውም። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ወደ ሌላ ሥራ ቢሠማሩ መልካም አይመስላችሁም?ብዙሃኑ የሚሠራውን እንደ ግብርና ቢሠሩ? ብዙሃኑ የጤና ረሃብተኛ ደግሞ የእነርሱን ሥራ ቢሠራ? ሁሉም ቢቀላቀሉ?።

እዚህ መፅሐፍ ውስጥ ታላቅ ቦታ የሚሰጠው እና ዋስትና ያለው ግኝት በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራው ጥገኛ ነፍሳትን፣ተዋሃሲያንን እና ቫይረስን  የሚደመስሰው መሣሪያ ጥራት ነው።

ይህንን ታላቅ የምሥራች ዜና በመስማትዎ የሆስፒታል ቀጠሮዎን ሊሰርዙ አይገባዎትም። ጥገኛ ነፍሳትን ከሰውነት ውስጥ ማጥፋት ማለት ወዲያው መፈወስ ማለት አይደለም። መፈወስ ጊዜን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። እዚህ ላይ በእርግጠኝነት ልገልጽልዎ የምፈልገው ነገር ቢኖር ለሁለተኛ ጊዜ ለምርመራ ሲሄዱ ግን ሐኪሞ በመደነቅ የመድኃኒት ተዕዛዙን ይቀንሳል ወይንም ጨርሶ አያዝሎትም።

የዚህ መሣሪያ ግኝት ሕጋዊ የባለቤትነት ዕውቅና ጊዜ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ አይደለም ይሉ ይሆናል። የብዙዎችም ምክር ይሄው ነበር። የእኔ ሐሣብ ግን ወዲህ ነው። የመሣሪያውን ሕጋዊ የባለቤትነት ዕውቅና አልፈለግኩትም። ምክንያቱም እርስዎም ልጆቾም የልጅ ልጆቾም በነፃ እንድትጠቀሙት ተውኩት። እርስዎ ጤናማ ከሆኑ ቤተሰብዎም ሌላውም ይፈወሳል። እንደዚህ ከሆነ ደግሞ በእዚህ በመድኃኒት ጋጋታ እና በበሽታ ከተቆራኘ ጨለማ ዓለም እንላቀቃለን። የበሽታንም ጠንቅ እና አመጣጡን ከአወቅን ከጥገኛ ነፍሳት ሁሉ ነፃ  የሆነች ዓለምን መፍጠር እንችላለን።

የስኳር በሽታ የለም፤ የደም ግፊት የለም፤ ካንሰር የለም፤ ኃይለኛ እራስ ምታት የለም፤ ኤች አይ ቪ(ኤድስ) የለም፤ ሉፑስ የለም

በዚህ በአዲሱ ግኝት አልንበረከክም ብሎ እፊቶ ላይ የሚቆም እኔ ነኝ ባይ በሽታ ፈፅሞ ሊገኝ አይችልም።

ቃል ኪዳን

                          ከአዲሱ ዓለም ጋር ይቆራኙ ከደዌ ነፃ ነውና

                           አሮጌውን ዓለም ይሰናበቱ እስረኛ አርጎታልና

አዲስ ነገር ይሞክሩ

እሥር ቤቱ ግርግዳ አልባ ነው። ነገር ግን በግርግዳ ምትክ ዙሪያዎን የከበቦት የተሠመረ መሥመር አለ። እዚያ የተሠመረው መሥመር ውስጥ አሮጌው አስትሳሰብዎ ይገኛል። ደግሞ ከመሥመሩ ውጪ አዲሱ አስተሳሰብዎ ይገኛል። ይህ አዲሱ አስተሳሰብዎ እመር ብለው ከመስመሩ እንዲያልፉ እና ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዞታል። ይደፈሩ እና ይወስኑ። ይህንን ከአደረጉ በጥቂት ሣምንታት ውስጥ ከበሽታዎ ይፈወሳሉ።

አንድ ሰው በመጥፎ በሽታ ከተለከፈ እራሱን መጥላቱ ወይንም አንዳንድ ጥያቄዎችን መጠየቁ አይቀርም። እኔ ከሌላው ሰው በምን ተለይቼ ነው? ምን ስሆን አገኘኝ? ምን ባደርግ ነው ከዚህ ጉድ የምውጣው? ለመሆኑ ይህን በሽታ የሚያድን መድኃኒት ይኖር ይሆን? የመሣሰሉትን።

ለብዙዎቻችን የሐኪሞች ቋንቋ ተስፋ አስቆራጭ ነው። ስለ እኛም ሆነ ስለ ልጆቻችን የሚሰጡን መግለጫ እና ማስጠንቀቂያ። ለምሳሌ አንድ ሐኪም ልጅዎት በኮክሳኪ ቫይረስ ተለክፏል እንዲሁም ወደጭንቅላቱ ዘልቆ በመለብለብ እያሰቃየው ነው ቢልዎት ይህ በሽታ ከሰነበተበት እና በደንብ የሚከታተለው ጥሩ ሐኪም ቤት ካላገኙ ሕመሙ እና ትኩሳቱ ልጅዎ ላይ የሚስከትለውን ዘላቂ ችግር ጠንቅቀው  ያውቃሉ እንበል። ምን ያደርጋሉ? ሐኪሞችን ከመማፅን ፤ የዘመድ ያልህ ከማለት፤ ከመጸለይ፣ ከመሣል፣ ከማልቀስ በስተቀር ምን የሚያደርጉት ነገር አለ።

ግን የተገላቢጦሽ ሆኖ ካለምንም ጉዳት ልጅዎት ላይ ያለውን ቫይረስ በ3ደቂቃ ውስጥ አጥፍተው እስከ ወዲያኛው ቫይረሱ እንዳይደርስበት አድርገው ቢያድኑት ምን ይሰማዎታል።

እንግድህ እዚህ መጽሐፍ ውስጥ  ይህንን ዘዴ ይማራሉ። የማጥፋት ዘዴውን ብቻ ሳይሆን እንዴት ልጆች በተለያየ ጥገኛ ነፍሳት እንደሚለክፉ እና መፍትሄውን ጭመር።

እንግዲህ  ተራ በተራ  እራስን ማስተማር መልካም ስለሆነ በመጀመሪያ እዚህ ዓለም ላይ የሚገኝ ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ የየግሉ የሆነ የሬድዮ ማሰራጫ ጣቢያ ዓይነት ነገር ስለአለው ይህንን ለይቶ ማወቅ። ሁለተኛ ትክክለኛውን የጣቢያ ሞገድ  እርግብግብ ማግኘት። ሦስተኛ ይህንን የሞገድ እርግብግብ መግታት። ይህንን የሞገድ እርግብግብ ለመግታት ደቂቃ በቂ ነው።

በመጨረሻም የእራስዎ የሆነውን ይህንን የመመርመርያ መሣሪያ እንዲሠሩ አበረታታዎታለሁ። ግልጽ እና ቀላል የሆነው የአሠራር ዘዴው እዚህ መጽሐፍ ውስጥ አለሎት። ከመንግሥታትም የእገዳ ሕግ ነፃ ስለሆነ የሚያስጋዎት ነገር የለም።

ሁለቱ የጤና ጠንቆች

በሰዎች ሁሉ ላይ የሚታዩ የሕመም ምልክቶች ከኃይለኛ ራስ ምታት እስከ መካንነት ብሎም እስከ አዕምሮ መሣት በጠቅላላው አነጋገር ከትንሹ እስከ ትልቁ ምንም የተለያየ እና የተዘበራረቀ ቢሆንም እርግጠኛ ነኝ መነሥኤው ሁለት ነገር ብቻ ነው። ይኸውም ጥገኛ ነፍሳት እና ብክለት ነው። ስፖርተኛ ባለመሆን ወይንም የሰውነት እንቅስቃሴ እጥረትም አይደለም። የባይታሚን እጥረትም አይደለም ወይንም የሆርሞን መቃወስም አይደለም።

መንሥኤ                                         መፍትሔ

ጥገኛ ነፍሳት                        የጥገኛ ነፍሳት መደምሰሻ ወይንም የባህል መድኃኒት

ብክለት                             እራስን ማግለል እና የውስጥ አካልን(ሆድዕቃን)ማጽዳት

ይህ የጎበዝ ፍልሚያ ነው። ጤንነትን በእጅ ለማድረግ የሚደረግ ትንቅንቅ። በአንድ እጅ ብሩህ ተስፋን በሌላው ቆራጥነትን ጨብጦ መጋፈጥ። በዚህ መጽሐፍ ላይ የበሽታ ታሪካቸው እንደ ተመዘገበላችው በሽተኞች እርስዎም ተአምር መሥራት ይችላሉ። የሚያስደስተው ይህንን ጥበብ ሁሉ ለማወቅም ሆነ እራስዎን ከደዌ ለመፈወስ እጅግ በጣም ብዙ ገንዘብ አለመጠየቁ ነው።

 

የጤና ቃኝ ይሁኑ

እራስዎን  ከደዌ ከፈወሱ በኋላ የሚቀጥለው ሥራዎ ቤተሰብዎን ጓደኞችዎን ጎረቤቶችዎን መፈወስ ነው። ቤተሰብ በደም የተያያዘ ስለሆነ ችግሩም ማለት በሽታውም እንዲሁ የተያያዘ እና ተመሳሳይ ነው። ይህ ደግሞ ግቦትን ያፋጥነዋል። ሁሉንም ነገር በማስታወሻ የማሥፈር ልምድ ይኑርዎ። ቢቻል ፎቶግራፍ። ከቤተሰብ የተላለፈን የስኳር በሽታን ከአባትዎ፣ ከአክስትዎ፣ ከወንድምዎ፣ ከእርስዎው ከእራስዎ በዚህ በተማሩት ጥበብ ተጠቅመው ቢፈውሱ በእውንት ይህ መልካም የቤተስብ ታሪክ አይደለም?ለቀሪው ትውልድስ መመዝገብ የለበትም?።

ብዙ በሽታ በዘር አይተላለፍም። ግን ይተላለፋሉ ተብለው የሚገመቱት እንደ ጡንቻ በሽታ የዓይን መለብለብ እና የመታወር በሽታ በቤተሰብ ቢኖርብዎ እና ይህንን በሽታ ከቤተሰብዎ ቢያጠፉ የቤተሰብዎን ተስፋ እንዳለመለሙ እና ዘሮን ጤናማ እንዳደረጉ ይወቁ ። በእውነት እላችኋለሁ ጥንት አባቶቻችን ንፁሕ ነበሩ አሁን ይህ የምናየው ችግር ሁሉ የመጣብን ከጥገኛ ነፍሳት እና የተበከለ ነገር ወደ ሰውነታችን ከማስገባት  ነው።

ወራሪ ጥገኛ ነፍሳት ከሰውነታችን ውስጥ ማስወገድ ቀዳሚ ተግባር ነው። ሆኖም ወሳኙ መንሥኤውን እና  ምንጩን ማወቅ ነው። ከየት መጡ? እንዴት አገኙኝ? ለምን ለይተው እኔን አጠቁኝ? መልስ ማግኘት የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው።

ብክለት የሚያስክትልብዎት የጤና ቀውስ እዚህ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት ስለሚገለጽ በጥንቃቄ ማስተዋል ይኖርብዎታል።  ከእነዚህ በዓይን ከማይታዩ አጥቂዎችዎ ጋር እንዴት ቆራጦቹ የሰውነትዎ የመከላከያ ኃይሎች እና የደም ሴሎችዎ በእየ ጥጋ ጥጉ እየተዋደቁ እንዳሉ ቁልጭ አድርጎ ያሳይዎታል።

ይህንን ፍልሚያችውን በዓይነ ሕሊናዎት ሲቃኙ ደግሞ ዳግም የተበከለ ነገር ወደ ሰውነትዎ ላለማስገባት ይወስናሉ።እንደ ኮባልት፣ አስቤስቶስ፣ ፈሬኦን፣ ሜርኩሪ፣ ሊድ ሌሎችንም።

በተለይ ደግሞ ይህንን የሰውነት የተፈጥሮ ጥበባቸውን  ቢደግፉላችው በድል አድራጊነት ስለሚወጡ በሕይወትዎ የሚያስደስት የምሥራች ያበስርዎታል። ለምሳሌ፦

-ከይስት የሚመጣ አደገኛ ሕመም ይጠፋል

-ፀጉርዎ መነቀል ያቆማል እንደውም አዲስ ይተካል

-የእርግዝና ችግር ይቀረፋል

-የድካም፣የመዛል፣ የመታከት ስሜት ይጠፋል

– የእንቅልፍ እጦት አይኖርም

-ቆዳ ላይ የሚወጣ ነገር ሁሉ ይረግፋል

-የማየት ሆነ የመስማት ችሎታዎ ይታደሳል

-ሌሎችም

ጤንነት ከበሽታ መገላገል ብቻም አይደለም። ጤንነት ደስታ ነው። ጤነንት እንደሚያስቅ ተረት ፈገግ ፈገግ የሚያሰኝ ነገር ነው። ጤንነት የመኖር ዋስትና ነው። ጤንነት የሰማይ ከዋክብትን የምድር አዝርዕትን እያዩ የመደሰት ያህል ነው። ጤንነት በልጅነት ወራት እንዴት እንደቦረቁ አሁንም ቢሆን ያ እርስዎነትዎ በውስጥዎ እንዳለ የሚያዩበት ልዩ መነፅር ነው።

 

ግኝት

ከአካላችን በደም ምርመራ እንኳን ሊገኙ የማይችሉ ነገሮችን መርምሮ ማግኘት የዘውትር ሐሳቤ ነበር።  ይህንን እቅዴን ዕውን የሚያደርግልኝስ መሣሪያ የቱ ነው? ለምንድነው በኤሌትሪክ ኃይል መጠቀም ከመድኃኒት በተሻለ የሚፈውሰው?በኤሌክትሪክ ኃይል ጥጋኛ ነፍሳትን የሚደመስሰው መሣሪያዪስ ፅንሰ ሐሳቡ ምንድነው?

በ1988 የሰውነት ብልትን የሚመረምር የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ፈለሰፍኩኝ። የሕክምና ጠበብቶች ሲኤቲ እና ኤም አር አይ በሚባሉ በኮምፒውተር በሚሠሩ የረቀቁ መሣሪያዎች የሰውነትን ብልት እንደሚመረምሩ የታወቀ ነው። እነዚህ ውድ መሣሪያዎች ብልትን ለይቶ ከማሣየት በስተቀር ዝርዝር ሁኔታን አይጠቁሙም። የእኔ መሣሪያ ግን ብልቱ ውስጥ ያሉትን ጥገኛ ነፍሳት፣ ባይረስ፣ተዋሃሲያን፣ፋንገስ፣ ኬሚካል፣ ሶልበንት፣ ቶክስንን በዝርዝር ከመጠቆምም ባሻገር በዋጋም ደረጃ ቢሆን እጅግ በጣም ርካሽ ነው። አሠራሩም የሬድዮ ኤሌክትሮኒክስን ፈለግ የተከተለ ነው።

በዚህ መሣሪያ በውስጠኛው ሰርኪዩት በኢንዳክታንሱ(ኤሌክትሪክ የማመንጫ ወይንም የማስተላለፊያ ዘዴ)እና በካፓሲታንሱ(ካፓሲተር ኤሌክትሪክን አምቆ የመያዝ እና የመልቀቅ ፀባይ)አሠራር የሚነዝረውን እርግብግብ እና ከሌላ ከማንኛውም ነገር የሚላከውን እርግብግብ በጥሞና ቢያስተያዩ ሁለቱ ተመሳሳይነት አላችው። ይህ ባህሪያችው ሰርኪዩቱ እንዲወዛወዝ ያደርጉታል። ይህም ሁኔታ በድምፅ ማውጫው በኩል ጫጫታ መሰል ነገር ያሰማል።

እኔ የመሣሪያውን የውስጥ ሰርኪዩት ለመሥራት የኦዲዮ ኦሲሌተር ነው የተጠቀሙኩት። ሰውነታችን በተፈጥሮው የራሱ የሆነ እርግብግብ አለው። ጥገኛ ነፍሳት እንደዚሁ የእየ እራሳችው እርግብግብ አላችው። እንግዲህ ይህንን ከኦዲዮ ኦሲሌተር  የሚወጣውን እርግብግብ እና ከሰውነታችን የሚወጣውን እርግብግብ ብናዋህደው የሆነ ንዝረት እናገኛለን ። ተመሳሳይ ነገር አገኘን ማለት ነው። እንደዚሁም በዚህ መሣሪያ ላይ በተዘጋጀ የመመርመሪያ ፕሌት ላይ የአንዱን ጥገኝ ነፍሳት ስላይድ ብናስቀምጥ እና የዚሁ ጥገኝ ነፍሳት ተመሳሳይ እውስጣችን ቢኖር እርግብግባቸው ተመሳሳይ ስለሆነ መሣሪያው ያጫድራል።

ይህ ከመሣሪያው የሚወጣው ድምፅ የቱ የማን እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ ጊዜን እና ትዕግሥትን ይጠይቃል። በእርግጥ ለሬድዮ ሠራተኞች እና ለሙዚቀኞች ቀላል ሊሆን ይችላል።

ይህንን መሣሪያ ለመሥራትም ሆነ አጠቃቀሙን ለማወቅ የሙያው ባለቤት መሆን አያስፈልጎትም። ማንም ተራ ሰው ትዕግሥቱ ካለው ይሠራዋል። የመሣሪያውን የአሠራር ዝርዝር ክፍል 3 ላይ ያገኙታል።

በዚህ ዓመት ይህንን መሣሪያ በጭፍኑ መጠቀም ጀመርኩ። ሰውነቴ ላይ ማንኛውንም ነገር በማስቀመጥ በደቂቃዎች ለይቼ ማወቅን ተላመድኩ። ከምላሴም ላይ እንዲሁ አንድን ነገር ሳላየው እቀምስ እና በዚሁ መሣሪያ መርምሬ አገኘው ጀመርኩ። መሣሪያው ሰውነት እና ምላስ ላይ በትክክል እንደሚሠራ አረጋገጥኩ። ይህ መሣሪያ የውስጥ ብልትንስ እንዲሁ ለይቶ ያውቅ ይሁን?ሌላስ ነገር በውስጤ? የጆሮ፣ የዓይን፣ የጨጓራ … ወዘተ ችግሮችንስ?

እነዚህ እና ሌሎችም ተጓዳኝ ጥያቄዎች በአዕምሮዬ ውስጥ ይመላላሱ ጀመር። በመሆኑም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ አለብኝ የሚል ቁርጥ ውሳኔ አደረግኩ። ለዚህ ሥራ ከፍተኛ እርግብግብ ያለው ኃይል ያስፈልጋል። የዚህ ዓይነት አስደናቂ ሥራ የሚሠራው መሣሪያ ደርማትሮን ነው። እሱም ቢሆን የሚያመነጨው ዲሲ ነው። በእርግጥ መሣሪያዬ ውስጥ የሬድዮ እርግብግብ መኖር አለ። ኦዲዮ ኦሲሌተሯ ውስጥ ያለው 1000ህርዝ (በሰከንድ የመርገብገብ መጠን) ብቻ ነው። ይህ የሬድዮ እርግብግብ ግን ከመቶዎቹ እና ሺዎቹ ህርዞች የሚበልጥ ነው መሆን ያለበት። ይህ ኃይል ከየት ይመጣል ከሰውነቴ ይመነጭ ይሁን? ይገርማል። ተጠራጠርኩ ስለሆነም ይህንን ለማረጋግጥ ሙከራዎቼን ተያያዝኩኝ።

ቀኑን ሙሉ የተለያዩ ሙከራዎችን በዝቺው መሣሪያዬ በመጠቀም ሳከናውን ዋልኩ። የተለያዩ ካፓሲተሮችን እና እርግብግብ ማገጃዎችን በመጨመር እና በመቀነስ ሞከርኩ። ግን ምንም ፍንጭ አልተገኘም። በመጨረሻም ከፍተኛ እርግብግብ የሚያመነጭ መሣሪያ ከእኔዋ ጋር አያያዝኩና ተጨማሪ እርግብግብ አገኘሁ። ከ1000 ህርዝ ጀመርኩ 10,000; 100,000; 1,000,000 ህርዝ ድረስ ዘለቅኩ ። ምንም የለም። ተስፋ ገን አልቆረጥኩም። አመሻሹ ላይ የመሣሪያውን እርግብግብ 1,800,000 ህርዝ ከፍ አደርግኩ እና ሞከርኩ። ይህኛው ሠራ በሰውነቴ ውስጥ አቻውን እርግብግብ ስለ አገኘ ድምፅ ማውጫው አጫደረ። አላመንኩም ደግሜ ደጋግሜ ሳዳምጥ አመሸሁ። በዚሁ ምሽት የሰው ሰውነት ዝቅተኛው እርግብግብ 1562,000 ህርዝ መሆኑን አረጋገጥኩ። መሣሪያው ግን ጣራው 2,000,000 ህርዝ ብቻ ስለሆነ ከእዛ በላይ ልሞክር አልቻልኩም። ከአመታት በኋላ ግን የተሻለውን ገዝቼ የሰው ሰውነት እርግብግብ ጣራ እስከ 9,457,000 ህርዝ እንደሚዘልቅ አረጋገጥኩ።

በእርግጥ የሰው ሰውነት ኤሌክትሪክን እንደ ሬድዮ ጣቢያ እንደሚያስተላልፍ ሳይታለም የተፈታ ሐቅ ነው። ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ድረስ ሚስጥሩ ያልታወቀው፣ ያልተመረመረው እና ያልተለካው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ቮልት እና እጅግ በጣም ብዙ  እርግብግብ እና ሞገድ ማስተላለፊያ መስመር ስለአለው ነው።

ሁሉም ነገር የእራሱ የሆነ ልዩ ሞገድ አለው

ዘመኑ 1989 ነው። ሩጫ የበዛበት ዓመት ነው። ሕይወት ያላችው ነገሮች ሞገድ ማስተላለፈያ መስመራቸውን ለይቶ በማወቅ ሥራ ስለተጠመድኩ ሥራ በዝቶብኛል። እጅግ በጣም አድካሚ ሥራ ቢሆንም ቅሉ ውጤቱም እንደዛው ያማረ ነው። የዝንብን፣ የጢንዚዛን፣ የሸረሪትን፣ የቁንጫን እና የጉንዳንን ሞገድ ማስተላለፊያ መስመር አግኝቼአለሁ። 1,000,000 ህርዝ እስከ 1,500,000 ህርዝ ነው። ከመረመርኳቸው ነፍሳት ሁሉ የበረሮ ሞገድ ከፍተኛ ነው። የሚገርመው የሞተ ነገር ሁሉ ሞገድ አለው። በሕይወት ዘመኑ እያለ የሚታይበትን ዝቅተኛውን ሞገድ በውስጡ ይዞ ይቆያል።ይህ ከሆነ ደግሞ ከሞተ ነገር ሁሉ ለምርምር የሚውሉ ስላይዶችን ማዘጋጀት ይቻላል ማለት ነው።

ቀጣዩ ተዕልኮዬ በአዝዕርት እና ሥጋ ውስጥ የሚገኙ ጥገኛ ነፍሳትን ማደን ነበር። በዚህም በኩል የተሳካ ውጤት አገኘሁ። የመጀመሪያ ስላይዴም የፍሉክ(ጉበትን እና ሌሎችንም ብልቶች የሚያጠቃ አደገኛ ጥገኝ ነፍሳት)ነበረ። እርግብግቡም 434,000 ህርዝ ነው። የእርሱ እጪ ደግሞ እርግብግቡ 432,000 ህርዝ ነው። ይህ ጥገና ነፍሳት በሁሉም የካንሰር በሽተኞች ላይ ይታያል።

ይህን የምርምር ሥራዬን እያከናወንኩ እያለሁ አንድ ሐሳብ ጭንቅላቴ ውስር ብልጭ አለ። ይህውም አንድ ፍሉክ በሰውነቱ ውስጥ ያለበት ስው ይህንን የእርግብግብ ማመንጫ መሣሪያ 434,000 ህርዝ ላይ እያለ ቢጨብጠው ምን ይሆናል?።

ይህንን መሞከር አልብኝ ብዬ ወሰንኩ። ለነገሩ እኔ ፍሉክ የለብኝም። በጉበት በሽታም አልሰቃይም። ሆኖም በሳልሞነላ(ከተበከለ ምግብ የሚመጣ በሽታ)በጂያርዲያ(የአንጀት ጥገኛ ነፍሳት)እና በህርፒስ(ሰውነት ላይ የሚወጣ ውኃ የሚቋጥር በሽታ)እሰቃይ ነበር። ለ3ት ደቂቃ ብቻ ነበር ላሉብኝ ጥገኛ ነፍሳት የሚመጥን እርግብግብ ሰውነቴ ውስጥ ያስተላለፍኩት ተመልሼ በመመርመሪያ መሣሪያዬ ስመረምር ሰውነቴ ውስጥ ቀደም ሲል የነበረው የእርግብግብ ምልክታቸው ጠፍቷል። ደግሜ ደጋግሜ ብመረምር ላገኘው አልቻልኩም። ድንገት ተዝለፍልፈው ወይንም ተደብቀው ይሆናል ብዬ ነበር ግን ከህርፒሱ ይመጣ የነበረ የመቆጥቆጥ ሆነ ሌላም የነበረብኝ የሕመም ስሜት እየጠፋ ሄደ። የሚገርም እና ለማመንም የሚቸግር ነገር ነው። ይሁን እንጂ የሚታመን እና የሆነም ነገር ነው።

ይህ ነገር ችግር ያመጣ ይሆን እንዴ? ብዬ ስልሰጋሁ ማረጋገጥ ፈለግኩ። በጥቂት ሣምንታት ውስጥ ትክክለኛ መልሱን አገኘሁ። በዚህ 3ት ደቂቃ ውስጥ ወደ ሰውነት የሚገባው የኤሌትሪክ መጠን 5 ቦልት እና የተወሰነለት እርግብግብ ስለሆነ ጉዳት የለውም።

ተስማሚ የኤሌትሪክ መጠን መምረጥ

ስድስት የተለያዪ ዓይነት እርግብግቦችን ብንጠቀም እና ጥገኝ ነፍሳቶችን ከሰውነታችን ብናጠፋ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ቤተሰቡን ሁሉ ከደዌ መፈወስ እንችላለን። በተለይ በሁሉም ካንሰር በሽተኞች ላይ የሚታየው ፖስፓ ታይሮሲን ከሰውነት ውስጥ ድራሹ ይጠፋል። የኤች አይ ቪ ቫይረሶች በሚገርም ሁኔታ ከሰውነታችን ውስጥ በደቂቃዎች ዕድሜ ይጠፋሉ። ዳግም የደም ምርመራ ቢደረግ አይታዩም። ትክክለኛው ጥገኛ ነፍሳት ታውቆ የሚመጥነው እርግብግብ ከተሰጠው ብዙ ዓይነት በሽታዎች እና ስሜታችው ወዲያው ይጠፋል። ይህ የሚያመለክተው ሁሉም የእየ እራሱ እርግብግብ እንዳለው ነው።

በዓይን ከማይታዩት ጥገኝ ነፍሳት ተዋሃሲያን እና ቫይረስ እስከ ትላልቆቹ ጥገኛ ነፍሳት ወስፋት እና ፍሉክን እንደምንገድለው ሁሉ በዓይን የሚታዩትን እንደ የመሬት ትል ወይንም ቁንጫን መግደል እንችላለን ወይ?

ይህንን ምርምር ከላይ በተጠቀሱት ሁለቱ ላይ አድርጌ ነበር። የሞገዳቸውን ከፍተኛውን እርግብግብ በመምረጥ ለ10 ደቂቃ አስተላለፍኩ። ወዲያው እራሳቸውን ሣቱ ግን አልሞቱም። ቆይቼ ስመረምራችው የመሬት ትል በጣም ብዙ እርግብግብ ከከፍተኛውም ከዝቅተኛውም ሞገድ አጥቷል ቁንጫ ግን ብዙም አላጣም። ሁለቱም ቢሆኑ ይህንን የተፈጥሮ ይዘታችውን ከሣምንታት በኋላ እንኳን ሊተኩት አልቻሉም። ውለው አድረው ሟቾች ናቸው።

የሰው ልጅስ በእራሱ እርግብግብ አቻ ቢጠቃ ይጎዳ ይሆን? የሚል ጥያቄ ታነሱ ይሆናል። በእርግጥ ይጎዳል። ቮልቱ ከፍተኛ ከሆነ የማይጎዳበት ምክንያት የለም። ይህ ግን አልተሞከረም አስፈላጊም አይደለም። ምክንያቱም ማጥፋት የምንሻው ጥገኛ ነፍሳትን ነው። የእነርሱ እርግብግብ ደግሞ ከሰው ልጅ በግምት ከአሥር እስከ አሥራ ሰባት እጅ ዝቅተኛ ነው። ለማገናዘብ በገፅ 18 ላይ ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ።

ይኸው እንግዲህ በአሌሌክትሪክ ኃይል በሽታን የሚያጠቃው መሣሪያዬ ተወለደ። ማድረግ ያለብን የሞቱ ጥገኛ ነፍሳትን ወይንም ስላይዳቸውን ማግኘት። የተፈጥሮ እርግብግባችውን ማወቅ። ለሰውነት ያንን የእርግብግብ መጠን መስጠት። በደቂቃዎች ዕድሜ ጥገኛ ነፍሳቱ ይሞታሉ። ወይንም ይታመማሉ። ይህንን እኛ ከአደርግን ቀሪውን ነጭ የደም ሴላችን ይወጣዋል።

የሚያሰጋኝ ነገር ነበር ይኸውም ይህንን ጥበብ በመጠቀም እጅግ በጣም ከፍተኛ ቮልት የሚያመነጭ መሣሪያ በመፍጠር የአንዳንድ አገር መከላከያ ክፍል ጣላትን ለመደምሰሻ ይጠቀም ይሆናል የሚል ነው። አሠራሩም ከፍተኛ የኤሌትሪክ ኃይልን እንደ መብረቅ በመጠቀም ከርቀት ማጥቃት ነው። ይሁን እንጂ ገና ለገና ይህ እንዳይፈጠር በመስጋት የሰው ልጅ በበሽታ ሲማቅቅ ማየቱን አልፈለግኩም። ከሆነም ደግሞ የሰውን ልጅ ከእዚህ ጥፋት የሚታደግ መከላከያ አይጠፋም።

ስለዚህ አሁን በተገኘው መሣሪያ አጥቂዎቻችንን መልሰን በማጥቃት ከአደገኛ በሽታ ለመከላከል በተጠንቀቅ መቆም አለብን። በአለፉት አሥር እና ሃያ ዓመታት እነዚህ ጥገኛ ነፍሳት እጅግ በጣም ያየሉበት ምክንያት የሰውም ሆነ የእንሰሳት በሽታን የመከላከል አቅም በመዳከሙ ነው። ለዚህም ተጠያቂው የዓለማችን መበከል ነው።

 

አስታውሱ እውነተኛ ፍልሚያ ጥገኛ ነፍሳትን ማጥፋት ብቻ አይደለም

                                           ነገር ግን

                 ጤንነታችንን እና የሰውነት የመከላከያ ኃይላችንን መልሶ መተካት ነው

 

ጥገኛ ነፍሳት እንደሚያጠቃን ሁሉ ብክለትም በበለጠ ያጠቃናል። ጥገኛ ነፍሳትን በማጥፋት ከደዌ እንደምንገላገለው ሁሉ ለአካባቢ መበከልም ትኩረት መስጠት አለብን። እንዴት ነው ይህንን ልንወጣው የምንችለው? ብዙዎቻችንን የተጠናወተ ትልቅ ችግር አለ። ይህውም በፋብሪካ ከተዘጋጀ ምግብ፣ መጠጥ፣ ቅባት፣ ማጠቢያ፣ መታጠቢያ… ወዘተ ጋር የተቆራኘ የአኗኗር ዘይቤ። ይህን ጭፍን የአኗኗር ዘይቤ እርግፍ አድርገን መተው እና ተራ የአኗኗር ዘይቤ መከተል አለብን። ራልፍ ዋልዶ ኢመርሰን በመጽሐፉ እንደጠቀሰው ያልተካበደ አኗኗር ማለትም እንደማንኛውም ተራ ሰው መኖር መቻል ታላቅነት ነው ይላል። ይህንን መንገድ ሁላችንም መከተል ከቻልን ዓለማችንን ከመመረዝ እናድናታለን።

ባዮራዲዬሽን

እንግዳ ነገር መስሎ ቢታይም ሐቁ ግን ይህ ነው። ፀሐይም መሬትም በመሬት ላይ ያለ ነገርም ሁሉ የራሱ የሆነ የሬድዮ ጣቢያ ዓይነት ነገር አለው። ይህንን እኔ ባዮራዲዬሽን ብዬ ሰይሜዋለሁ።  ይህ ሚስጥሩ ረቂቅ የሆነ ነገር ምን ይሆን? ከምንስ ጋር ሊቆራኝ ይችላል?

ምናልባት ከሜሪዲያን ፍልስፍና ጋር?(የቻይናውያን የሕክምና ጥበብ)ወይንስ ከሳይኪኮች ጥበብ ጋር?ወይንስ ከኃይማኖት አባቶች የመፈወስ ኃይል ጋር?

እጅጉን የሚገርመው እና የሚደንቀው ነገር ደግሞ ስንት ጠቢባን ሳይንቲስቶች እያሉ እነዚህ እና ከእዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች በተራ ሰዎች እጅ መገለጣቸው ነው። ለምሳሌ ያህል ብንወስድ ኪኒሲዬሎጂ(የአካል እንቅስቃሴ ጥናት)፣ ፔንድለም(ትንሽ የመመርመሪያ ቱንቢ)፣ ራዲዮኒክስ(የፔንድለም አጠቃቀም ዘዴ) እና ሌሎችም። ይህ ታላቅ ተሰጥዖ ከተራው ሕዝብ መገኘቱ የሳይንስን አካሄድ ስልሚቃወም በዚህ አቅጣጫ ሳይንስን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። እርግጠኛ ነኝ እነዚህ እና ሌሎችም ብዙ የሚያስደንቁ ነገሮች ሁሉ ከባዮራዲዬሽን ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላችው።

ከብዙ ዘመን በፊት የአውሮፓ ሳይንቲስቶች ኢላን ቪታልን(የህይወት ኃይል)በመቃወም ኅሳቡን ውድቅ አድርገውት ነበር። ወጣት ሳይንቲስቶች እኔንም ጨምሮ ይህንን ጉዳይ ማብላላት አንዳንዴ ማዋደቅ በሌላ ጊዜ ደግሞ በታቃራኒው መመልከት ተያያዝነው። ለነገሩ የኮሌጅ ዘመን ደስ የሚለው ለዚሁ ነው። ወደ አንዱ ማዘንበል ወይንም ነገሩን ሳያብጠረጥሩ መቀበል የተለመደ ነው። በመሠረቱ አንድ ሳይንቲስት አንድን ሐሣብ በችኩልነት ማጣጣል የለበትም። ጊዜ እና ዘመን በመስጠት የጉዳዩን መጨረሻ ግብ ማየት አለበት። እኔ ልቤ የፈቀደው አባባል “እውነትን አሳድድ” ነበር። በመሆኑም “ለመቀበል ተመራመር” ወደሚለው አዘነበልኩ።

የትኛው ባዮራዲዬሽን ይህንን የኤሌትሪክ ስርጭት በሰውነታችን ሴል አንደሚፈጥር አላውቅም። እስካሁን የደረስኩበት ሆነ በራሴ መንገድ የለካሁት እርግብግቡን ብቻ ነው። እርግብግቡም 1520,000 ህርዝ እስከ 9,460,000 ህርዝ ሲሆን ዝቅተኛው የሰው እርግብግብ መጠን ከከፍተኛው የኤ ኤም ሬዲዮ እርግብግብ ጋር ይመሳሰላል።

ማንኛውም ስለ ሬድዮ እርግብግብ የሚያውቅ ሰው እንግዳ ፀባዩንም የሚያውቅ ይመስለኛል። እንግድነቱ ግራ በማጋባቱ ሳይሆን በአስደናቂነቱ ነው። አንድ ሰርኪዩት ተሠርቶ ባይጠናቀቅ ወይንም ባይዘጋ እንኳን ሬድዮ እርግብግብ መተላለፉን አያቋርጥም። ሰውነት ሆነ ሌላም ነገር ከሰርኪዩቱ ጋር ሳይያያዝ ወይንም ሳይነካካ ያገኘዋል። በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮች ሆኑ እኛ እራሳችንም ይህንን አስገራሚ ነገር ያገኘነው ከሰውነታችን ኢንዳክቲቭ እና ካፓሲቲቭ ባህሪይ ነው።

ጥገኛ ነፍሳትን መደምሰስ

መደምሰስ ስንል በአጠቃላይ በሽታ የሚያመጡብንን ጠንቆች በኤሌትሪክ ኃይል ማስወገድ ማለት ነው። ለብዙ ጊዜያት የተጠቀምኩበት ይኸው የእርግብግብ መሣሪያ በግዢ የተገኘ ነው። ጥገኛ ነፍሳትንም ተራ በተራ ነበር የሚደመስስልኝ።

በመጀመሪያ ከ80 የሚበልጡ የተዋሃሲይን እና የቫይረሶች የእርግብግብ ሠንጠረዥ አወጣሁ።(ክፍል 3ን ይመልከቱ)። ከእዛ በሽተኛ ሲመጣ እመረምር እና ያለበትን ችግር ሳውቅ ለእዛ የሚመጥን እርግብግብ ለ3 ደቂቃ እሰጠዋለሁ። አንዳንዱ በሽተኛ ሁለትም ሦስትም ከእዛ በላይም ችግር ስለሚኖርበት ብዙ እርግብግብ ሊሰጠው ይችላል። ይህንን ሁሉ ለማድረግ 2 ሰዓት ይፈጃል። ድንገት ሰንጠረዥ ውስጥ ያልተጠቀሰ ችግር ያለበት በሽተኛ ከመጣ ደግሞ ሰዓቱ እጥፍ ይሆናል። አንዴ ይህ ከተደረገለት በሽተኛው ወዲያውኑ ይሻለዋል። ሆኖም ብዙ አይቆይም ወዲያው ይመለስበታል። ተመልሶ ያው የበሽታ ስሜት ይታይበታል። በወቅቱ ያላወቅኩት ነገር ቢኖር ቫይረሶች ወደ ሰውነታችን ውስጥ ሲገቡ እኛንም በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ጥገኛ ነፍሳትንም ሰለሚለክፉ እነዚህን ጥገኛ ነፍሳት ከሰውነታችን ካላስወገድን ፈፅሞ ከበሽታው ልንፈወስ አለመቻላችንን ነበር።

በ1993 ልጄ ጀፍሪ በዚህ ሥራ ይተባበረኝ ጀመር። ከትንሹ ጥገኝ ነፍሳት እርግብግብ ጀምሮ እስከ ትልቁ ጠገኛ ነፍሳት እርግብግብ አጠቃሎ በመመዝገብ በኮምፒዩተር እየታገዙ መሥራት የሚቻልበትን ዘዴ አበጀ። ይህም ከ290,000 ህርዝ እስከ 470,000 ህርዝ እርግብግብን የሚሸፍን ሆኖ በእየ 1000 ህርዝ ልዩነት ላይ ለ3 ደቂቃ ኮምፒዩተሩ እራሱ እየቀየረ ማስተላለፍ የሚቻልበት አሠራር ነበር። በዚህ አሠራር ከላይ የተጠቀሰውን ህርዝ ለመሸፈን 10 ሰዓት ያስፈልጋል።

በዚህኛውም መንገድ ቢሆን ብዙ አልተደሰትኩም። ቁርጥማት፣ የዓይን ሕመም፣ የብርድ በሽታ የመሳሰሉ ተቀርፈዋል።ሆኖም በአንድ ቀን ከሁሉም በሽታ መገላገል አልተቻለም። ከወር በኋላ አንድ ነገር አገኘሁ። ይኸውም ጥገኛ ነፍሳት ዝቅተኛ እርግብግባቸው 170,000 ህርዘ ከፍተኛ እርግብግባቸው 690,000 ህርዝ መሆኑን። ታዲያ ይህንን ስፋት ከላይ እንደጠቀስኩት 1000 ህርዝ በ3 ደቂቃ እያስተላለፉ ለመሽፈን ቢያንስ 26 ሰዓት ነው የሚፈጀው። ሰዓቱስ ምንም ባልጎዳ ነበር። ውጤቱ ግን አሁንም አያስደስትም።

አንድ ዓመት ሙሉ ይህንን ነገር በተለያየ መልኩ ስንሞክር አሳለፈን። በ1994 ልጄ አንድ በእጅ የሚያዝ እና በባትሪ የሚሠራ የእርግብግብ መሣሪያ አበጀ።  ይህ መሣሪያ ወጪው ዝቅተኛ አገልግሎቱ ግን እጅግ ከፍተኛ እና አስደናቂ ነው። ማንኛውንም ዓይነት ጥገኛ ነፍስት ከትንሽ እስከ ትልቅ መደምሰስ ይችላል። ታላቅ ጥበብ የተሞላበት ፍልስፍና ነበር።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.