እንቁላል የካንሰር፣ የስኳር እና የልብ ህመም ስቃይን መቀነስ እንደሚያስችል የጤና ባለሙያዎች ገለፁ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ህክምና መከታተል፣ ውፍረትን መቀነስ እና አመጋገብን ማስተካከል የሰው ልጅ ጤናውን ለመጠበቅ ከሚያደርጋቸው ተግባራት መካከል ይጠቀሳሉ።

በየዕለት ውሏችን የምንከተለው የኑሮ ዘይቤ እና አመጋገብም በጤናችን ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

እንቁላል በፕሮቲን የበለፀገ መሆኑ ለሰውነታችን ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው፤ ከዚህ ውጭ ቫይታሚን ዲ እና ሌሎችም የቫይታሚን ንጥረ ነገሮችን በውስጥ መያዙ ደግሞ ለጤናችን የሚሰጠውን ፋይዳ ጉልህ ያደርገዋል።

እንቁላል የተለያዩ የቫይታሚን ንጥረ ነገሮችን በውስጡ መያዙም የካንሰር፣ የስኳር እና የልብ ህሙማንን ስቃይ እንደሚቀንስላቸው ነው የጤና ባለሙያዎች የገለፁት።

ሮብ ሆብሰን የተባሉ የሄልዝ ስፓን የስነ ምግብ ድርጅት ሃላፊ እንቁላል ሰዎች በየቀኑ በብዛት የሚመገቡት ምግብ ነው ይላሉ።

በፕሮቲን እና በቫይታሚን የበለፀጸገ መሆኑ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ንጥረ ምግብ ከእንቁላል በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

እንቁላል ለሰውነታችን ተስማሚ ያልሆኑ እና በሽታ አምጪ ተህዋስያንን የሚያስወግድ ንጥረ ነገር ስላለው፥ በሰውነታችን ውስጥ ህመም ቢያገጥመን ሰቃዩን ይቀንስልናል ብልዋል ሮብ ሆብሰን።

በተለይም እንቁላሉ ንጥረ ነገር በዘይት እና በክሬም አዋህዶ ካዘጋጁ በኋላ መመገብ ለሰውነታችን የሚሰጠውን ጥቅም ላቅ ያደርገዋል።

እንቁላሉን ለምግብንት ስንሰራም የምናዘጋጅበት መጠነ ሙቀት ዝቅተኛ መሆን እንዳለበት የምግብ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.