pleaser_milanመቼም ቢሆን መቼ የሚያጠብቅና ረጅም ታኮ ያላቸው ጫማዎችን ሲጫሙ ተፈጥሮ እግር ካስቀመጠችለት ቅርፅ ውጭ እንዲራመድ እያሰገደዱት እንዳሉ ያስታውሱ፡፡ ባለረጃጅም ተረከዝ ጫማዎችን በተጫሙባቸው ወቅቶች የሰውነትዎ ጠቅላላ ከብደት በሙሉ እግርዎ ላይ ከማረፍ ይልቅ ወደጣቶችዎ ያመራል፡፡ ምክንያቱም ታኮ ወደ ላይ መነሳቱንና ጣቶችዎ ወደፊት ማዘቅዘቃቸውን ተከትሎ ክብደትዎ ወደጣቶችም በማምራቱ ነው፡፡

በየቀኑ በረጃጅም ተረከዝ ታኮዎች የሚጫሙ ከሆነ ቢያንስ በ2 የእግር ህመሞች የተጐዱ እንደሆኑ አይጠራጠሩ፡፡ እነዚህ በእርግጠኝነት ይከሰታሉ ተብለው የሚታመኑ ‹corns› እና ‹causes› ተብለው የሚጠሩ ክፍሎች ናቸው፡፡ እነዚህ የህመም አይነቶች እግርዎ ከጫማዎ ጋር በሚያደርገው ፍትጊያና አጓጉል የኃይል ጭነት ምክንያት የቆዳ መሞት /መደንደንና መጠንከር/ አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ ጣቶችዎ በሚደርስበት ከባድ ጫና ከጫማዎ የፊት ግድግዳ ጋር በእጅጉ ስለሚጣበቅ ጥፍር ወደውጭ ከማደግ ይልቅ ወደውስጥ ማደግ መጀመሩ ነው፡፡ ከዚህና በተጨማሪ ባለረጅም ታኮ ጫማ በመጫማታችን ጣቶቻችን ጐብጠው እንዲቀሩ የምናደርግ ሲሆን ይህንንም ችግር ‹‹Hammertoe›› ሲሉ ይጠሩታል፡፡

በእርግጥ በ20ዎቹና በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች ባለረጅም ታኮ ጫማዎችን ሲጫሙ ምንም አይነት ችግር ላይሰማቸው ይችል ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ዕድሜ እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ የእግራችንም ቅርፅ መለወጥ ይጀምራል፡ ፡ የእግራችንን አጥንት እንዲከላከል ተፈጥሮ ያስቀመጠችው ሥጋ ወደፊተኛው የእግራችን ክፍል የሚሰባሰብና የተቀረው እግር ሥር ያለው ሥጋ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መምጣቱም የዚህ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ አይነቱ የሥጋ /የፋት/ ከቦታው መሸሽ ፍላት ጫማዎችን በምንጫማ

ወቅት ተረከዛችን ያለምንም መከላከያ ሥጋ ከመሬት ጋር እንዲገናኝ የምናደርገው ሲሆን፤ በዚህ መነሻ ‹fractures› እና ‹Osteoarthritis› ለተባሉ ችግሮች እንጋለጣለን፡፡

በዚህ ችግር የተጠቁ አብዛኞቹ ሴቶች ከተረከዛቸው የተሰወረውን መከላከያ ሥጋ ለመመለስ የተለያዩ መንገዶችን ሲከተሉ ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ ያህል በህክምና በመታገዝ ሲልኮንን የመሠሉ አርተፊሻል ሙሌቶችን በእግሮቻቸው ላይ ያስደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ የአሜሪካ የኦርፔዲክ የእግርና የጉልበት ማህበር እንዲህ አይነቱ እርምጃ አደገኛ መሆኑን ይገልፃል፡፡ ማህበሩ እንደሚጠቁመው መሠል መንገዶችን መጠቀም ለኢንፌክሽን፣ ለነርቭ ጉዳትና ለመራመድ መቸገርን የመሰሉ እክሎችን ይፈጥራል፡፡

በባለረጅም ተረከዝ ጫማዎችዎ የሚደርሱብዎን ችግሮች ያስታውሱ

– ባለረጅም ተረከዝ ጫማ መጫማትዎ የሰውነትዎ ክብደት በሙሉ ወደ እግር ጣቶችዎ እንዲያጋድል ምክንያት ይሆናል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የተቀረው ሰውነትዎን ሚዛን ለመጠበቅ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነትዎን ክፍል ቀና አድርጐ መጓዝ የግድ ይልዎታል፡ ፡ ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊውን የአቋቋም ይዘት መለወጥ በመሆኑ ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡

– ባለረጅም ተረከዝ ጫማ አድርጐ መጓዝ ማለት በአንድ አግዳሚ እንጨት ወይም ብረት ላይ እንደመራመድ በእያንዳንዷ እርምጃ የሰውነትዎን ሚዛን ለመጠበቅ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ይህም በራሱ ከትኩረትዎ የተወሰነውን ፐርሰንት እርምጃዎ ላይ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሲሆን በውስጥዎም መጠነኛ ውጥረት እንደሚፈጠር ምክንያተ ይሆናል፡፡ ለምን ሲሉ በዚህ ጫና ውስጥ ይቆያሉ?

ባለረጅም ታኮ ጫማዎችን ሲጫሙ ሊወስዷቸው የሚገቡ 5 ጥንቃቄዎች

ረጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች በመጫማትዎ ብቻ እነዚህ ከላይ ለጠቀስናቸውና ለሌሎች በርካታ ችግሮች እንደሚጋለጡ ቢያውቁም ያለረጅም ጫማ አልጫማም የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ እርስዎም ከእነዚህ ሰዎች መደብ ከሆኑ ቢያንስ እነዚህን ነጥቦች ያስታውሱ፡-

1. ባለረጅም ታኮ ጫማዎችም ያልሰፉዎ ወይም ያልጠበብዎ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከልክዎ ሰፋ ያሉ ከሆኑ እግርዎ ወደፊት እንዲንሸራተትና ጣቶችዎ ከጫማው የፊት ገፅ ጋር እንዲፋተግ ምክንያት ይሆናልና ነው፡፡

2. ለረጅም ሰዓታት እነዚህን ጫማዎች አድርገው የሚቆሙ ወይም የሚራመድ ከሆነ ለስላሳና ወፈር ያለ የጫማ ገበር ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡

3. የጫማዎ ተረከዝ ምንም ያህል ቢረዝምና ቢያጥር ከቀጫጭን ተረከዞች ይልቅ ሠፋ ያለ ተረከዝ ያላቸውን ጫማዎች ይምረጡ፡፡ የሰውነትዎን ከብደት ሚዛን/ባላንስ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

4. ጫማዎ ወደፊት የሚያጋድልበት መጠን በተቻለ መጠን አነስተኛ መሆኑትንን ያረጋግጡ፡፡

5. የጫማዎ ተረከዝ ከፍታ ትልቅም ይሁን መጠነኛ ከተረከዙ ክፍት የሆኑትንና ባለዘለበቶቹን ይምረጡ፡፡

‪Source:  clickhabesh.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.