ከዚህ በታች የተጠቀሱት የጤና እክሎች ከካንሰርና ህክምናው ሊመነጩ ይችላሉ። በተጨማሪም ድካምን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
o   የደም ማነስ፤ ተቅማጥ/ሸርተቴ፤ የሰውነት ድርቀት (dehydration)፣ ትኩሳት ወይንም ኢንፌክሽን፤ ማቅለሽለሽሰ ወይህም ትውከት፤ ሌሎች የህመም ስሜቶች
o   መደበር (depression) በሚቀጥሉት ክፍሎች የበለጠ ይብራራል።
o   ሌሎች የካንሰር ህክምና የሚያስከትሉዋቸው እክሎች የሚከተሉት ናቸው
o   አነስተኛ የምግብ ፍላጎትና የተመጣጠነ ምግብ ማነስ
o   የሰውነት ውሀ መቀነስ (ለምሳሌ በቂ ፈሳሽ አለመጠጣት)
o   ኢንሶማንያ (እንቅልፍ ማጣት ወይንም የተለመደው የ እንቅልፍ ሁኔታ መቀየር) ከለሊት እንቅልፍ ብዙ ጊዜ መንቃት
o   መጨነቅና መጠበብ
o   በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ አለመኖርአንዴ ህክምናዎን ካጠናቀቁ በሗላ ቀድሞ የነበሮት አቅም/ጉልበት ሊመለስ ይችላል። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ አንዳንድ ከካንሰር የዳኑ ሰዎች ለማገገም (ወደ የቀድሞው አቅማቸው ለመመለስ) ወራቶች ወይንም አመታት ሊወስድባቸው ይችላል። የእንደዚህ አይነቱን ረጅም ጊዜ የሚቆይን ድካም መንስኤ ለመናገር አዳጋች ነው።

ከካንሰር የተያያዘና በየዕለቱ የሚያጋጥሞት ድካም የተለያየ ነው።

የተለመደ ድካም
 o   ከፍተኛ/ ሀይለኛ (intense)ነው።
o   ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው።
o   በጥሩ የማታ እንቅልፍ ሊወገድ ይችላል።ከካንሰር ጋር የተያያዘ ድካም
o  ባልተለመደ መንገድ የበዛና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነው።
o  ምንም አይነት እረፍት ቢደረግ ሊወገድ አይችልም።
o  ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነው።
o  በየእለቱ ሊያከራውኑ የሚያስፈልጎትን ነገሮች ለማድረግ ያዳግታል።ያስታውሱ
o   ድካምን መቆጣጠር ይቻላል
o   ድካሞን መቆጣጠር ህክምናዎን ለመቀጠልና ለመከታተል ይረዳዎታል።
o   መቼ የሌሎች ሰዎችን ድጋፍ መጠየቅ እንዳለብዎት ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
o   ለዚህ አይነቱ እክል የተጋለጡት እርስዎ ብቻ አይደሉም።

የኑሮዎን ጥራት ማሳደግ ይችላሉ።

የድካም ምልክቶች

 o   የአቅም/ጉልበት ማነስ
o   “ይህንን ለመስራት መጨነቅ የለብኝም ወይንም አቅም የለኝም” የሚል ስሜት መኖር
o   ለመተኛት አለመቻል
o   ጧት ከእንቅልፍ ከነቁ በሗላ ከመኝታ ለመነሳት አለመቻል
o   የመደበር ወይንም የመረበሽ(anxious) ስሜት
o   በጡንቻ ውስጥ የሚሰማ የህመም ስሜት
o   ቀላል ስራዎችን ከሰሩ ወይንም ከተንቀሳቀሱ በሗላ የመተንፈስ ችግር ወይንም የትንፋሽ እጥረት
o   አትኩሮ ለመስማት/ለማሰብ አለመቻል(finding it hard to concentrate)
o   ግልጽ በሆነ መንገድ ማሰብ አለመቻል ወይንም ውሳኔዎችን ለማሳለፍ/ለመስጠት ማዳገት
o   ቀድሞ ማድረግ የሚወዱትን ነገር ለማድረግ ፍላጎት ማጣት
o   ለራስዎና ለሌሎች ሰዎች አሉታዊ(negative) ስሜቶች መኖር

Fatigue የሰውነት ድካም

6717193

ካንሰርና ህክምናው ጉልበትዎን በእጅጉ ይቀንሳል። ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ብርቱ/intense ድካም (acute fatigue)  ይሰማዎታል ነገር ግን ጥሩ የምሽት እንቅልፍ በመተኛት ድካሞን ማስወገድ  ይችላሉ። ሆኖም ግን እጅግ የበዛና በተደጋጋሚ  የሚከሰት ድካም (chronic fatigue) ተለይቶ መታየት አለበት። ይህ በተደጋጋሚ የሚከሰት ድካም በየጊዜው ከመከሰቱ ባሻገር በየዕለቱ በሚኖርዎት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማድረግ የሚኖሩበትን ሁኔታ/ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል። ቀድሞ ያለምንም ችግር የሚያከናውኑዋቸውን ነገሮች ሁሉ ማከናወን በድካም ምክንያት ያቅቶታል።ጥሩነቱ እንዲህ አይነቱን ድካም አብዛኛውን ጊዜ መቆጣጠር ይቻላል። ምን ማግኘት እንደሚፈልጉና ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ ካወቁ ለእርስዎ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማድረግ የሚበቃ ጉልበት እንዲኖርዎት ማድረግ ይችላሉ። ለዚህ ዋነኛው እርምጃ የሚሆነው የድካሞን መጠን ለይቶ ማወቅ ነው። ይህንንም የሚከተለውን በማድረግ ሊገነዘቡት ይችላሉ።1.     ከዚህ የተያያውን መጠይቅ በመሙላት የሰውነት ድካምዎ በየእለቱ ከሚያደርጉት ነገሮች ጋር ምን ያህል እንዳስተጓጘሎት ማወቅ ይችላሉ።
መጠይቁን ለማግኘት

ይህንን ይጫኑ

 2.    የሰውነት ድካም መለኪያ ደረጃን  በመለየት ዛሬ ምን እየተሰማዎት እንደሆነ ለይተው ማወቅ
3.    ይህንን መረጃ ለሀኪምዎ ወይንም ለባለሙያ በማሳየት ምክር መጠየቅ ይችላሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.