በአልን በወሲብ ድግስ ማክበር የጥቂት ሃብታሞች ስራ ሳይሆን የመደበኛ ዜጎች ባህሪ እየሆነ ነው! ኧረ ሞራል የት ገባሽ?

የወሲብ ኢንደስትሪ አለምን ከሚገዙ ጥቂት ኢንደስትሪዎች አንዱ ለመሆኑ በርካታ የስነ ማህበረሰ ባለሙያዎች መናገር ጀምረዋል። ፒተር ኖዋክ የተባለው አሜሪካዊ ፀሃፊ በጥልቅ ምርምር ስራ ያሳተመው Sex bombs and burgers መፅሃፍ የወሲብ ኢንደስትሪው ከአለማችን የእለት ተእለት ትኩሳት ከሆነው የፖለቲካ ደም መፋሰስ እኩል ትኩሳት መፍጠሩን በዝርዝር አስነብቧል።

በበአል ወቅቶችም የዚህ ኢንደስትሪ ገበያ ልክ እንደሌላው ግብይት ሁሉ ይጨምራል። በአመት በአል ሰሞን ለወሲብ ጉዞ (sex vacation) ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ቱሪስቶች ብዙ ናቸው። በአለም ዙሪያ ደጃቸውን ከፍተው የሚጠብቋቸውን የወሲብ ንግስቶች ይጎበኛሉ። ቱሪስት ሲባል መቼም ገንዘብ ያለው ነው። ገንዘብ ሰብስቦ እነዚህ የወሲብ መላእክቶች ላይ ሊያፈስ የሚዞር ነው ተብሎ ነው የሚታሰበው። ደግሞም ነው። ዋጋው በተራ ዜጋ የማይቀመስ መሆኑ እነማን የዚህ ምግባር ጌቶች እነማን መሆናቸውን በግልፅ ያሳያል።

“ ሴትዮ ‘ሆቴል ብቻ ነው የምሄደው ፤ ለደህንነቴ እጠነቀቃለው’ ያልሽው ተመችቶኛል። የማይተዋወቁ ሰዎች ሆቴል ውስጥ አይጋደሉም ያለሽ ማነው”

ይህ በአልን በወሲብ ድግስ የማክበር የጥቂት ሃብታሞች ባህል ግን አሁን አሁን ወደ ተራ ዜጎችም እየተሸጋገረ መሆኑ ግርታን ፈጥሯል። ብሪታንያ ውስጥ በሚታይ አንድ የቴሌቪዥን ቶክሾው ላይ የቀረበች እናት ብዙዎችን አስገርማለች። የሁለት ልጆች ወላድ የሆነችው እንስት ወሲብ ፍለጋ በአል በመጣ ቁጥር ከአገር እንደምትወጣ ተናግራለች።

“የዛሬ አምስት አመት ገደማ ገናን ለማክበር ወደ ቆጵሮስ ከሄድኩበት ጊዜ ጀምሮ ነው ይህን ማድረግ የጀመርኩት። አንድ ነገር ለማደን ከአገር እወጣለው ፤ እሱም ወሲብ ነው” ብላለች።

የ 42 አመቷ ሴትዮ ፍላጎቷን ለሟሟላት ፤ አይታው ከማታውቀው ሰው ጋር ወሲብ ለመፈፀም እሰው አገር ከገባች በኋላ ግማሽ ቀን አይፈጅባትም።

“መጠጥ ቤት ገብተህ መጠጥ ይዘህ መቀመጥ ነው። 20 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አንዱ መቶ ካላዋራሁህ ይልሃል። ከወደድከው ጥርስህን መግለጥ ነው። ከአንድ ሰኣት ጨዋታ በኋላ ወይ የእሱ ቤት አልጋ ላይ ወይ ስሙን የማታውቀው ሆቴል አልጋ ላይ እርቃን ሰውነትህን ታገኘዋለህ። ለነገሩ እኔ ሁልጊዜም ሆቴል ብቻ ነው የምሄደው ፤ ለደህንነቴ እጠነቀቃለው” ስትል ጨምራ ተናግራለች።

የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን ያዩ ተመልካቾች ግን አልደገፏትም። በትዊተር አስተያየቱን የሰጠ አንድ ተመልካች “ ሴትዮ ‘ሆቴል ብቻ ነው የምሄደው ፤ ለደህንነቴ እጠነቀቃለው’ ያልሽው ተመችቶኛል። የማይተዋወቁ ሰዎች ሆቴል ውስጥ አይጋደሉም ያለሽ ማነው” ሲል የምፀት ምላሽ ፅፏል።

ሌላ ተመልካች ደግሞ “ሴትየዋ አይን ያወጣች ቂል ናት ፤ ሰዎች እንዴት መሬ ሆነዋል? በቃ የሰው ልጅ ሞራል የሚባል ነገር ጠፋበት እንዴ!” ብሏል።

 

እኛ የምናውቀው ‘በአመት በአል ወደ አገሬ ልግባ ዘመድ ጥየቃ ፤ ቤተሰብ ጥየቃ’ ሲባል ነው። አሁን ‘በአመት በአል ከአገሬ ልውጣ ሴት ፍለጋ ፤ ወንድ ፍለጋ’ እየሆነ ነው መባሉ ገርሞናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.