የልብ በሽታ

ልቅ ሰው 

የልብ በሽታበሰውነታችን ውስጥ ደም የሚሰራቸጨው በልብ አማካኝነት ነው፡፡ ልባችን ለመላው ሰውነታችን ደም ለማሰራጨት የደም ስሮችን ይጠቀማል፡፡ በልባችን ውስጥም ያሉ የደም ስሮች ኦክስጅን እና ከምግብ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን ለልባችን ያደርሳሉ:: እነዚህ በልባችን ውስጥ ያሉ የደም ስሮች በስብ (ፋት) ሊደፈኑ ይችላሉ:: ይህም ለልብ ድካም፣ ስትሮክ ወይንም ለሌሎች የልብ በሽታዎች ሊያጋልጦት ይችላል፡፡የልብ በሽታዎችን እንዴት መከላከል እንችላለንዘወትር ስፖርት በመስራት
ጤናማ የሆነ የሰውነት ክብደት በመጠበቅ
ሲጋራ ማጨስ በማቆም ወይንም ባለመጀመር
የደም ግፊቶን በማወቅ እና በመጠበቅ
የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡ
ብዙ አታክልት፣ ፍራፍሬዎች እና ጥራጥሬዎች ይመገቡ
ስብ (ፋት) የበዛባቸው ምግቦችን ይቀንሱ፡፡ እነዚህም በዘይት የተጠበሱ ምግቦችን፣ የዘይት ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያካትታሉ፡፡
ኮሌስትሮል የበዛባቸው ምግቦች አይብሉ: : ኮሌስትሮል ማለት በእንስሳ ስጋ ውስጥ የሚገኝ ስብ (ፋት) ሲሆን በስጋዎች፣ በቅቤ፣ በእንቁላል አስኳል፣ በወተትና በክሬም ውስጥ ይገኛል፡፡
የልብ በሽታ ምልክቶች

በእርግጥ የልብ በሽታ ምልክቶች በልባችን ዙሪያ የሚገኙ የደም ወሳጅ (አርተሪ) የተባሉ የደም ሥሮች ካልተዘጉ በስተቀር በቀላሉ አይታዩም፡፡ ሐኪሞት ልቦት ምን ያህል ጤነኛ እንደሆነ በምርመራ ሊያውቅ ስለሚችል በየአመቱ ቀጠሮ ይዘው ይመርመሩ:: የሰውነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በደረትዎ ላይ የሚሰማዎትን ዓይነት የመጫን ስሜት በሌላ ጊዜ ከተሰማዎት በአስቸኳይ ወደ ሐኪም ጋር ይሂዱ፡፡

ድንገተኛ የልብ ድካም ምልክቶች

ከፍተኛ የደረት ሕመም
ወደ ክንድዎ፣ ትከሻ፣ ጀርባ ወይም መታጠፊያዎች የሚዛመት የደረት ሕመም
ከፍተኛ የመተንፈስ ችግር
የላብ መብዛት፣ ወደ ላይ የማለት (የማስታወክ) እና የማዞር ስሜት
እነዚህን ምልክቶች በራሶ ወይም አቅራቢያዎ ያለ ሰው ላይ ከተመለከቱ ወዲያውኑ አምቡላንስ ይጥሩ እስከዛም አስፕሪን ይዋጡ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.