በደማችን ውስጥ የሚገኝ የቪታሚን ዲ ክምችት በካንሰር የመያዝ እድላችንን ሊቀንሰው እንደሚችል የጃፓን አጥኚዎች አስታወቁ።

ጥናቱ ያተኮረው በዋናነት በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ መሆኑ ተነግሯል።

በጥናቱ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት እስከ 69 ዓመት በሚገኙ 33 ሺህ 736 ሰዎች ላይ መካሄዱን ገልጸዋል።

ታሳታፊዎችም የጤና ታሪካቸውን መረጃ ለአጥኚዎቹ የሰጡ ሲሆን፥ በተጨማሪም የቪታሚን ዲ ክምችት ለማወቅ የደም ናሙና መወሰዱን አጥኚዎቹ አስታውቀዋል።

ሂደቱ ለ16 ዓመታት መቆየቱን የተናገሩት ተመራማሪዎች በ3 ሺህ 301 ሰዎች ላይ አዲስ የካንሰር ምልክት ማየታቸውን ገልጸዋል።

በዋናነት ካንሰር አማጪ ተብለው የተለዩ እንደ ዕድሜ፣ ክብደትና አብዝቶ መጠጣት የመሳሰሉትን ታሳቢ በማድረግ ጥናቱ 20 በመቶ በካንሰር የመያዝ እድልን እንደሚቀንስ አሳይቷል።

እንዲሁም በጉበት ካንሰር የመያዝ እድልን ደግሞ በተለይ ለወንዶች 50 በመቶ መቀነሱን ገልጸዋል።

በአንጻሩ የቪታሚን ዲ ክምችት የሳንባና የፕሮስቴት ካንሰርን እንደማይከላከል ጥናቱ አሳቷል።

ቪታሚን ዲ በሰውነታችን ውስጥ የሚመረተው ቆዳችን ለፀሐይ ብረሃን በሚሰጠው ምላሽ ሲሆን፥ በሰውነታቸን ውስጥ የካልሲየምን ይዘት በመቆጠጠር አጥንትን፣ ጥርስንና ጡንቻዎችን ይረዳል።

በሌላ በኩል በተፈጥሮ የምናገኘው ቪታሚን ዲ እንደ የአገሩና እንደ የሕዝቡ እንደሚለያየም ነው የተጠቀሰው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.