ኪንታሮት በዘመናዊ ህክምና የሚድን በሽታ ነው

7

የበሽታ ቀላል የለም፡፡ ምክንያቱም ቀለል ያለ በሽታ ለጉዳት አሳልፎ አይሰጥም በማለት ብዙዎቻችን ወደ ህክምና የመሄዱሁኔታ አይታየንም፡፡ ሆኖም እንደቀላል ያየነው በሽታ ባህሪይውን ይለውጥና የጤና መቃወስን ማስከተሉ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው የህመም ስሜት ሲሰማው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ባለሙያን ማማከር ግድ ይለዋል፡፡

Hemorrhoidsየኪንታሮት በሽታ በህክምናው አባባል (ሄሞሮይድ) በፊንጢጣ ዙሪያ የሚመጣ የደም ስር ማበጥ ነው፡፡ ሆኖም የደም ስር ብቻ ሣይሆን የሚያብጠው ደምስርን የሚይዘ ው የፊንጢጣ ዙሪያ አብሮ የሚያብጥበት የበ ሽታ አይነት ነው፡፡ የኪንታሮት በሽታ ወይም ሄሞሮይድ በአብዛኛው የሚከሰተው ፊንጢጣ አካባቢ ነው፡፡ በፊንጢጣ አካባቢ ሄሞሮይድ የሚባሉ ሶስት ዓይነት የደም ስሮች አሉ፡፡ እነሱም፡-በቀኝ በኩል፣ በፊትና በኋላ በኩል፣ በግራ በኩል የሚገኙ ናቸው፡፡ እነዚህ የደም ስሮች ሲያብጡ በሽታው በፊንጢጣ አካባቢ ይከሰታል፡፡ አልፎ አልፎ ሌላ ቦታ ሊከሰት እንደሚችል የህክምና
ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ኪንታሮት ማንኛውንም የህብረተሰብ ክፍልን እንደሚያጠቃ የሚገልፁት ባለሙያዎ ች በአብዛኛው አምራቹን የህብረተሰብ ክፍል ያጠቃል፡፡ ወላድ ሴቶች ላይም ይከሰታል፡፡ ወላዶች ላይ እርግዝና ስላለ እርግዝናው የደም ስሮችን ይጫ ናል፡፡ በዚህ ምክንያት በሽታው ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህ በሽታ ከስቴት ስቴት በሚዟዟሩ (ረዥም ጊዜ በሚያሽከረክሩ) በሹፌሮች ላይም ይታያል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለብዙ ሰዓታት ተቀም ጠው ስለሚውሉ ወይም የሚ ቀመጡበት ቦታ ጠበብ ያለች በመሆኗ ደምስርን ተጭኖ ስለሚይዘው ነው፡፡ ወላዶች ላይ ብዙውን ጊዜ የማማጥ ሁኔታ ከታየባቸው በሽታው ሊከሰት እንደሚችል የሚናገሩት የህክምና ባለሙያዎች የሽንት ቧንቧ መጥበብ ኖሮባቸው ለብዙ ጊዜ የሚያምጡ ሰዎች ላይም ይከሰታል፡፡ ድርቀት ኖሮባቸው የሚያ ምጡ ወይም ተደጋ ጋሚ ተቅማጥ የሚያስቀ ምጣቸው ሰዎችም ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

የኪንታሮት ደረጃ

የኪንታሮት በሽታ ደረጃዎች የውጭና የውስጥ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ የውጭ ኪንታሮት የሚባለው ከፊንጢጣ ዙሪ ያ ሆኖ ቆዳ ስር የሚፈጠረው ዓይነት ሲሆን የውስጥ የሚባለው ግን በውስጠኛው የፊን ጢጣ ክፍል የሚከሰት መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የውስጥ ኪንታሮትም ደረጃዎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ደረጃ በውስጡ ብዙ ህመም ሳይኖር ወይም እብጠት ሳይኖር ምልክቱ መድማት ብቻ ይሆናል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ የሚባለው አልፎ አልፎ የመድማት ምልክት ሊኖርበት ይችላል፡፡ ግን ሲያምጡ ወጣ ይልና በራሱ ጊዜ የሚገባው ነው፡፡ ሦስተኛው ደረጃ ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ ሰዎቹ በግድ እንደገና የሚመልሱት ዓይነት ሲሆን አራተኛው የሚባለው ወጥቶ የሚቀረው ነው፡፡

ጠበብት እንደሚሉት ይህ በሽታ አልፎ አልፎ ከሌላ በሽታ ጋራ ግንኙነት አለው፡፡ ድርቀት ያለባቸው፣ ለብዙ ጊዜ የሚ

ያምጡ ወይም ተቅማጥ ያለባቸው በሽተኞች ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ስለዚህ ድርቀትን የሚያመጣ፣ ተቅማጥ የሚያመጣ ነገር እንደመነሻ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ሌላው የሽንት ቧንቧ መዘጋት ያለባቸው ሰዎች ኪንታሮት ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ጉበታቸው በበሽታ የተጠቃ ሰዎች ላይም ደም ስሮቻቸው ስለሚለጠጡ፣ በሽታ ሳይኖርባቸው ነፍሰ ጡር እናቶች በሚያምጡበት ጊዜ እና በሆድ ውስጥ ካንሰር ያለባቸው ሰዎች በበሽታው ይጠቃሉ፡፡ በዋናነት የመድማቱ ሁኔታ የሚታየው በሚፀዳዱበት ሰዓት ነው፡፡ ማማጥ በሚኖርበት ሰዓት የደም ስሩን ይወጥሩትና እንዲፈነዳ ያደርጉታል፡፡ በተለይም ዓየነ-ምድሩ ድርቀት ኖሮት የማስማጥ ሁኔታ ካለ በሚፀዳ ዱበት ጊዜ ደም ይፈሳል፡፡

እንደ ዶክተሮች ገለጻ እዚህ አሜሪካ የህክምና አማራጮች ቀላል ቢሆኖም ባልሰለጠኑትና እንደኢትዮጵያ ባሉት ሃገራት በማወቅና ካለማወቅ ወይም ከግንዛቤ ማነስ ሰዎች በኪን ታሮት ሲታመሙ ወደ ዘመናዊ ህክምና ተቋም ከመሄድ ይልቅ ባህላዊ መድሃኒት ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ቶሎ መዳን ሲችሉ በሽታው ሲባባስባቸው ይታያል፡፡ እንደሚታወቀው የኪንታሮት በሽታ /ሄሞሮይድ/ አራት ደረጃዎች አሉት፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃዎች የሚባሉት ወደ ቀዶ ህክምናም ላያስኬዱ ይችላሉ፡፡ በቀላሉ በመድሃኒት ና በምክር የሚድን በሽታ ነው፡፡ የኪንታሮት በሽታ (ሄሞሮይድ) ማለት ከባድ በሽታ አይደለም፡፡ ምና ልባት ተጨማሪ ሌላ ሄሞሮይድ መስሎ የሚከሰት እንደ ካንሰር ዓይነት ካልተፈጠረ በስተቀር ለህይወት እንደማያሰጋ የሚገልፁት ዶ/ሮች ሦስተኛና አራተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ የቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው ይሆናል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ው ደረጃ የሚባሉት በዘመናዊ ህክምና የሚፈወስ ስለሆነ ወደ ባህል መድሀኒት መሄዱ ተገቢ አይደለም፡፡ ለዚህ በሽታ ባህላ ዊ መድሃኒት በመጠቀም ፊንጢጣ አካባቢ ችግር ተፈጥ ሮባቸው የሚመጡ ታማሚዎች አሉ፡፡ የባህል መድሀኒቱም ጠባሳውን ያጠቃ ዋል፤ ያብጥናም ፊንጢጣ ውን ይዘጋዋል፤ ለመፀዳዳትም አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡

የኪንታሮት በሽታ ህክምና ያለው ቀላል በሽታ ነው፡፡ የተለያዩ ደረጃዎች ስላሉት እንደ በሽታው ደረጃ ቀዶ ህክምና ሊኖር ይችላል፡፡ የህክምና ባለሙያ ሳያማክሩና ሳይታዩ ባህላዊ መድሃኒት ወስደው ለከፋ ችግር የሚጋለጡ በመኖራ ቸው ወደባህላዊ መድሀኒት ቤቶች ባይሄዱ ይመከራል፡፡ ስለዚ ህ በሽታው ከታወቀ ወደ ህክምና ባለሙያ በመሄድ ባለሙያውን ማማከሩ ተገቢ ነው በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Source: clickhabesh

7 COMMENTS

 1. የኔ ሁሉተኛ ድረጃ ነው የሚያመኝ ሀይለኛ ድርቀት ስመጣ ነው የሚደማውም የዛኔ ብቻ ነው ከዚ በፊት ታይቼ ንነበር የመጀመርያ ያየኝ ችግር የለውም ነበር ሁለተኛው ኦፕራስዪን አለኝ እኔ ህመም የሚሰማኝም ሆነ የሚደማው ድርቀት ሲኖረኝ ነው ምን ላድርግ ወደሌላ ይቀየራል ወይ?

 2. በጣም ላመሰግናቹ እወዳሎህ በራሳችን ቋንቋ ተርጉማቹ ምን እና እንዴት በሽታን መከላከልና መዳን እንዳለብን ስላስተማራቹን፡፡እኔ በ ኪንታሪት በሽታ እምሰቃይ ሰው በኝ 3 ኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ 4 ዓመት አልፎታል መጀመርያ ላይ የተነሳብኝ በድርቀት ሲሆን 2ኛ ደረጃ ላይ የደረሰም ዩኒበርሲቲ ላይ ሆነን ውሀ በመጥፋቱ መፀዳጃቤት ሞልቶና ተግማምቶ ሳንበላ ሳንፅዳዳ ሳምንት በመቆየታችንና በወቅቱ አላማያ ዩኒበርስቲ በሚፈጠሩ የጠባብነት ዓመፆች ረብሻ ስለነበረ አመጋገባችንም ሆነ ንፅህና አጠባበቃችን ከፍተኛ የጤና መቃወስ ስለፈጠረብን ነበር፡፡ያም ሆኖ በቢላ ታርደው ፣ከአልጋ ተወርውረው ሂወታቸው ካጡ ንፁኀን ዜጎች ሳነፃጥራት የኔ ችግር ትንሽ ናት!!! በጣም እየባሰብኝ የመጣውም ስራ ይዜ የመንግስት ሰራተኛ በሆንሁበት ወቅት ስራ አስኪያጁ ስግብግብና ጅል ስለነበረ የሽንትቤቱን ቁልፍ በእጁ ይዞ ስለሚሄድ ለረጅም ሰዓታት ሳልፅዳዳ በሟሌና በተከራየኋት በመኖርያ ቤትም በወረፋ መሽናት ስላስጠላኝ ተጨማሪ ችግር እየሆነብኝ መጥቷል፡፡ በጣም የተደሰትሁት እስካሁን በባህላዊ ህክምና የደረሰብኝ አደጋ ስለሌለ ነው ፡፡ በርግጥ አልተሳካምንጂ ሙከራ አድርጌ ነበረ ! አዲስ አበባ ልደታ ላይ ሆኖ የድሀ ገንዘብ የሚበላው ደጀኔ ብሩ በርካታ ገንዘቤን በልቶ አሰናበተኝ !! ምስጋና ለመድሀኒአለም ይግባውና የሚቀባ ማር ሰጠኝ ገንዘቤን አጥፍቸ በሽታ ሳልጨምር ተለያየን ተመስገን ነው ፡፡ ዘመናዊ ህክምና እንዳልታይ ባገራችን እንደ ጨርቅ እየቆራረጠ የሚጫወት ባለሙያ እንጂ ሙያውን አክብሮ እና ታምኖ የሚፈለገውን ቀዶ ጥገና የሚያካሂድ ሙያተኛ የለም፡፡ ብቃት የለውም ሳይሆን ሥነ-ምግባር የለውም ነው ክርክሬ፡፡ ብቃት እንኳን አይታሙም !!! ሙስና ለመዱ !!! በግላቸው ሆስፒታል ካለሆነ በመንግስት ሆስፒታል በትክክል ታክሞ የዳነ ሰው ለም፡፡ ላልድን ለምን እሰቃያሎህ ብየ ነው እግሬን አጣጥፌ የተቀመጥሁ፡፡
  በግል እንዳልታከም በመንግስት ስራ ስለምተዳደር ለህክምና የሚተርፍ ገንዘብ የለኝም፡፡በርግጥ መስራቤቴ የህክምና ሽፋን ይሸፍንልኛል ግን መስራቤቱ በተዋዋላቸው ቦታዎች በመሆኑ ትክክለኛዎቹን ማግኘት አልችልም፡፡ማንም ተረኛ ፍላጎቱ የሌለው እየደበረው አበላሽቶ ያልጋ ቁራኛ እንዳያደርገኝ ሰጋሁ፡፡ እረ በለማጅ የሚያሰሩም አሉ !! ቆዳችን እኮ እንደ ጨርቅ ቢበላሽ የምንጥለው አይደለም!! የሀገራችን ሰዎች በባህላዊ እና በዘመናዊ ታክመው ከዳኑ መካከል በባህለዊ ታክመው የዳኑትን ስለሚበዙ ነው ወደባህላዊ የምንሮጨው !! እኔ ግን ሁለቱም ከንቱ ናቸው እላሎህ፡፡ሁለቱም ያዳኑት ሰው የለም፡፡
  ዘመናዊ ህክምናዎች ከባህላዊ የሚለያቸው ማደንዘዣ ስለሚጠቀሙ ብዛ ነው፡፡በሞት እና በሂዎት ልዩነት የላቸውም ፡፡እንዴውም በውሀና በሳሙና እየታጠቡ ለስለስ ያሉ ምግቦች እየተመገቡ ሞትዎን መጠበቅ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም፡፡
  ሽንት ቤቶቻችን ውሀ ያላቸው ፣ዘመናዊና ንፁህ ባለመሆናቸው ምክንያት በሽታውን ክፉ ያደርገዋል፡፡ውሀ መጠቀም እምንጀምረው ስንታመም ነው፡፡እንደእውነቱ ግን ሳንታመም ነበር መሆን ያለበት፡፡ውሀ ይዞ ሽንት ቤት መግባት እንደነውር የሚታይበት ሀገር ፣ ምግብ በልተህ ሽንት እምትሸናበት ቦታ የሌላቸው ምግብ ቤቶች የበዙበት ሀገር ፣ የሳኒተሪ ባለሙያው በሙስና የሚመዝንበት ዶክተቱ በሙስና የሚያክምበት ሀገር ላይ እየኖርን የኪንታሮትም የሌሎችም በሽታዎች መጫወቻ መሆናችን አይቀሬ ነው፡፡አዝናሎህ!!
  ሙስና በሁሉም ቦታ ላይ እየገባ ማንነታችንን ተፈታተነን፡፡
  እባካቹ አሁን አዲስ አበባ ከተማ ላይ የሚገኝ በሙያው የተካነ ዶክተር ሙያውን አክብሮ ብትክክል አክሞ የሚያድነኝን ጨቁሙኝ ፡፡እኔ የሚከፈለውን ልክፈል ግን ደግሞ ላያቆጠቁጥ በሙሉ ብቀት እና ጥንቃቄ የሚሰራኝ እፈልጋሎህ፡፡

 3. ኪንታሮት ከያዘኝ አንድ አመት ሆኖኛል ሶስተኛ ደረጃ ላይ ደረሷል እድሜ 23 ሲሆን የ5ኛ አመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ነኝ የያዘኝም በዩንቨርሲቲው በሚቀርበው የምግብ ጥራት ምክንያት ተቅማጥ ያዘኝ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እየደማ አሁን 3ኛ ደረጃ ላይ ደረሷል እና ብዙ ሠዎችን ጠይቂያለሁ ያሉኝም መልስ ቀዶ ህክምና ሂድ ነው ያሉኝ ሁሌም በአእምሮየ ፈፅሞ ደስታ የለኝም ሁሌም እጨነቃለሁ መማር አልቻልኩም ሁሌም በተፀዳዳሁ ቁጥር የሚፈሰው ደም ለደም ማነሰ በሽታም እንደሚያጋልጠኝም አውቃለሁ ምን ትመክሩኛላችሁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.