608የፆታና(Sexuality) ተዋልዶ ጤና ጤናማና ደህንነቱ የተጠበቀ ፆታዊ ግንኙነት፣እርግዝናን እንዲሁም ወሊድን አጠቃልሎ የሚይዝ ነው፡፡ የፆታና ተዋልዶ ጤና በሰዎች ኑሮ ውስጥ በጣም ድብቅ እና የግል ተብለው የሚታሰቡ፣ለመፃፍና በግልፅ ለማውራት የሚከብዱ ጉዳዮችን ያካትታል፡፡በዚህም ምክንያት አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ፆታንና ተዋልዶ ጤናን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረው አድርጎታል፡፡በተጨማሪም ፆታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖናና ድብቅነት ህብረተሰቡን ስለጉዳዩ መረጃና አገልግሎት ከመፈለግ በመገደብ መንግስታትም አስቸኳይ መፍትሄ እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል፡፡

ነገር ግን የፆታና ተዋልዶ ጉዳይ  ከአገሮች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው፡፡ እናቶች በወሊድ ወቅት ሲሞቱ፤ልጆች ወላጅ አልባ ይሆናሉ፡፡ ሴቶችም ታናናሽ እህትና ወንድሞቻቸውን መንከባከብ ስለሚኖርባቸው ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ፡፡ ትምህርታቸውንም የማይከታተሉ ሴት ልጆች ያለዕድሜ ትዳር እንዲመሰርቱ ይገደዳሉ፡፡ይህም ጤናቸውን አደጋ ላይ ከመጣልም አልፎ በህብረተሰባቸውና በአገራቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ይገድበዋል፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ፆታዊና የተዋልዶ ጤና ጉዳዮችን ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማድረግ በሕብረተሰቡ ተሰሚነትና ተፅዕኖ ማሳደር የሚችሉ ግለሰቦችን ግንዛቤ በማዳበር የህብረተሰብ ጤና ፖሊሲው ላይ ግፊት እንዲያደርጉ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ እነዚህ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች መካከል  የመንግስት ባለስልጣናት እና ሰራተኞች፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎች፣የሴቶችና የሀይማኖት ማህበራት፣የትምህርትና የጤና ኤክስፐርቶች እንዲሁም ሌሎች  ተሰሚነት ያላቸው መሪዎችን ያካትታል፡፡

እነዚህ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች በየዕለቱ ጋዜጦችን፣ሬድዮንና ቴሌቪዥን ይከታተላሉ፤አመለካከታቸውም ከዚያ በሚያገኙት መረጃ ይቀረፃል፡፡  አልፎ አልፎ አንድ የዜና ዘገባ አንድን ውሳኔ ሰጪ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን ቀጣይነት ያለው ዘገባና የመረጃ ፍሰት  ለተለያዩ ተደራስያንን በፆታና ተዋልዶ ጉዳች ትምህርትና መረጃ ለመስጠት አስፈላጊ ነው፡፡

በዚህ መመሪያ የተካተቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኢትዮጲያ፣ኬንያ፣ሩዋንዳ፣ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ ይህ መመሪያና በውስጡ የተካተቱት ለመረጃ ምንጭነት ያገለገሉ ሪፖርቶች በመረጃ መረብ ላይ ከሰኔ 12 2009 ጀምሮ ይገኛሉ፡፡

ስለፆታና ተዋልዶ ጤና ትክክለኛና ወቅታዊ ሪፖርቶችን የሚያቀርቡ ጋዜጠኞች፤

  • ድብቅ/ነውር ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮችን በግልፅ ለውይይት እንዲቀርቡ ያደርጋሉ፡፡
  • የመንግስታቸውን የጤና ዕቅድ አፈፃፀም ይከታተላሉ፤ የመንግስት ኃላፊዎች ያለባቸውን ተጠያቂነት ለሕዝብ ያሳውቃሉ፡፡

ይህ መመሪያ በኢትዮጲያ፣ኬንያ፣ሩዋንዳ፣ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ላይ ያተኮሩ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን በማሰባሰብ ለጋዜጠኞች ህብረተሰቡንና ውሳኔ ሰጪዎችን በፆታና ተዋልዶ ጤና  ጉዳይ  ትምህርት እንዲሰጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

የፆታና ተዋልዶ ጤና ለሁሉም

በአለምአቀፍ ደረጃ የፆታና ተዋልዶ ጤና መብት  መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት መሆኑ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ይህም በ1994 እ.ኤ.አ በተካሄደው አለማቀፉ የስነ-ህዝብና ልማት ኮንፈረንስ የፕሮግም እቅድ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡

ከበሽታ ወይም ከህመም ነፃ መሆን ብቻ ሳይሆን የተዋልዶ ሥርዓት ተግባራትና ዕድገታዊ ሂደቶች ጋር የተዛመዱ ማንኛቸውም ጉዳዮችን በተመለከተ የተሟላ :: ልጅ የመውለድ   እና መቼ የሚለውን ለመወሰን እንደሚችሉም ያሳያል፡፡

በአለማቀፉ የስነ-ህዝብና ልማት ኮንፈረንስ ግለሰቦችም ሆነ ጥንዶች የልጆቻቸውን ቁጥርና መቼ መውለድ እንደሚፈልጉ እንዲወስኑ ህዝብ-ተኮር አቀራረብን አስተዋውቋል፡፡ሴቶችን ማብቃት ዋንኛ የዚህ አቀራረብ አካል ነው፡፡

በአለማቀፉ የስነ-ህዝብና ልማት ኮንፈረንስ ስምምነት ተዋልዶ ጤና ከሌሎች የሰዎች የኑሮ ሁኔታዎች ጋር ለምሳሌ ከኢኮኖሚ ፣የትምህርት ደረጃቸው፣የስራቸው አይነት፣የቤተሰባቸው መዋቅር እንዲሁም የሚኖሩበት የፖለቲካ፣የሃይማኖትና የህግ ስርአት ጋር  ቁርኝት እንዳለው አሳይቷል፡፡

ምንም እንኳ የተዋልዶ ጤና  የሰዎች የኑሮ ሁኔታዎች ጋር ይህን አይነት ቁርኝት ቢኖረውም እ.ኤ.አ በ 2000 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት በተካሄደው ስብስባ ከፀደቁት የመጀመሪያዎቹ ስምንቱ የምዕተ ዓመቱ ግቦች ውስጥ ግን አልተካተተም ነበር፡፡ከአምስት አመት በኋላ ግን የአለም መሪዎች ተዋልዶ ጤና የእናቶች ጤናን ለማሻሻል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ያለውን ሚና በማመን የተዋልዶ ጤናን ለሁሉም በ2015 ለማዳረስ ቃል ገብተዋል፡፡

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.