የአስም በሽታን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ 5 ነገሮች

ከዶ/ር ሆነሊያት ቱፈር የአስም በሽታ ሳንባችንን የሚጎዳ የህመም አይነት ሲሆን በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የበሽታው ተጠቂዎች ይገኛሉ፡፡ የአስም ህመም በአብዛኛው ከልጅነት ጀምሮ በመከሰት ደረጃ በደረጃ እያደገ...

የአስም በሽታ

(በዳንኤል አማረ) አስም የአየር ቧንቧዎች በሽታ ሲሆን የአተነፋፈስ ስርዓትን በማዛባት ለመተንፈስ አዳጋች ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ የአየር መተላለፊያ ቧንቧዎችን እንዲቆጡ በማድረግ ወደ ሳንባ ኦክስጂን የሚወስዱ ቧንቧዎችን እንዲጠቡ...

ከሥራ ጋር የተያያዘ ጭንቀት ለአስም ሊያጋልጥ ይችላል

ሥራዬን ላጣ እችላለሁ የሚል ስጋትና ጭንቀት በአስም የመያዝ አደጋን ሊጨምር እንደሚችል በአውሮፓ የተደረገ አዲስ ጥናት አመለከተ፡፡ ጥናቱ በጀርመን የሚገኙ ከ7ሺ በላይ ተቀጣሪ ሠራተኞችን ያሳተፈ...

የሚበሉና የማይበሉ ምግቦች – ለአስም ህመምተኞች

 ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ        በዚህ የክረምት ወራት መግቢያ ወቅት የአስም ህመም የሚቀሰቀስባቸው ሰዎች በርካታ ናቸው፡፡ ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰባቸው ደግሞ ወቅትና ጊዜ ሳይጠብቅ...

አስም ትናንት፣ ዛሬና ነገ – የአስም ህክምናዎችና መድሃኒቶች በቀድሞዎቹ እና በአዳዲስ...

ከመተንፈሻ አካል ጋር ተያይዞ የሚከሰተው የአስም ህመም ከፍተኛ ቅዝቃዜ ባለበት በዚህ በክረምት ተባብሶ የመታየት እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ቀዝቃዛማ ወቅት እኛ ላይ ይበረታሉ እንጂ...

አስም

   

አስም ትናንት፣ ዛሬና ነገ

      Source: goshhealth.org

አስም ምንድን ነው?

አስም የመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሆን የአየር ቧንቧዎች መጥበብን በማስከተል በአተነፋፈስ ላይ ችግር ያመጣል፡፡በተፈጥሮ የአይር ቱቦዎቻችን እንዳጋጣሚ ከሚገባ ከማንኛውም ባእድ ነገር እራሳቸውን የሚጠብቁበት መንገድ አላቸው፡፡...

የሳይነስ እና የአስም በሽታ

የሳይነስ ቁስል ሳይነስ ቁስል ከፊት ጀርባ የሚገኙት በአየር የተሞሉት ቀዳዳዎች (sinuses) መቁሰል (inflammation) ነው፡፡ ይኽ ቁስል በአብዛኛው በራሱ ጊዜ የሚድን ሲሆን በአፍንጫ እና በአይን ዙሪያ...

ማጨስ ክልክል ነው!!!

ውድ አንባቢያን በመቀጠል ሌላውንና በጤናችንና በማህበራዊ ሕይወታችንከፍተኛ የሆነ ጉዳት ስለሚያመጣው፣የሲጋራ ሱስ በሰፊው እንመለከታለን፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 1940 ዎቹ ድረስ ሲጋራን ማጨስ ምንም ጉዳት እንደሌለውናእንዲያውም የቅንጦት እና ክብር መገለጫ ተደርጎ ይታስ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግንበተደረጉ የላብራቶሪ ፍተሸዎች እንደተረጋገጠው ከአንድ ሲጋራ የሚወጣው ጭስወደ 4ሺህ ዓይነት ኬሚካል ንጥረ-ነገሮችን የያዘ፣ ከእንዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹመርዛማነት ያላቸውና 43 ያህል ደግሞ ካንሰርን ሊያመጡ የሚችሉ መሆኑን ነው፡፡ የትምባሆ ቅጠል ማጨስ የተጀመረው በቀድሞዎቹ የአሜሪካ ነዋሪዎች ዘንድ ነው፡፡በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነዋሪዎቹ የትምባሆን ቅጠል በፒፓ (Pipe) መሳይ ዕቃ ሲያጨሱ የተመለከቱት አውሮፓውያን የዚህን ቅጠል ተፈላጊነትበመገንዘብ ትላልቅ የትምባሆ ማሳዎችን በማስፋፋት ለአውሮፓ ገበያ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ይህንንም ተከትሎ በ 17ኛው ክፍለ ዘመን ሲጋራን ማጨስከአውሮፓውያን ባህል ጋር በቀላሉ ለመዋሃድ ቻለ፡፡ በዚያን ወቅት በአብዛኛው ህብረተሰብ ውስጥ የነበረው አስተሳሰብ ሲጋራ ጭንቀትን የሚያስወግድ እና አነቃቂ እንደሆነ ነበር፡፡ እንዲያውምበሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካን መንግሥት ለወታደሮቹ ከሚያከፋፍላቸው የዕለት ራሽን ውስጥም ሲጋራ አንዱ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግንየህክምና ባለሙያዎች በአገልግሎት መስጫ ሆስፒታሎቻቸው የሳንባ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ሕሙማን መብዛት ሲያጋጥማቸው ባደረጓቸውምርምሮች የሲጋራ አጫሾች ከማያጨሱት የበለጠ ለካንሰር እና ሌሎች ተመሳሳይ እክሎች የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በሲጋራ ውስጥ ብዙ ዓይነት ንጥረ -ነገሮች የሚገኙ ሲሆን ዋነኞቹ ታር፣ ካርቦን ሞኖኦክሳይድና ኒኮቲን የተባሉትን ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለሱስአስጣዥነት ዋናኛ ሚና የሚጫወተው ኒኮቲን የተባለው ንጥረ-ነገር ነው፡፡ ኒኮቲን ማት በትምባሆ ቅጠል ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ንጥረ- ነገር ሲሆን አነቃቂነትና ሱስ የማስያዝ ኃይል አለው፡፡ ከቅጠል ውስጥ በሚወጣበት ጊዜምንም ዓይነት ቀለም የሌለው ቢሆንም አየር ሲነካው ወዲያውኑ የቡኒነት ቀለም ይዛል፡፡ ኒኮቲን በጣም መርዛማነት ያለው ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩተባይ ማጥፊያ ኬሚካሎች ውስጥ እንደአንድ ግብአት በመሆን ያገለግላል፡፡ በሲጋ ውስጥ የሚገኘው የኒኮቲን መጠን አነስተኛ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛው ነው፡፡ ከእዚሀም ውስጥ አብዛኛው እሳቱ ፍም ውስጥጠሚቃጠል ስለሆነ ወደ ሰውነታችን የሚገባው በጣም ጥቂቱ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ተጠቃሚውን ሱሰኛ ለማድረግ ከበቂ በላይ ነው፡፡ አንድ ሰው ሲጋራን በሚያጨስበት ጊዜ የኒኮቲን ንጥረ-ነገር በቀጥታ ወደ ሳንባው በመጓዝ ከደሙ ጋር ይቀላቀላል፡፡ ከዚያም በልብ አማካኝነትተረጭቶ ወደ አንጎል ይጓዛል፡፡ ይሄ ሁሉ ሂደት ግን የሚፈጀው ጊዜ ሰባት ሰኮንድ ብቻ ነው፡፡ ቢኮቲን ወደ አንጎል  ከደረሰ በኋላ በአጫሹ ውስጥጊዜዊ የሆነ የእርካታ ስሜትን የሚገጥሩ ኬሚካሎችን በመርጨት እርካታን ስሜት ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ይሄ የእርካታ ስሜት ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እናበደቂቃዎች ውስጥ የኒኮቲኑ መጠን ስለሚቀንስ የእርካታ ስሜቱ እንደገና ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክንያት ሌላ ሲጋራን ለመለኮስ ይገደዳል፡፡ የጊዜክፍተቱ ደግሞ በሱሰኝነት መጠኑ ልክ እያነሰ በመምጣት መቸረሻ ላይ ሲጋራ ከአፋ መነጠል እስኪሳነው ድረስ በሱሱ ይጠመዳል፡፡ ሲጋራን ማጨስ በሰውነት ላይ የተለያዩ ለውጦችን ይፈጥራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አድሬናሊን (Adrenealline) መዘውር በመጨመር አነቃቂሆርሞኖችን መፍጠር፣ የልብ ምት መጨመር. የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የማስመለስና መሳሰሉት ስሜቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ሲጋራን ለማቆምበሚሞከርበት ጊዜ ጎጂ የሆኑ ምልክቶች በሰውነት ላይ ይከሰታሉ፡፡ ከእነዚህም የራስ ምታት፣ የመቅበጥበጥ ስሜት እና ጭንቀትን መጥቀስ እንችላለን፡፡   ሲጋራ እና ጤና   ሰጋራ ማጨስ አብዛኞቹ ሰውነት ክፍሎቻችን ላይ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ በሀገራችን የተደረገ ጠጨባጭ ጥናት ማግኘት ባንችልም በአሜሪካ ብቻበየዓመቱ 442 ሺህ ሰዎች ሲጋ ማጨስ በሚያስከትላቸው ጠንቆች የተነሣ ይሞታሉ፡፡ በሳንባ ካንሰር ከሚሞቱ ሰዎች መካከል ደግሞ 90 ከመቶ  ያህሉበማጨስ የተነሣ የሚሞቱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ኒኮቲን ኢንሱሊን የተባለውንና አላስፈላጊ የስኳር መጠንን ከሰውነታችን የሚስወግደውን የስኳርመጠን እንዳይመነጭ ስለሚያደርገው የስኳር መጠን እንዲጨምር ይሆናል፡፡ ይሄም በደም ውስጥ የስኳር መጠን መብዛት ደግሞ በተዘዋዋሪ የምግብፍላጎትን ይቀንሳል፡፡   በተጨማሪም በሲጋራ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ወደ ሰውነታችን ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ (Monoamine oxidize) ወይንም በአጭሩ (MAO-B)የተሰኘውን ኢንዛይም በሰውነታችን ውስጥ መኖር ደግሞ ዶፓሚን የተሰኘውንና እርካታን አብዘወቶ የመፈለግ ስሜትን የሚቆጣጠር እና የሚገታ ነው፡፡ነገር ግን ሲጋራን በምናጨስበት ወቅት በውስጡ የሚገኘው ንጥረ-ነገር ይህንን (MAO-B) ኢንዛይም ስለሚጠፋ የዶፓሚን ስርጭት ያለ ተቆጣጣሪበመስፋፋት ውስጣችን አምጣ አምጣ እንዲለን ያደርጋል፡፡ በመሆኑም አጫሾች ከሌሎች የማያጨሱ ሰዎች ያነሰ  (MAO-B) ነገር ግን የበለጠዶፓሚን ባለቤት በመሆናቸው እርካታን በመፈለግ ደጋግመው እንዲያጨሱ ይገፋፋሉ፡፡ ሲጋራን የጤና ጠንቅነት በቀጥታ የሚያጨሱት ላይ ብቻሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ሲጋራውን ጭስ ወደ ሰውነታችው የሚገባውን የሚያጨሱሰዎችም (Passive Smokers) ይጎዳል፡፡ በዚህም ሳቢያ አንዳንድ ሰዎች ወደው እና ፈቅደው ሳይን በአጫሾ ዙሪያ በመገኘታቸው የተነሣ የተለያዩዓይነት የመተንፈሻ እና ከልብ ጋር የተያያዙ በሽታዎች ሰላባ ይሆናሉ፡፡   ሲጋራ እና ስነ-ልቦናዊ ትስስር ሲጋራን የሚያጨሰው ሰው በጤናው ለይ ከሚከሰተው ችግር ባሻገር በማኅበራ ህይወቱም ላይ ራሱን የቻለ አሉታዊ ተፅእኖ ይደርስበታል፡፡ በተለይደግሞ ሲጋራ ማጨስ እንደመጥፎ ልማድ በሚታይባት ሃገራችን ችግሩ የጎላ ይሆናል፡፡ ይኸውም አጫሽ የሆነ ሰው በሌሎች ሰዎች ዘንድ ምንም ያህልጥሩ ሰብዕና እና መልካም ባህሪይ ቢኖረውም እንኳን በአጫሽነቱ ብቻ ተቀባይነቱ ይቀንስበታል፡፡ አጫሽ ግለሰብም ቢሆን ከሌሎች የማያጨሱ ሰዎችጋር በሚሆንበት ጊዜ ስለ ሰውነቱ ሽታ፣ ስለ አፋ ተረን እና ስለ ከንፈሩ መጥቆር መሳቀቁ አይቀርም፡፡ በቅርቡ ያሉ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ደግሞ ይሄንንባህሪ የሚቃወሙ ከሆኑ በሚያደርሱበት ወቀሳና ተግሣፅ ከውስጣዊ ፍላጎቱ ጋር ተፃራሪ ስለሚሆንበት አንዱን ለመምረጥ በሚገደድበት ጊጊ ጭንቀትውስጥ ይገባል፡፡ ሲጋራውንም በሚመርጥበት ጊዜ ከሌሎች የመገለል አቋሙን ያራዳል፡፡ ገና ለገና ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ማጨሱ በራሱ ነፃነትንየሚነፍግ እና የድብብቆሽ ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡ ለተተኪው ትውልድም ቦሆን ጎጂ የሆነ ልማድን እናስቀር እያሉ በጎን ደግሞ  ጎጂ የሆነ ልማድንእየፈጠሩ አይቀርም፡፡ አንድ ሰው ሲጋራን ማጨስን ለማቆም በሚሞክርበት ጊዜ አካላዊ ጥገኝነቱን በ 14 ቀናት ውስጥ ሊያስወግድ ቢችልም ከዚሁ ተግባር ጋርየሚኖረውን ስነ-ልቦናዊ ትስስር ለማስወገድ ግን እስከ 4 ዓመት ያህል ጊዜ ሊወስድበት ይችላል፡፡ የዚህም ዋነኛው ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ አጫሾች በጭንቀት (Strees) እና በመረበሽ ስሜት ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ሲያጨሱ ኒኮቲኑ ወደ አንጎልበመሄድ የመረጋጋትን ስት ይፈጥርላቸዋል፡፡ ይሄም ሲጋራን እንደመፍትሄነት እና ሃሳብ ማሠባሰቢያነት የመውሠድ አስተሳሰብ ግለሰቡ ለማቆም ወስኖ ባለበት ሁኔታ ውስጥ እንኳን በውጥረትውስጥ በሚሆንበት ጊዜ ውስጡን ይፈታተነዋል፡፡ ለዚህም ነው አንዳነድ አጫሾች ምግብ በልተው ከጠገቡ በኋላ ማጨስ ሲያምራቸው፣ ሆን ሲጠግብ ሳንባ…” የምትለውን አባባል ሲጠቀሙየሚደመጡት፡፡ ነአሁኑ ወቅት ከሲጋራ ጋር በተያየዘ አሳሳቢ እሆነ የመጣው ደግሞ በከተማ በሚገኙ ታዲጊ ወጣቶች መካከል እየተስተዋለ የመጣውየሲጋራ አጫሽነት መስፋፋት ነው፡፡ አብዛኛውን አዳጊ ወጣት በጉርምስና ጊዜ ላይ በሚደርስበት ወቅት በአንድ ወይም በብዙ አጋጣሚዎች ሲጋራንማጨሱ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወጣቱ ትውልድ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለውን ችግር ሳይሆን የአራድነት፣ የነፃነት እና የትልቅነት ምልክት አድርጎመመልከቱ ነው፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ ከታላላቆቻቸው እንደሚመለከቱት ሲጋራን ማጨስ የአዋዊነት መገለጫ አድረጊው የሚወስዱትም አሉ፡፡   የሲጋራ አጫሽነትን ለመቀነስ ሀገራት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሲጋራ አምራች ድርጅቶች ምርቶቻቸውንበቴሌቪዥን እንዳያስተዋውቁ ማገድ፣ ህዝብ በሚሰበስባቸው እና ዝግ በሆኑቦታዎች ላይ ሲጋራ ማጨስን መከላከል እና በሲጋራ ፓኮዎች ለይ ጉዳቱንበተመለከተ በግልፅ እንዲያስቀምጡ የሚስገድዱ ሕግጋትን ሥራ ላይ ማዋል ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን በየዓለም ሀገራቱ ያሉ የሲጋራሱሰኞች ብዛት ከፍተኛ ነው፡፡ በቀላሉ መካላከል እየተቻለ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የሞት ቁጥር በማስመዝገብ ላይ ከሚገኙ በሽታዎች ግንባር ቀደሙንስፍራ የሚይዘው የሲጋራ አጫሽነት ነው፡፡   ከሲጋራ ሱስ ለመላቀቅ ከሁሉም የሚበልጠው እና ቀዳሚ የሆነው ተግባር መወሠን ነው፡፡ ነገር ግን ይሄ ብቻውን በቂ አይደለም ፡፡ ምክንያቲም ብዚዎች ሲጋራን ለማቆምውሳኔ ላይ ደርሰው ተግባ ላይ ስለሌሉበት አሁንም በተመሳሳይ ቦታ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ከውሳኔው በኋላ ወደ ትግበራው መፍጠን ተገቢ ነው፡፡ በዚህላይ ትኩረት መስጠት ያለብን ባሕሪየቶቻችን በራሳችን ስት ብቻ ላይ የተመረኮዙ ሳይሆን ሌሎች በሕይመታችን ውስጥ ቦታ የምነስጣቸውን ስሜትግንዛቤ ውስጥ መክተት አለብን፡፡ ለምሳሌ ፡- አንተ የሲጋራ ማጨስ ልማድህ የሚያመጣብህን ጉዳት አምነህ ተቀብለህ ብትቀጥልብህ ጉዳት አምነህ ተቀብለህብትቀጥልበትም ነገር ግን ቤተሰቦችህ እንደታደርገው የመይፈልጉት ቢሆን እና በጤናቸውም ላይ እክል የሚፈጥር ቢሆን ምን ማድረግይኖርብሃል? ማዳመጫዬ ድፍተን ነው ብለህ የራስህን ስት ብቻ ታስተናግዳለህ? ወይንስ የምትወዳቸውን ቤተሰቦችህን ከምትወደውሲጋራ በማስበለጥ ይህንን ባህሪህን መተው? ሌላ ደግሞ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የሚሰጥህን ጥቅም በዝርዝርነማስመጥ ብታመዛዝናቸው ለመወሰን ሊያመችህ ይችላል፡፡   በተጨማሪም ጠንካራ ከሆንክና ራስህን መቆጣጣት እንደምትችል ካመንክ ከነአካቴው በአንድ ገዚ መተው፡፡ አይ! እንደርሱ እንኳ ይከብደኛል የምትል ከሆነ ደግሞ በቀን ውስጥ የምታጨሰውን ሲጋራ ቁጥር ቀስ በቀስ በመቀነስ መሞከር ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ በቀን አንድ ፓኮ የምትጨርስ ቢኆንዳ ግማስ፣ ከግማሱዳ ሩብ እያልክ መቀነስ ትችላለህ፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ታጨስባቸው የነበሩ ሰዓቶችን በመቀየር ልማዳዊ ጥገኝነትህን መቀነስ ይቻለል፡፡ ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ምሳ በልተህ ወዲያውኑየምታጨስ ከሆነ አሁን ደግሞ ትንሽ በመ፣ዘግየት ሞክር… ሁልጊዜ እንታጨስ ከሚያደርጉህ ሁኔታዎች ራስህን ማራቅ ሲጋራን በማጨስ የምታከናውናቸውን ተግባራት በሌላ ተለዋዋጭ ልምዶች መቀየርም ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ለመተኛት ስትል የምታዐስ ከሆነ ቆሎበመብላት ሞክረው፡፡ እንደዚህ እያደረግክ ጎጂ ከሆነው ልማድህ በመላቀቅ በሌላ የተሸለ ልማድ መተካት አማራጭ ነው፡፡   ሌላ ደግሞ ሲጋራን ማጨስ በሚያሰኝህ ሰጫት ጣፋጭ ነገሮችን መጠቀምም አምጣ አምጣ የሚለውን ስሜት ለማዘናጋት ጠቃሚ ነው፡፡  

ማጨስ ለአዕምሮ ህመም ያጋልጣል

ሲጋራ ማጨስ ለሳምባ ካንሰርና ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ የጥናት ውጤቶች አሳይተዋል፡፡ ሰሞኑን በዩናይትድ ስቴትስ ይፋ የተደረገው አንድ የጥናት ውጤት በበኩሉ በየዕለቱ...

ደረቅ ሳልን ለመከላከል በቤት ውስጥ በቀላሉ የምናዘጋጃቸው መድሃኒቶች

ደረቅ ሳልን ለመከላከል በቤት ውስጥ በቀላሉ የምናዘጋጃቸው መድሃኒቶች። ደረቅ ሳል ጉሮሮዎን ካሰመሞትና በእንቅልፍ ሰዓት የሚያስቸግሮት ከሆነ እነዚህን በቀላሉ የምናዘጋጃቸውን ነገሮች በመጠቀም ማከም እንደምንችል በተለያዩ ጊዜያቶች...