የአልኮል መጠጦችና እፆችና ወሲብ

በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ‹‹የወሲብ ፍላጎትን ያነሳሳሉ›› በሚል እምነት ተዘውትረው ጥቅም ላይ የሚውሉ አልኮል መጠጦችና ሌሎች ሱስ አስያዥ እፆች ሰዎች ከወሲብ ማግኘት የሚገባቸውን እርካታ...

“በመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ… መጠን አትለፋ…”

አልኮል መጠጥ ሱስ ራሱን የቻለ በሽታ ሲሆን ፣ ዋነኛመገለጫውም ከፍተኛ የሆነ የአልኮል መጠጥ ፍላጎት ነው፡፡በዚህም ሱስ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የመጠጥ ፍላጎታቸው ምንምያህል በቤተሰባቸው፣ በሥራቸውና በጤናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳትየሚያመጣ ቢሆንም እንኳን ለማቆም ሲቸገሩ ይታያሉ፡፡ የአልኾልጥገኝነት በእያንዳዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ይገለጣል፡፡ ነገርግን ሁሉንም የአልኾል ሱሶች አንድ የሚያደርጓቸውን ተመሳሳይምልክቶችንም ማውጣት ይቻላል፡፡ እነዚህም፡- ለመጠጣት የሚያሳሳ ከፍተኛ ፍላጎት ፣ ምንምያህል ጉዳት ቢያደርስባቸውም መጠጥን በተመለከተ  ራስን የመግታትም ሆነ የመቆጣጠር ችግር፣ አንዴ ከጀመሩ በኋላ ደግለማቆም ያለመቻል፣ እንዲሁም ደግሞ አልክኾል...

በትዳር መካከል ጸብ ሲነሳ እንዴት መፍታት ይቻላል?

ከሊሊ ሞገስ ትዳር በባህር ወይም ውቅያኖስ ውስጥ ያለችን ትልቅ መርከብ ይመስላል፡፡ መርከቧ ረጅም ርቀት እንደመጓዟ ለተለያዩ አየር ፀባይ ለውጦች መጋለጧ አይቀሬ ነው፡፡ ፀጥታና ሰላም የሰፈነበት...

ሱስን ለማቆም የሚጋጥሙ መሰናክሎች

“አዲስ ለተወለደው ልጃችን ጤንነት ስል ማጨስ ለማቆም ወሰንኩ። በመሆኑም ‘ማጨስ ክልክል ነው’ የሚል ምልክት ቤታችን ውስጥ ለጠፍኩ። ልክ ከአንድ ሰዓት በኋላ የኒኮቲን ሱሴ ውስጤን...

ሺሻ የማጨስ አደጋዎች –

መቀመጫውን በአሜሪካው ጆርጂያ ክፍለ ግዛት ፣ አትላንታ ከተማ ያደረገው በአለም ታዋቂው የጤና የምርምር ተቋም Centers for Disease Control and Prevention (CDC) ሺሻ የማጨስን አደገኛነት...

ማጨስ ክልክል ነው!!!

ውድ አንባቢያን በመቀጠል ሌላውንና በጤናችንና በማህበራዊ ሕይወታችንከፍተኛ የሆነ ጉዳት ስለሚያመጣው፣የሲጋራ ሱስ በሰፊው እንመለከታለን፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 1940 ዎቹ ድረስ ሲጋራን ማጨስ ምንም ጉዳት እንደሌለውናእንዲያውም የቅንጦት እና ክብር መገለጫ ተደርጎ ይታስ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግንበተደረጉ የላብራቶሪ ፍተሸዎች እንደተረጋገጠው ከአንድ ሲጋራ የሚወጣው ጭስወደ 4ሺህ ዓይነት ኬሚካል ንጥረ-ነገሮችን የያዘ፣ ከእንዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹመርዛማነት ያላቸውና 43 ያህል ደግሞ ካንሰርን ሊያመጡ የሚችሉ መሆኑን ነው፡፡ የትምባሆ ቅጠል ማጨስ የተጀመረው በቀድሞዎቹ የአሜሪካ ነዋሪዎች ዘንድ ነው፡፡በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነዋሪዎቹ የትምባሆን ቅጠል በፒፓ (Pipe) መሳይ ዕቃ ሲያጨሱ የተመለከቱት አውሮፓውያን የዚህን ቅጠል ተፈላጊነትበመገንዘብ ትላልቅ የትምባሆ ማሳዎችን በማስፋፋት ለአውሮፓ ገበያ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ይህንንም ተከትሎ በ 17ኛው ክፍለ ዘመን ሲጋራን ማጨስከአውሮፓውያን ባህል ጋር በቀላሉ ለመዋሃድ ቻለ፡፡ በዚያን ወቅት በአብዛኛው ህብረተሰብ ውስጥ የነበረው አስተሳሰብ ሲጋራ ጭንቀትን የሚያስወግድ እና አነቃቂ እንደሆነ ነበር፡፡ እንዲያውምበሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካን መንግሥት ለወታደሮቹ ከሚያከፋፍላቸው የዕለት ራሽን ውስጥም ሲጋራ አንዱ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግንየህክምና ባለሙያዎች በአገልግሎት መስጫ ሆስፒታሎቻቸው የሳንባ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ሕሙማን መብዛት ሲያጋጥማቸው ባደረጓቸውምርምሮች የሲጋራ አጫሾች ከማያጨሱት የበለጠ ለካንሰር እና ሌሎች ተመሳሳይ እክሎች የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በሲጋራ ውስጥ ብዙ ዓይነት ንጥረ -ነገሮች የሚገኙ ሲሆን ዋነኞቹ ታር፣ ካርቦን ሞኖኦክሳይድና ኒኮቲን የተባሉትን ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለሱስአስጣዥነት ዋናኛ ሚና የሚጫወተው ኒኮቲን የተባለው ንጥረ-ነገር ነው፡፡ ኒኮቲን ማት በትምባሆ ቅጠል ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ንጥረ- ነገር ሲሆን አነቃቂነትና ሱስ የማስያዝ ኃይል አለው፡፡ ከቅጠል ውስጥ በሚወጣበት ጊዜምንም ዓይነት ቀለም የሌለው ቢሆንም አየር ሲነካው ወዲያውኑ የቡኒነት ቀለም ይዛል፡፡ ኒኮቲን በጣም መርዛማነት ያለው ከመሆኑ የተነሳ የተለያዩተባይ ማጥፊያ ኬሚካሎች ውስጥ እንደአንድ ግብአት በመሆን ያገለግላል፡፡ በሲጋ ውስጥ የሚገኘው የኒኮቲን መጠን አነስተኛ ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛው ነው፡፡ ከእዚሀም ውስጥ አብዛኛው እሳቱ ፍም ውስጥጠሚቃጠል ስለሆነ ወደ ሰውነታችን የሚገባው በጣም ጥቂቱ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ተጠቃሚውን ሱሰኛ ለማድረግ ከበቂ በላይ ነው፡፡ አንድ ሰው ሲጋራን በሚያጨስበት ጊዜ የኒኮቲን ንጥረ-ነገር በቀጥታ ወደ ሳንባው በመጓዝ ከደሙ ጋር ይቀላቀላል፡፡ ከዚያም በልብ አማካኝነትተረጭቶ ወደ አንጎል ይጓዛል፡፡ ይሄ ሁሉ ሂደት ግን የሚፈጀው ጊዜ ሰባት ሰኮንድ ብቻ ነው፡፡ ቢኮቲን ወደ አንጎል  ከደረሰ በኋላ በአጫሹ ውስጥጊዜዊ የሆነ የእርካታ ስሜትን የሚገጥሩ ኬሚካሎችን በመርጨት እርካታን ስሜት ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ይሄ የእርካታ ስሜት ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እናበደቂቃዎች ውስጥ የኒኮቲኑ መጠን ስለሚቀንስ የእርካታ ስሜቱ እንደገና ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክንያት ሌላ ሲጋራን ለመለኮስ ይገደዳል፡፡ የጊዜክፍተቱ ደግሞ በሱሰኝነት መጠኑ ልክ እያነሰ በመምጣት መቸረሻ ላይ ሲጋራ ከአፋ መነጠል እስኪሳነው ድረስ በሱሱ ይጠመዳል፡፡ ሲጋራን ማጨስ በሰውነት ላይ የተለያዩ ለውጦችን ይፈጥራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አድሬናሊን (Adrenealline) መዘውር በመጨመር አነቃቂሆርሞኖችን መፍጠር፣ የልብ ምት መጨመር. የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የማስመለስና መሳሰሉት ስሜቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ሲጋራን ለማቆምበሚሞከርበት ጊዜ ጎጂ የሆኑ ምልክቶች በሰውነት ላይ ይከሰታሉ፡፡ ከእነዚህም የራስ ምታት፣ የመቅበጥበጥ ስሜት እና ጭንቀትን መጥቀስ እንችላለን፡፡   ሲጋራ እና ጤና   ሰጋራ ማጨስ አብዛኞቹ ሰውነት ክፍሎቻችን ላይ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ በሀገራችን የተደረገ ጠጨባጭ ጥናት ማግኘት ባንችልም በአሜሪካ ብቻበየዓመቱ 442 ሺህ ሰዎች ሲጋ ማጨስ በሚያስከትላቸው ጠንቆች የተነሣ ይሞታሉ፡፡ በሳንባ ካንሰር ከሚሞቱ ሰዎች መካከል ደግሞ 90 ከመቶ  ያህሉበማጨስ የተነሣ የሚሞቱ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ኒኮቲን ኢንሱሊን የተባለውንና አላስፈላጊ የስኳር መጠንን ከሰውነታችን የሚስወግደውን የስኳርመጠን እንዳይመነጭ ስለሚያደርገው የስኳር መጠን እንዲጨምር ይሆናል፡፡ ይሄም በደም ውስጥ የስኳር መጠን መብዛት ደግሞ በተዘዋዋሪ የምግብፍላጎትን ይቀንሳል፡፡   በተጨማሪም በሲጋራ ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ወደ ሰውነታችን ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ (Monoamine oxidize) ወይንም በአጭሩ (MAO-B)የተሰኘውን ኢንዛይም በሰውነታችን ውስጥ መኖር ደግሞ ዶፓሚን የተሰኘውንና እርካታን አብዘወቶ የመፈለግ ስሜትን የሚቆጣጠር እና የሚገታ ነው፡፡ነገር ግን ሲጋራን በምናጨስበት ወቅት በውስጡ የሚገኘው ንጥረ-ነገር ይህንን (MAO-B) ኢንዛይም ስለሚጠፋ የዶፓሚን ስርጭት ያለ ተቆጣጣሪበመስፋፋት ውስጣችን አምጣ አምጣ እንዲለን ያደርጋል፡፡ በመሆኑም አጫሾች ከሌሎች የማያጨሱ ሰዎች ያነሰ  (MAO-B) ነገር ግን የበለጠዶፓሚን ባለቤት በመሆናቸው እርካታን በመፈለግ ደጋግመው እንዲያጨሱ ይገፋፋሉ፡፡ ሲጋራን የጤና ጠንቅነት በቀጥታ የሚያጨሱት ላይ ብቻሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ሲጋራውን ጭስ ወደ ሰውነታችው የሚገባውን የሚያጨሱሰዎችም (Passive Smokers) ይጎዳል፡፡ በዚህም ሳቢያ አንዳንድ ሰዎች ወደው እና ፈቅደው ሳይን በአጫሾ ዙሪያ በመገኘታቸው የተነሣ የተለያዩዓይነት የመተንፈሻ እና ከልብ ጋር የተያያዙ በሽታዎች ሰላባ ይሆናሉ፡፡   ሲጋራ እና ስነ-ልቦናዊ ትስስር ሲጋራን የሚያጨሰው ሰው በጤናው ለይ ከሚከሰተው ችግር ባሻገር በማኅበራ ህይወቱም ላይ ራሱን የቻለ አሉታዊ ተፅእኖ ይደርስበታል፡፡ በተለይደግሞ ሲጋራ ማጨስ እንደመጥፎ ልማድ በሚታይባት ሃገራችን ችግሩ የጎላ ይሆናል፡፡ ይኸውም አጫሽ የሆነ ሰው በሌሎች ሰዎች ዘንድ ምንም ያህልጥሩ ሰብዕና እና መልካም ባህሪይ ቢኖረውም እንኳን በአጫሽነቱ ብቻ ተቀባይነቱ ይቀንስበታል፡፡ አጫሽ ግለሰብም ቢሆን ከሌሎች የማያጨሱ ሰዎችጋር በሚሆንበት ጊዜ ስለ ሰውነቱ ሽታ፣ ስለ አፋ ተረን እና ስለ ከንፈሩ መጥቆር መሳቀቁ አይቀርም፡፡ በቅርቡ ያሉ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ደግሞ ይሄንንባህሪ የሚቃወሙ ከሆኑ በሚያደርሱበት ወቀሳና ተግሣፅ ከውስጣዊ ፍላጎቱ ጋር ተፃራሪ ስለሚሆንበት አንዱን ለመምረጥ በሚገደድበት ጊጊ ጭንቀትውስጥ ይገባል፡፡ ሲጋራውንም በሚመርጥበት ጊዜ ከሌሎች የመገለል አቋሙን ያራዳል፡፡ ገና ለገና ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ማጨሱ በራሱ ነፃነትንየሚነፍግ እና የድብብቆሽ ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡ ለተተኪው ትውልድም ቦሆን ጎጂ የሆነ ልማድን እናስቀር እያሉ በጎን ደግሞ  ጎጂ የሆነ ልማድንእየፈጠሩ አይቀርም፡፡ አንድ ሰው ሲጋራን ማጨስን ለማቆም በሚሞክርበት ጊዜ አካላዊ ጥገኝነቱን በ 14 ቀናት ውስጥ ሊያስወግድ ቢችልም ከዚሁ ተግባር ጋርየሚኖረውን ስነ-ልቦናዊ ትስስር ለማስወገድ ግን እስከ 4 ዓመት ያህል ጊዜ ሊወስድበት ይችላል፡፡ የዚህም ዋነኛው ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ አጫሾች በጭንቀት (Strees) እና በመረበሽ ስሜት ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ሲያጨሱ ኒኮቲኑ ወደ አንጎልበመሄድ የመረጋጋትን ስት ይፈጥርላቸዋል፡፡ ይሄም ሲጋራን እንደመፍትሄነት እና ሃሳብ ማሠባሰቢያነት የመውሠድ አስተሳሰብ ግለሰቡ ለማቆም ወስኖ ባለበት ሁኔታ ውስጥ እንኳን በውጥረትውስጥ በሚሆንበት ጊዜ ውስጡን ይፈታተነዋል፡፡ ለዚህም ነው አንዳነድ አጫሾች ምግብ በልተው ከጠገቡ በኋላ ማጨስ ሲያምራቸው፣ ሆን ሲጠግብ ሳንባ…” የምትለውን አባባል ሲጠቀሙየሚደመጡት፡፡ ነአሁኑ ወቅት ከሲጋራ ጋር በተያየዘ አሳሳቢ እሆነ የመጣው ደግሞ በከተማ በሚገኙ ታዲጊ ወጣቶች መካከል እየተስተዋለ የመጣውየሲጋራ አጫሽነት መስፋፋት ነው፡፡ አብዛኛውን አዳጊ ወጣት በጉርምስና ጊዜ ላይ በሚደርስበት ወቅት በአንድ ወይም በብዙ አጋጣሚዎች ሲጋራንማጨሱ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ወጣቱ ትውልድ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለውን ችግር ሳይሆን የአራድነት፣ የነፃነት እና የትልቅነት ምልክት አድርጎመመልከቱ ነው፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ ከታላላቆቻቸው እንደሚመለከቱት ሲጋራን ማጨስ የአዋዊነት መገለጫ አድረጊው የሚወስዱትም አሉ፡፡   የሲጋራ አጫሽነትን ለመቀነስ ሀገራት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሲጋራ አምራች ድርጅቶች ምርቶቻቸውንበቴሌቪዥን እንዳያስተዋውቁ ማገድ፣ ህዝብ በሚሰበስባቸው እና ዝግ በሆኑቦታዎች ላይ ሲጋራ ማጨስን መከላከል እና በሲጋራ ፓኮዎች ለይ ጉዳቱንበተመለከተ በግልፅ እንዲያስቀምጡ የሚስገድዱ ሕግጋትን ሥራ ላይ ማዋል ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን በየዓለም ሀገራቱ ያሉ የሲጋራሱሰኞች ብዛት ከፍተኛ ነው፡፡ በቀላሉ መካላከል እየተቻለ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የሞት ቁጥር በማስመዝገብ ላይ ከሚገኙ በሽታዎች ግንባር ቀደሙንስፍራ የሚይዘው የሲጋራ አጫሽነት ነው፡፡   ከሲጋራ ሱስ ለመላቀቅ ከሁሉም የሚበልጠው እና ቀዳሚ የሆነው ተግባር መወሠን ነው፡፡ ነገር ግን ይሄ ብቻውን በቂ አይደለም ፡፡ ምክንያቲም ብዚዎች ሲጋራን ለማቆምውሳኔ ላይ ደርሰው ተግባ ላይ ስለሌሉበት አሁንም በተመሳሳይ ቦታ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ከውሳኔው በኋላ ወደ ትግበራው መፍጠን ተገቢ ነው፡፡ በዚህላይ ትኩረት መስጠት ያለብን ባሕሪየቶቻችን በራሳችን ስት ብቻ ላይ የተመረኮዙ ሳይሆን ሌሎች በሕይመታችን ውስጥ ቦታ የምነስጣቸውን ስሜትግንዛቤ ውስጥ መክተት አለብን፡፡ ለምሳሌ ፡- አንተ የሲጋራ ማጨስ ልማድህ የሚያመጣብህን ጉዳት አምነህ ተቀብለህ ብትቀጥልብህ ጉዳት አምነህ ተቀብለህብትቀጥልበትም ነገር ግን ቤተሰቦችህ እንደታደርገው የመይፈልጉት ቢሆን እና በጤናቸውም ላይ እክል የሚፈጥር ቢሆን ምን ማድረግይኖርብሃል? ማዳመጫዬ ድፍተን ነው ብለህ የራስህን ስት ብቻ ታስተናግዳለህ? ወይንስ የምትወዳቸውን ቤተሰቦችህን ከምትወደውሲጋራ በማስበለጥ ይህንን ባህሪህን መተው? ሌላ ደግሞ ሲጋራ ማጨስ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የሚሰጥህን ጥቅም በዝርዝርነማስመጥ ብታመዛዝናቸው ለመወሰን ሊያመችህ ይችላል፡፡   በተጨማሪም ጠንካራ ከሆንክና ራስህን መቆጣጣት እንደምትችል ካመንክ ከነአካቴው በአንድ ገዚ መተው፡፡ አይ! እንደርሱ እንኳ ይከብደኛል የምትል ከሆነ ደግሞ በቀን ውስጥ የምታጨሰውን ሲጋራ ቁጥር ቀስ በቀስ በመቀነስ መሞከር ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ በቀን አንድ ፓኮ የምትጨርስ ቢኆንዳ ግማስ፣ ከግማሱዳ ሩብ እያልክ መቀነስ ትችላለህ፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ታጨስባቸው የነበሩ ሰዓቶችን በመቀየር ልማዳዊ ጥገኝነትህን መቀነስ ይቻለል፡፡ ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ምሳ በልተህ ወዲያውኑየምታጨስ ከሆነ አሁን ደግሞ ትንሽ በመ፣ዘግየት ሞክር… ሁልጊዜ እንታጨስ ከሚያደርጉህ ሁኔታዎች ራስህን ማራቅ ሲጋራን በማጨስ የምታከናውናቸውን ተግባራት በሌላ ተለዋዋጭ ልምዶች መቀየርም ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ለመተኛት ስትል የምታዐስ ከሆነ ቆሎበመብላት ሞክረው፡፡ እንደዚህ እያደረግክ ጎጂ ከሆነው ልማድህ በመላቀቅ በሌላ የተሸለ ልማድ መተካት አማራጭ ነው፡፡   ሌላ ደግሞ ሲጋራን ማጨስ በሚያሰኝህ ሰጫት ጣፋጭ ነገሮችን መጠቀምም አምጣ አምጣ የሚለውን ስሜት ለማዘናጋት ጠቃሚ ነው፡፡  

ሱስና መፍትሄዎቹ

አንድ ስኒ ቡና ለንቃት ሁለትና ሶስት ድብን ብሎ በመተኛት የካፌይን ተፅዕኖ ሲገለፅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስራ፣ ጥናትንና በአጠቃላይ ለነቃ ውሎ ስንል ካፌይን ብለን የምንጠራውን ኬሚካል የያዙ...

የአልኮል መጠጦችና እፆችና ወሲብ የጤና ችግሮች

  በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ‹‹የወሲብ ፍላጎትን ያነሳሳሉ›› በሚል እምነት ተዘውትረው ጥቅም ላይ የሚውሉ አልኮል መጠጦችና ሌሎች ሱስ አስያዥ እፆች ሰዎች ከወሲብ ማግኘት የሚገባቸውን እርካታ...

የአልኮል መጠጥን አብዝቶ በመጠጣት ምክንያት የሚጎዱ የሰውነት ክፍሎች

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም) 1) ልብ ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ ማዘውተር የልብ ጡንቻዎችን በማዳከም የደም ፍሰት መዛባትን ያሰከትላል፡፡ በአልኮል መጠጥ ብዛት የሚከሰት የልብ ሕመም የትንፋሽ ማጠር፤ የተዛባ...

ወጣቶች ለካንሰር ከሚዳርጉ ሱሶች ራሳቸውን በማራቅ የበሽታውን መስፋፋት እንዲገቱ አሶሴሽኑ ጠየቀ

ወጣቶች ለካንሰር ከሚዳርጉ ሱሶች ራሳቸውን በማራቅ የበሽታውን መስፋፋት መግታት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን አሳሰበ፡፡ በአዲስ አበባ የካንሰር በሽታን የመመዝገብ ሥራም ተጀምሯል፡፡የአሶሰሴሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር...

ጫት መቃም ከሚያስከትላቸው ጉዳቶት ውስጥ ( የወንድነት ስሜት ያጠፋል/ያሳጣል/ )

ጨጓራ ተልጦ ጥርስ እየረገፈ የለጋነት እድሜ በከንቱ አለፈ፡፡ በጤና በአካል ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ጫት ለጤና ጠንቅነቱ ለሥነ-ምግባር ብልሹነቱ መንስኤነቱ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ላይ ጎጂነቱ ማንም ሠው የሚያውቀውና...

ለትርፍ ሲባል እንዴት መርዝ ይጨሳል? ሳያናይድ ተገኘበት! 

የኤሌክትሪክ ሲጋራና መዘዙን በህግ እሰኪለከል ድረስ እኔም ከመምከር አልቆጠብም፡፡ የምትከታተሉ ሰዎች ካላችሁ፣ ህዝቡም እየነቃ፣ መንግሥትም ጠበቅ ያለ ርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ ለመሆኑ፣ የዚህ ቬፒንግ ወይም...

ስለ ጫት ጎጂነት ከብዙ በጥቂቱ

በጫት ተክል ወይም ቅጠል ውሰጥ ብዙ የሆኑ ንጥረነግሮች (ኪሚካሎች) ሲኖሩ፤ በጤንነት ላይ ጉዳት ያሰከትላሉ ተብለው በይበልጥ የሚታመንባቸው ሶሰት ናቸው። እነሱም ካቲኖን፣ ካቲን እና ታኒንሰ...

አደገኛ እፆችና የሚያስከትሉት የጤና ቀውስ

የአደገኛ እጾች መዘዝ የልብ በሽታየአዕምሮ መዛባትየእንቅልፍ እጦትተስፋ የመቁረጥ ስሜትጭንቀትና መደበትራስን የማጥፋት ፍላጎት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሣይኮሎጂ ትምህርት ዘርፍ የአራተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ነው ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ...

ሲጋራ የውበትና የገፅታ፣ የስያሜና የአርማ እገዳ ተጣለበት

ጤናንና ህይወትን ለመታደግ ነው ተብሏል ሲጋራ ማጨስ ለከፍተኛ የጤና አደጋ፣ ባስ ሲልም ለህልፈት እንደሚዳርግ ማንም ሊክድ አይችልም። እንዲያም ሆኖ ከወደ አየርላንድ የተሰማው አዲስ እገዳ ክፉኛ...

ስለ ጫት ምን ያውቃሉ – ከዘለቀ ወ.አ

  በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውሰጥ በየከተማው አሰተዉሎ ለሚመለከትው ሁሉ ብዙ ሰዎች ጫት አንደሚቅሙ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። በየቦታው የጫት ምርት ጨምራል፤ የመሸጫና የመቃሚያ ሱቆች በብዛት ተከፍተዋል፡...

የወሲብ ሱስ (Sex Addiction)

  ብዛቻችን ሱስ ሱባ የምናያይዛ ከሲጋራ ከመጠጥና ከመሣሰሉት ጋር ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ የተለያዩ የአደነዛዥ ዕፆችን ተጠቃሚነት ሱስ በዋናነትየሚጠቀስ ሱስ ነው፡፡ ከዚያ በተለየ ወሲብንስ ብናይ ለመሆኑ የወሲብ ሱስ አለው? ብለን ብንጠይቅ መልሳችን አንድና አንድ ነው እሱም “አዎ!የወሲብ ሱስ አለው፡፡” ነው፡፡ ልክ እንደ ሲጋራ፣ እንደ አልክሆል፣ ጫት አሊያም ቁማር መጫወት ከመጠን ሲያልፍ እና ግለሰቡ ራሱን መቆጣጠርሲያቅተው ሱስ ሆነበት እንደምንለው ሁሉ ወሲባዊነት ከገደቡ በላ አልፎ አዕምሮንና ድርጊትን የሚቆጣጠርበት ደረጃ ላይ ሲደርስ የወሲብ ሱሰኝነትደረጃ ላይ ሲደርስ የወሲብ ሱሰኝነት ብለን እንጠራዋን፡፡   ይሄም ሱስ በማህበረሰቡ ላይ በሰፊው የተንሰራፋና ሁሉም ሰው በልቡ እያወቀው ከሌሎቹ የሱስ ዓይነቶች ባነሰ እውቅና የሚሠጠው እና እንደቀልድ ተደርጎ የሚወራ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የሴሰኝነት ባህሪ በተለያየ መንገድ ሊገደጋጋሚ የፖርኖግራፊ ምስል እና ቪዲዮዎችን በመመልከት፣ ከተለያዩሰዎች ጋር ግንኙነት በመፈጸም ፣ ወደ ሴተኛ አዳሪዎች አብዝቶ በመሄድ፣ ስለ ወሲብ በብዛት  በማሰብ እንዲሁም በማውራት እና በተደጋጋሚ ወሲብንበመፈጸም ሊሆን ይችላል፡፡   ለመሆኑ የወሲብ ሱስ ምንድነው ?   ወሲብ ማለት ከሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ስሜቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን፣ በአግባቡሲጠቀሙበት ደግሞ ትውልድን ከመተካት ባሻገር ታላቅ የሆነ ደስታን የሚሰጥ ስሜትነው፡፡ ይኸውም ማንኛውም ነገር ከመጠን በላ ሲበዛም ሆነ ከሚገባው መጠን ሲያንስችግር እንደሚያስከትለው ሁሉ ወሲባዊ ባህሪይም ከመጠን ሲያንስም ሆነ ከመጠን በላይሲያልፍ የግለሰቡን ጤንነት እና ማህበራዊ ኑሮ ያቃውሳል፡፡ ሴሰኝነት ከሃሳ ወደ ድርጊትየሚሸጋገር ባሪ ነው፡፡ ይህም ባህሪይ በአንድ ስው አዕምሮ ውስጥ ገዥ ሲሆን፣ መላውየህይወት ኃይሉ ልቅ በሆኑ የወሲብ ሃሳቦች ተሞልቶ ወደ ድርጊት ሲወጣ ሰዎችገንዘባቸውን ፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውን ፣ እውቀታቸውን፣ ኃላፊነታቸውንናተፈጥሮሯቸውን ሳይቀር ልቅ ለሆነ የወሲብ ስሜታቸው ማርኪያ ይጠቀሙበታል፡፡በአብዛኛው ከተቃራኒጾታዎች ጋር ያላቸው ግንኙነትና ሃሳብም ወደ ወሲብ ስሜት ዝቅይላል፡፡   የወሲብ ሱሰኝነት በግለሰቡ ላይ በሚያደርሰው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ማበራዊ ግንኙነት በመላሸት እንዲሁምበሚፈጠረው ገለልተኝነት ከሌሎች ሱሶች ጋ ተመሳሳይ ሲያደርገው የሚለይበት ደግሞ ሳይጫወትም ሆነ አልክሆል ሳይጠጣ መኖር የሚቻል ሲሆንወሲብ መፈጸምን ግን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ አንዱ አካል በመሆኑ የተነሣ እስከነአካቴው ይቅር የሚሉት አይደለም፡፡   በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች በሁኔታዎች ተገደውም ሆነ በራሳቸው ምርጫ ከወሲባዊ ባህሪይ ርቀው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ጤናማ የሆነ ሰው ግን ወሲባዊፍላጎት ይኖረዋል፡፡ እንዳውም የወሲብ ፍላጎት አለመኖር ወይም መቀነስ በራሱ ችግር ነው፡፡   ወሲባዊ ሱስ ማለት እየጨመረ የሚሄድ ተደጋጋሚ በሆነ የወሲብ ሃሳብ እና ድርጊት የሚገለጥ ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ነው፡፡ ለአንዳንድ የወሲብ ሱሰኞችይሄ ችግር በተደጋጋሚ ፖርኖግራፊ ከመመልከት፣ ወሲብ ከመፈፀም ወይም በተደጋጋሚ ወሲብ መፈፀም ከመፈለግ ላያልፍ ይችላል፡፡ ይሄ ጥገኝነትደግሞ ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ተደማምሮ ከፍተኛ የአዕምሮ ቀውስ ሲያስከትልና ወደ አደገኛ የሆነ ከራስም አልፎ ሌሎችን ሰዎች ወደ ሚጎዳእንደአስገድዶ መድፈር በህፃናት ላይ ወሲባዊ ጥቃትን መፈፀምና ወደ መሳሰሉት ድርጊት ሊሸጋገር ይችላል፡፡   ሁሉንም ባህሪያት አንድ የሚያደርጋቸው ሁሉም የሚፈፁሙት በድብቅ ስለሚሆን በቅርበት ባሉ ሰዎች ሁሉ የመታወቅ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡   በዚህ ሱስ ውስጥ የሚገኝ ሰው አዕምሮው ልቅ የሆነ ወሲብን መፈፀም ምግብን እንደመመገብ አስፈላጊ እንደሆነ ስለሚቀበለው አብዛኛውን ጊዜውንከወሲብ ጋር በተያያዙ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ይወጠራል፡፡ እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ወሲብ መፈፀም ትልቁ የእርካታ ምንጫቸው እንደሆነ ቢያስቡምየተቃራኒ ጾታ ግንኙነታቸው ፍቅር የጎደለው እና እንደ መጠቀሚያ ቁስነት የመቁጠር ያህል ነው፡፡ ወሲባዊ ስሜታቸውም በሚነሳሳበትም ጊዜራሳቸውን አደጋ ውስጥ በሚከት ሁኔታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በዚህም የተነሣ ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት በሚመጡ በሽዎች የመያዛቸው ዕድል ሰፊነው፡፡   እንዲሁም በወሲብ ሱስ የተጠመዱ ሰዎች ወሲብን እርካታን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ከመጥፎ ስት ለመሸሽ፣ ፍርሃትንና ጭንቀትን ለማስወገድ እንደመደበቂያነት ሲገለገሉበት ይታያሉ፡፡ ድርጊቱን ከፈፀሙ በኋላ ግን በአብዛኞቹ የማዘን እና የመፀፀት ስሜት ስለሚከተልባቸው ዳግመኛ ላለመፈፀምቃል ይገባሉ፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን መልሰው ያገኙታል፡፡   በትዳር ሕይወት አሊያም ደግሞ በፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ ያሉ ሴሰኞች ከፍቅረኞቻቸው ውጭ ከተለያ ሰዎች ጋር ወሲብ ስለሚፈፅሙ የተቃራኒ ጾታግንኙነታቸው ሊበላሽ ይችላል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በሚኖራቸው የወሲብ ግንኙነት አለመጣጣም ሊኖር ስለሚችልከሚወዱት ሰው ጋር ለመያየት ሊፈጠር ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ባሕሪይ ጋር በተያያዘ በሥራ ገበታ ኃላፊነትን አለመወጣት እና ያልተገባባሕሪይን ስለሚያሳዩ በሥራ ሕይወታቸው ውጤታማ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡   የወሲብ ሱስ መገለጫዎችከተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ መፈፀም ወይንም መፈለግ ከሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ረጅም ጊዜን የወሲብፍጎትን ለሟሟላት በሚደረጉ ጥረቶች ማሳለፍ ለወሲብ ቅድሚያ በመስጠት ሌሎች በማህበረሰቡ የተሰጡ የሥራ፣ የቤተሰብ እና የትዳር ኃላፊነቶችንችላ ማለት ተመሳሳይ የሆነ ወሲባዊ እርካታን ለማግኘት ይበልጥ ለመጨመር መገደድ በተደጋጋሚ ሁኔታ ወሲብን መፈጸም ከሰዎች ጋር የሚመሠረቱግንኙነቶች በቀዳነት በወሲብ ላይ ያተኮሩ መሆን ወሲባዊ ባህሪን ሳያስታግሱ ሲቀሩ የባህሪ መለዋወጥ (መቆጣት፣ መነጫነጭ..)       መንስኤው መንድነው?   የወሲብ ሱሰኝነት የተለያዩ መንስኤዎች በአንድ ላይ ተዳምረው የሚያመጡት ችግር ነው፡፡ከዚህም ውስጥ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለው በልጅነት አስተዳደግ ወቅት የሚፈጠሩ እናከወሲብ ጋር የተያያዙ ክስተቶች መፈጠር ነው፡፡ በተለይ በልጅነት መደፈር ወይም ደግሞከትክክለኛው ዕድሜ ቀደም ብሎ የሚከሰቱ ወሲባዊ ልምምዶች ያንን ግለሰብ በቀሪ ህይወቱከወሲብ ጋር የተያያዘ ጥብቅ ቁርኝት እንዲኖረው ያደርጋሉ፡፡   በዘርፋ በተደረገ ጥናት ሊታወቅ የቻውም በወሲብ ሱሰኝነት ተጠቂ ከሚሆኑት ሰዎችመካከል ከግማሽ በላይ በልጅነታቸው ወቅት ወሲብን መፈጸም የጀመሩ አሊያም ወሲባዊጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ነው፡፡   ከዚህም ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው የወሲብ ግንኙነታቸው ወቅት የአስገድዶ መደፈር ሰለባየሆኑ ሴቶች በቀሪው ወሲባዊ ህይወታቸው ሁለት ዓይነት አማራጮችን ሊከተሉ ይችላሉ፡፡አንደኛው ለወሲብ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻን ማዳበር እና ምንም ዓይነት ደስታ እንደማይገኝበት አምነው መቀበል ሲሆን ፣ ሌላኛው ደግሞ ከፍተኛ የሆነየወሲብ ፍላጎት ማዳበር ውስጣዊ ጠባሳን የበለጠ ወሲብ በመፈጸም ለመሸፋፈን መሞከር ነው፡፡ እነዚህም ሴቶች ወሲባዊ ስሜታቸውን ለማርካታበሚል ብቻ ምንም አይነት ውስጣዊ መተዋወቅ እና መግባባት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ወሲብን መፈፀም ቀላል ነው የሚሆንላቸው፡፡ በዚህምባሕሪያቸው የተነሣ እውነተኛ የሆነ ፍቅር ከፊታቸው ሆኖ በሚገኝበት ሁኔታ ውስጥ ለመሰብሰብ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም እንኳ በአካላዊ ስሜት ብቻበመገፋፋት በሚኖራቸው ወሲባዊ ህይወት የፍቅር ሕይወታቸው የተበላሸ መሆኑ አይቀርም፡፡   በተጨማሪም በአንዳንድ ሁኔታዎች ከልክ በላይ የሆነ ወሲባዊ እንቅስቃሴ ለራሳችን የሚኖረንን አመለካከት እና የበታችነት ስሜት ሊያንፀባርቅይችላል፡፡ የወሲብ ስሜት ከስጦታዎች አንዱ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊት ከሚገኘው የደስታ እና የእርካታ ስሜት ባሻገር ተፈጥሮን ለመቀጠል እና በጊዜየተገደበውን የሰው ልጅ ሕይወት መቀጠያ ታላቅ ጥበብ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ ይሄንን  የተሠጠንን ታላቅ ሥጦታ በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ይሄም ማለት በውስጣችን ያለውን ተፈጥሪአዊ ስሜት በቁጥጥራችን ሥር በማድረግ በተገቢው ቦታ፣ በተገቢው ጊዜ፣ ከተገቢው ሰው ጋር ሆኖመጠቀም የተፈጥሮ ህግ ሥር የሚገኝ በመሆኑ ይህንን ተገንዝበን ትክክለኛ የሆነ የወሲብ ባሕሪይን በዕድሜያችንና ከምንኖርበት ማበረሰብ እና ከጊዜውጋር በማጣጣም ማስኬድ ጤናማነትን ይገልፃል፡፡   ምክንያቱም አርስቶትል እንደተናገረው የሰው ልጅ የመጨረሻ ፍላጎቱ ደስታን መጎናፀፍ እንደመሆኑ ይህንን ደስታ ቋሚ ለማድረግ ደግሞ ስሜታችንን፣ድርጊታችንና ፍላጎታችንን ከልክ ሳያልፍና ጉድለት ሳይኖርበት የተጠበቀ ማለትም መካከለኛ ወይንም ሚዛናዊ ማድረግ አለብን፡፡ በጣም የበዛም ሆነበጣም ያነሰ ነገር ጎጂ በመሆኑ ነገሮችን ሁሉ በሁለቱ መካከል ሚዛናችንን መጠበቅና ማመጣጠን መቻል አለብን፡፡      

ማጨስ ለአዕምሮ ህመም ያጋልጣል

ሲጋራ ማጨስ ለሳምባ ካንሰርና ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ የጥናት ውጤቶች አሳይተዋል፡፡ ሰሞኑን በዩናይትድ ስቴትስ ይፋ የተደረገው አንድ የጥናት ውጤት በበኩሉ በየዕለቱ...

የአልኮል ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦች

ሀሰን አሰፋ (የኛ ፕሬስ) በፍቅረኝነት ጊዜና በትዳር ውስጥ ሴቶች ‹‹ባለቤቴን ከአልኮል ሱሰኝነት እንዴት ልታደገው እችል ይሆን?›› በማለት ይጨነቃሉ፡፡ ወንዶችም ፍቅረኛቸው የአልኮል ተጠቂ ከሆነች እንዲሁ ነው፡፡...

ካፌይን እና መዘዞቹ

ካፌይን አዕምሮን ለማነቃቃት የሚረዳና በተለይ በቡና፣ በሻይና በተለያዩ የለስላሣ መጠጦች ውስጥ በስፋት የሚገኝ ኬሚካል ነው፡፡ ካፌይን ከእነዚህ መጠጦች በተጨማሪ በቸኮሌቶች፣ በብስኩቶችና በተለያዩ የህመም ማስታገሻና...

ሲጋራ ለማቆም የሚረዳው ተክል

በ ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ) ይህ ተክል በአማርኛ በትንጀን (ደብርጃን) የሚባል ስም ሲኖረው በዎልፍ ሌስላው የተዘጋጀው የእንግሊኛ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ደግሞ ‹‹ማደርቻ፣ መደርቻ›› ብሎ ይገልፀዋል፡፡ ለጋራ መግባባት...